ኢሳይያስ
30 “ግትር ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው”+ ይላል ይሖዋ፤
“በኃጢአት ላይ ኃጢአት ለመጨመር
የእኔን ሳይሆን የራሳቸውን ዕቅድ ይፈጽማሉ፤+
ደግሞም ኅብረት ይፈጥራሉ፤* ይህን የሚያደርጉት ግን በመንፈሴ አይደለም።
3 ይሁንና ፈርዖን የሚያደርግላችሁ ጥበቃ ለኀፍረት፣
በግብፅ ጥላ ሥር መጠለልም ለውርደት ይዳርጋችኋል።+
4 መኳንንቱ በጾዓን+ ናቸውና፤
መልእክተኞቹም ሃኔስ ደርሰዋል።
6 በደቡብ እንስሳት ላይ የተላለፈ ፍርድ፦
አንበሳ፣ አዎ የሚያገሳ አንበሳ ባለበት፣
እፉኝት እንዲሁም የሚበርና የሚያቃጥል እባብ* በሚገኙበት፣
አስጨናቂና አስቸጋሪ ሁኔታዎች በሞሉበት ምድር
ሀብታቸውን በአህያ ላይ፣
ቁሳቁሳቸውንም በግመል ሻኛ ላይ ጭነው ይሄዳሉ።
ሆኖም እነዚህ ነገሮች ለሕዝቡ ምንም ጥቅም አያስገኙለትም።
7 ግብፅ የምትሰጠው እርዳታ ምንም እርባና የለውምና።+
ስለዚህ እሷን “ረዓብ፣+ ሥራ ፈታ የምትጎለት” ብዬ ጠርቻታለሁ።
10 ባለ ራእዮችን ‘ከእንግዲህ ራእይ አትዩ’ ይላሉ፤
ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እውነተኛ ራእይ አትንገሩን።+
የሚጥም* ነገር ንገሩን፤ አሳሳች የሆነ ሕልም አልሙልን።+
11 ከመንገዱ ዞር በሉ፤ ጎዳናውንም ልቀቁ።
የእስራኤልን ቅዱስ በፊታችን አታድርጉ።’”+
12 ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፦
“ይህን ቃል ስለናቃችሁ፣+
በማጭበርበርና በማታለል ስለታመናችሁ፣
በዚያም ላይ ስለተደገፋችሁ፣+
13 ይህ በደል እንደተሰነጠቀ ቅጥር፣
ሊወድቅ እንደተቃረበ ያዘመመ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።
ሳይታሰብ በድንገት ይፈርሳል።
14 ሸክላ ሠሪ እንደሠራው ትልቅ እንስራ ይሰባበራል፤
እንክትክቱ ከመውጣቱ የተነሳ ከምድጃ ፍም ለመውሰድ
ወይም ከረግረጋማ ቦታ* ውኃ ለመጨለፍ የሚያስችል
አንድም ገል አይገኝም።”
15 የእስራኤል ቅዱስ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
“ወደ እኔ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤
ሳትረበሹ፣ ተማምናችሁ በመኖር ብርቱ መሆናችሁን ታሳያላችሁ።”+
እናንተ ግን ፈቃደኞች አልሆናችሁም።+
16 ይልቁንም “አይሆንም፣ በፈረሶች እንሸሻለን!” አላችሁ።
ደግሞም ትሸሻላችሁ።
“በፈጣን ፈረሶችም እንጋልባለን!” አላችሁ።+
ስለሆነም የሚያሳድዷችሁ ሰዎች ፈጣኖች ይሆናሉ።+
17 አንድ ሰው ከሚሰነዝረው ዛቻ የተነሳ ሺዎች ይሸበራሉ፤+
በተራራ አናት ላይ እንደተተከለ ምሰሶና
በኮረብታ ላይ እንደቆመ ለምልክት የሚያገለግል ግንድ ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፣
አምስት ሰዎች ከሚሰነዝሩት ዛቻ የተነሳ ትሸሻላችሁ።+
ይሖዋ የፍትሕ አምላክ ነውና።+
እሱን በተስፋ* የሚጠባበቁ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።+
19 ሕዝቡ በጽዮን ይኸውም በኢየሩሳሌም በሚኖርበት ጊዜ+ ፈጽሞ አታለቅስም።+ እርዳታ ለማግኘት በምትጮኽበት ጊዜ በእርግጥ ሞገስ ያሳይሃል፤ ጩኸትህን እንደሰማም ይመልስልሃል።+ 20 ይሖዋ የጭንቀትን ምግብና የጭቆናን ውኃ ቢሰጥህም+ እንኳ ታላቁ አስተማሪህ ከእንግዲህ ራሱን አይሰውርም፤ በገዛ ዓይኖችህም ታላቁን አስተማሪህን+ ታያለህ። 21 ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ዞር ብትል ጆሮህ ከኋላህ “መንገዱ ይህ ነው።+ በእሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።+
22 የተቀረጹ ምስሎችህ የተለበጡበትን ብርና ከብረት የተሠሩ ሐውልቶችህ*+ የተለበጡበትን ወርቅ ታረክሳለህ። እንደ ወር አበባ ጨርቅ “ከዚህ ጥፉ!”* በማለት አሽቀንጥረህ ትጥላቸዋለህ።+ 23 እሱም መሬት ላይ ለምትዘራው ዘር ዝናብ ይሰጥሃል፤+ ምድሪቱም የምታፈራው እህል የተትረፈረፈና ምርጥ* ይሆናል።+ በዚያም ቀን ከብቶችህ ሰፊ በሆነ የግጦሽ መስክ ይሰማራሉ።+ 24 መሬቱንም የሚያርሱ ከብቶችና አህዮች በእንቧጮ* የተቀመመ እንዲሁም በላይዳና በመንሽ የተለየ ገፈራ ይበላሉ። 25 ብዙ እልቂት በሚደርስበትና ግንቦች በሚፈርሱበት ቀን፣ በረጅም ተራራና ከፍ ባለ ኮረብታ ሁሉ ላይ ጅረቶች ይፈስሳሉ፤+ የውኃ መውረጃ ቦዮችም ይኖራሉ። 26 የሙሉ ጨረቃ ብርሃንም እንደ ፀሐይ ብርሃን ይሆናል፤ ይሖዋ የሕዝቡን ስብራት* በሚጠግንበትና+ በእሱ ምት የተነሳ የደረሰባቸውን ከባድ ቁስል በሚፈውስበት ቀን+ የፀሐይ ብርሃን፣ እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይደምቃል።+
27 እነሆ፣ የይሖዋ ስም በቁጣው እየነደደ
ጥቅጥቅ ካለ ደመና ጋር ከሩቅ ይመጣል።
ከንፈሮቹ በቁጣ ተሞልተዋል፤
ምላሱም እንደሚባላ እሳት ነው።+
28 መንፈሱ* እስከ አንገት ድረስ እንደሚደርስ የሚያጥለቀልቅ ወንዝ ነው፤
ብሔራትን በጥፋት ወንፊት* ይነፋቸዋል፤
በሕዝቦች መንጋጋም መንገድ እንዲስቱ የሚያደርግ ልጓም ይገባል።+
29 እናንተ ግን፣ ለበዓል በምትዘጋጁበት* ጊዜ+
በሌሊት እንደሚዘመረው ያለ መዝሙር ትዘምራላችሁ፤
ደግሞም ወደ እስራኤል ዓለት፣+ ወደ ይሖዋ ተራራ ሲጓዝ
ዋሽንት ይዞ* እንደሚሄድ ሰው
ልባችሁ ሐሴት ያደርጋል።
30 ይሖዋ ግርማ የተላበሰ ድምፁ+ እንዲሰማ ያደርጋል፤
የክንዱንም ብርታት ይገልጣል፤+
ይህን የሚያደርገው በሚነድ ቁጣ፣+ በሚባላ የእሳት ነበልባል፣+
ሳይታሰብ በሚወርድ ዶፍ፣+ ነጎድጓድ በቀላቀለ ውሽንፍርና በበረዶ ድንጋይ+ ታጅቦ ክንዱ ጥቃት ለመሰንዘር ወደ ታች በሚወርድበት ጊዜ ነው።
የእንጨት ክምሩ ጥልቀትና ስፋት ያለው እንዲሆን አድርጓል፤
ብዙ እሳትና እንጨትም አለ።
የይሖዋ እስትንፋስ ልክ እንደ ድኝ ጅረት
በእሳት ያያይዘዋል።