ሚክያስ
የእስራኤልን ፈራጅ ጉንጩን በዱላ ይመቱታል።+
2 ከይሁዳ አእላፋት* መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽው
ቤተልሔም ኤፍራታ+ ሆይ፣
ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣
በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።+
3 ስለዚህ ልትወልድ የተቃረበችው ሴት እስክትወልድ ድረስ
አሳልፎ ይሰጣቸዋል።
የቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ።
አሦራዊው ምድራችንን ሲወርና ክልላችንን ሲረግጥ
እሱ ይታደገናል።+
7 የተረፉት የያዕቆብ ወገኖች በብዙ ሕዝቦች መካከል፣
ከይሖዋ ዘንድ እንደሚወርድና
ሰውን ተስፋ እንደማያደርግ
ወይም የሰው ልጆችን እንደማይጠባበቅ ጠል፣
በአትክልትም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ።
8 በዱር እንስሳት መካከል እንዳለ አንበሳ፣
በሚያልፍበት ጊዜ እየረጋገጠና እየሰባበረ እንደሚሄድ፣
በበግ መንጎች መካከል እንዳለ ደቦል አንበሳ፣
የተረፉት የያዕቆብ ወገኖችም በብሔራት፣
በብዙ ሕዝቦችም መካከል እንዲሁ ይሆናሉ፤
ሊያስጥል የሚችልም አይኖርም።
9 እጅህ ከባላጋራዎችህ በላይ ከፍ ከፍ ትላለች፤
ጠላቶችህም ሁሉ ይወገዳሉ።”
10 “በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣
“ፈረሶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ ሠረገሎችህንም አጠፋለሁ።
11 በምድርህ ላይ የሚገኙትን ከተሞች እደመስሳለሁ፤
የተመሸጉ ስፍራዎችህንም ሁሉ አፈራርሳለሁ።
13 የተቀረጹ ምስሎችህንና ዓምዶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤
ከእንግዲህም ወዲህ ለእጆችህ ሥራ አትሰግድም።+
15 ታዛዥ ያልሆኑትን ብሔራት፣
በቁጣና በንዴት እበቀላለሁ።”