መዝሙር
የዳዊት ማህሌት።
29 እናንተ የኃያላን ልጆች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤
ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+
2 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ።
ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ።*
3 የይሖዋ ድምፅ ከውኃዎች በላይ ተሰማ፤
ክብር የተጎናጸፈው አምላክ አንጎደጎደ።+
ይሖዋ ከብዙ ውኃዎች በላይ ነው።+
4 የይሖዋ ድምፅ ኃይለኛ ነው፤+
የይሖዋ ድምፅ ክብራማ ነው።
5 የይሖዋ ድምፅ አርዘ ሊባኖስን ይሰብራል፤
አዎ፣ ይሖዋ አርዘ ሊባኖስን ይሰባብራል።+
በቤተ መቅደሱም ውስጥ ያሉ ሁሉ “ክብር ለአምላክ!” ይላሉ።
11 ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል።+
ይሖዋ ሰላም በመስጠት ሕዝቡን ይባርካል።+