ዘፀአት 23:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የሚጠላህ ሰው አህያ ጭነቱ ከብዶት ወድቆ ብታይ ዝም ብለህ አትለፈው። ከዚህ ይልቅ ጭነቱን ከእንስሳው ላይ ለማውረድ እርዳው።+ ዘሌዋውያን 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “‘የሕዝብህን ልጆች አትበቀል፤+ በእነሱም ላይ ቂም አትያዝ፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።+ እኔ ይሖዋ ነኝ። ሉቃስ 10:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው። ገላትያ 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እንግዲያው ይህን ለማድረግ የሚያስችል አጋጣሚ* እስካገኘን ድረስ ለሁሉም፣ በተለይ ደግሞ በእምነት ለሚዛመዱን ሰዎች መልካም እናድርግ።
27 እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣* በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤+ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’”+ አለው።