12 በዚያ ቀን በእርግጥ እንዲህ ትላለህ፦
“ይሖዋ ሆይ፣ ተቆጥተኸኝ የነበረ ቢሆንም
ቁጣህ ቀስ በቀስ ስለበረደ
ደግሞም ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ።+
2 እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው!+
በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤+
ያህ ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው፤
ለእኔም አዳኝ ሆኖልኛል።”+
3 ከመዳን ምንጮች
በደስታ ውኃ ትቀዳላችሁ።+
4 በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦
“ይሖዋን አመስግኑ! ስሙን ጥሩ፤
ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+
ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱን አውጁ።+
5 አስደናቂ ነገሮችን+ ስላከናወነ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።+
ይህም በመላው ምድር ይታወጅ።
6 እናንተ የጽዮን ነዋሪዎች ሆይ፣ ጩኹ፤ በደስታም እልል በሉ፤
የእስራኤል ቅዱስ በመካከላችሁ ታላቅ ነውና።”