1 ሳሙኤል 17:37 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 37 ዳዊትም በመቀጠል “ከአንበሳና ከድብ ጥፍር የታደገኝ ይሖዋ አሁንም ከዚህ ፍልስጤማዊ እጅ ይታደገኛል” አለ።+ በዚህ ጊዜ ሳኦል ዳዊትን “እሺ ሂድ፤ ይሖዋ ከአንተ ጋር ይሁን” አለው። መዝሙር 27:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው። ማንን እፈራለሁ?+ ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+ ማን ያሸብረኛል? ኢሳይያስ 12:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው!+ በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤+ያህ* ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው፤ለእኔም አዳኝ ሆኖልኛል።”+ ዳንኤል 6:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እሱ ይታደጋል፤+ ደግሞም ያድናል፤ በሰማያትና በምድርም ተአምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን ያደርጋል፤+ ዳንኤልን ከአንበሶች መዳፍ ታድጎታልና።”
37 ዳዊትም በመቀጠል “ከአንበሳና ከድብ ጥፍር የታደገኝ ይሖዋ አሁንም ከዚህ ፍልስጤማዊ እጅ ይታደገኛል” አለ።+ በዚህ ጊዜ ሳኦል ዳዊትን “እሺ ሂድ፤ ይሖዋ ከአንተ ጋር ይሁን” አለው።