አብድዩ
1 የአብድዩ* ራእይ፦
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦+
“ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምተናል፤
በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦
‘ተነሱ፤ እሷን ለመውጋት እንዘጋጅ።’”+
2 “እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር አድርጌሃለሁ፤
አንተ እጅግ ተንቀሃል።+
3 አንተ በቋጥኝ መሸሸጊያ ውስጥ የምትኖር፣
መኖሪያህን በከፍታ ቦታ ላይ ያደረግክ፣
በልብህ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣
የልብህ እብሪት አታሎሃል።+
የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ አይደለም?
ደግሞስ ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ
ጥቂት ቃርሚያ አያስቀሩም?+
6 ኤሳው ምንኛ ተበረበረ!
የተደበቀው ውድ ሀብቱ ምንኛ ተፈለገ!
7 እስከ ድንበሩ ድረስ እንድትሄድ አስገደዱህ።
አጋሮችህ* ሁሉ አታለውሃል።
ከአንተ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች አይለውብሃል።
ከአንተ ጋር የሚበሉ ሰዎች ከሥርህ መረብ ይዘረጉብሃል፤
አንተ ግን አታስተውለውም።
11 ዳር ቆመህ ትመለከት በነበረበት ጊዜ፣
እንግዶች ሠራዊቱን ማርከው በወሰዱበትና+
የባዕድ አገር ሰዎች በበሩ ገብተው በኢየሩሳሌም ላይ ዕጣ በተጣጣሉበት ጊዜ፣+
አንተም ልክ እንደ እነሱ አደረግክ።
12 በወንድምህ ቀን ይኸውም ወንድምህ ክፉ ነገር በደረሰበት ቀን መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤+
የይሁዳ ሕዝብ በጠፋበት ቀን ሐሴት ማድረግ አልነበረብህም፤+
ደግሞም በጭንቀታቸው ቀን በእብሪት መናገር አይገባህም ነበር።
13 በጥፋታቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር መምጣት አልነበረብህም፤+
በጥፋቱ ቀን በደረሰበት መከራ መፈንደቅ አይገባህም ነበር፤
ደግሞም ጥፋት በደረሰበት ቀን ሀብቱን መውሰድ አልነበረብህም።+
15 ይሖዋ በብሔራት ሁሉ ላይ የሚነሳበት ቀን ቀርቧልና።+
አንተ በእሱ ላይ እንዳደረግከው በአንተም ላይ ይደረጋል።+
በሌሎች ላይ ያደረግከው ነገር በገዛ ራስህ ላይ ይመለሳል።
16 እናንተ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ እንደጠጣችሁ፣
ልክ እንደዚሁ ብሔራት በሙሉ ዘወትር ይጠጣሉ።+
ይጠጣሉ፤ ደግሞም ይጨልጡታል፤
ፈጽሞ እንዳልነበሩም ይሆናሉ።
18 የያዕቆብ ቤት እሳት፣
የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤
የኤሳው ቤት ደግሞ እንደ ገለባ ይሆናል፤
እነሱም ያቃጥሏቸዋል፤ ይበሏቸዋልም፤
ከኤሳውም ቤት የሚተርፍ አይኖርም፤+
ይሖዋ ራሱ ተናግሯልና።
የኤፍሬምን መሬትና የሰማርያን መሬት ይወርሳሉ፤+
ቢንያምም ጊልያድን ይወርሳል።
በሰፋራድ የነበሩት ከኢየሩሳሌም በግዞት የተወሰዱ ሰዎችም የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።+