10 የሰለሞን ምሳሌዎች።+
ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤+
ሞኝ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናል።
2 በክፋት የተገኘ ሀብት ምንም ፋይዳ የለውም፤
ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።+
3 ይሖዋ ጻድቅ ሰው እንዲራብ አያደርግም፤+
የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል።
4 ሥራ የፈቱ እጆች ያደኸያሉ፤+
ትጉ እጆች ግን ብልጽግና ያስገኛሉ።+
5 ጥልቅ ማስተዋል ያለው ልጅ እህሉን በበጋ ይሰበስባል፤
አሳፋሪ ልጅ ግን በመከር ወቅት ለጥ ብሎ ይተኛል።+
6 በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፤+
የክፉዎች አፍ ግን የዓመፅ ዕቅዳቸውን ይሰውራል።
7 የጻድቅ መታሰቢያ በረከት ያስገኛል፤+
የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።+
8 ጥበበኛ ልብ ያለው ሰው መመሪያዎችን ይቀበላል፤+
በሞኝነት የሚናገር ሰው ግን ጥፋት ይደርስበታል።+
9 ንጹሕ አቋሙን ጠብቆ የሚሄድ ያለስጋት ይመላለሳል፤+
መንገዱን ጠማማ የሚያደርግ ግን ይጋለጣል።+
10 በተንኮል የሚጣቀስ ሐዘን ያመጣል፤+
በሞኝነት የሚናገር ሰውም ጥፋት ይደርስበታል።+
11 የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፤+
የክፉዎች አፍ ግን የዓመፅ ዕቅዳቸውን ይሰውራል።+
12 ጥላቻ ጭቅጭቅ ያስነሳል፤
ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ይሸፍናል።+
13 አስተዋይ በሆነ ሰው ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፤+
በትር ግን ማስተዋል ለጎደለው ሰው ጀርባ ነው።+
14 ጥበበኞች እውቀትን እንደ ውድ ሀብት ያከማቻሉ፤+
የሞኝ ሰው አፍ ግን ጥፋት ይጋብዛል።+
15 የባለጸጋ ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው።
ድሆችን የሚያጠፋቸው ድህነታቸው ነው።+
16 የጻድቅ ሰው ሥራ ወደ ሕይወት ይመራል፤
የክፉ ሰው ፍሬ ግን ወደ ኃጢአት ይመራል።+
17 ተግሣጽን የሚቀበል ለሌሎች የሕይወት መንገድ ይሆናል፤
ወቀሳን ችላ የሚል ግን ሌሎች መንገድ እንዲስቱ ያደርጋል።
18 ጥላቻውን የሚሸፋፍን ሰው ሐሰት ይናገራል፤+
ተንኮል ያዘለ ወሬ የሚያስፋፋ ሰውም ሞኝ ነው።
19 ከቃላት ብዛት ስህተት አይታጣም፤+
ከንፈሩን የሚገታ ግን ልባም ሰው ነው።+
20 የጻድቅ አንደበት ጥራት ያለው ብር ነው፤+
የክፉ ሰው ልብ ግን እርባና የለውም።
21 የጻድቅ ከንፈሮች ብዙዎችን ይመግባሉ፤+
ሞኞች ግን ማስተዋል ስለሚጎድላቸው ይሞታሉ።+
22 የይሖዋ በረከት ባለጸጋ ታደርጋለች፤+
እሱም ከበረከቱ ጋር ሥቃይን አይጨምርም።
23 አሳፋሪ ምግባር መፈጸም ለሞኝ ሰው እንደ ጨዋታ ነው፤
ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ጥበበኛ ነው።+
24 ክፉ ሰው የፈራው ነገር ይደርስበታል፤
ጻድቅ ግን የተመኘውን ያገኛል።+
25 አውሎ ነፋስ ሲያልፍ ክፉ ሰው ተጠርጎ ይወሰዳል፤+
ጻድቅ ግን ለዘላለም እንደሚኖር መሠረት ነው።+
26 ኮምጣጤ ጥርስን፣ ጭስም ዓይንን እንደሚጎዳ፣
ሰነፍም ለሚልከው ሰው እንዲሁ ነው።
27 ይሖዋን መፍራት ዕድሜን ያስረዝማል፤+
የክፉዎች ዕድሜ ግን በአጭሩ ይቀጫል።+
28 የጻድቃን ተስፋ ደስታ ያስገኛል፤+
የክፉዎች ተስፋ ግን መና ይቀራል።+
29 የይሖዋ መንገድ፣ ያለነቀፋ ለሚመላለስ ሰው መሸሸጊያ ነው፤+
ለክፉ አድራጊዎች ግን መጥፊያቸው ነው።+
30 ጻድቅ ሰው ምንም ነገር አይጥለውም፤+
ክፉዎች ግን በምድር ላይ መኖራቸውን አይቀጥሉም።+
31 የጻድቅ አፍ ጥበብን ያፈልቃል፤
ጠማማ ምላስ ግን ትቆረጣለች።
32 የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ደስ የሚያሰኘው ነገር ምን እንደሆነ ያውቃሉ፤
የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነው።