ሚክያስ
2 ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦
“ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራና
ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+
እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤
በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”
ሕግ* ከጽዮን፣
የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣
ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+
አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤
ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+
7 የሚያነክሰው የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩት* አደርጋለሁ፤+
ወደ ሩቅ ስፍራ የተወሰደውንም ኃያል ብሔር አደርገዋለሁ፤+
ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም
በጽዮን ተራራ በእነሱ ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።
9 አሁንስ ድምፅሽን ከፍ አድርገሽ የምትጮኺው ለምንድን ነው?
10 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት
ተንፈራገጪ፤ አቃስቺም፤
አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትሰፍሪያለሽና።
11 አሁንም ብዙ ብሔራት በአንቺ ላይ ይሰበሰባሉ፤
እነሱም ‘የረከሰች ትሁን፤
ዓይኖቻችንም ይህ በጽዮን ላይ ሲደርስ ይመልከቱ’ ይላሉ።
12 ይሁንና የይሖዋን ሐሳብ አያውቁም፤
ዓላማውንም አይረዱም፤
እሱ ገና እንደታጨደ እህል ወደ አውድማ ይሰበስባቸዋልና።
በማጭበርበር ያገኙት ትርፍ ለይሖዋ የተወሰነ እንዲሆን፣
ሀብታቸውም ለምድር ሁሉ ጌታ ብቻ እንዲውል ታደርጊያለሽ።”+