ኢሳይያስ
2 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፦+
3 ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦
“ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣
ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+
እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤
በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+
እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣
ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+
አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤
ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+
6 አንተ ሕዝብህን ይኸውም የያዕቆብን ቤት ትተሃል፤+
ምክንያቱም እነሱ ከምሥራቅ በመጡ ነገሮች ተሞልተዋል፤
እንደ ፍልስጤማውያን የአስማት ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፤+
በባዕድ አገር ሰዎች ልጆችም ተጥለቅልቀዋል።
7 ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤
ሀብታቸውም ገደብ የለውም።
ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤
ሠረገሎቻቸውም ስፍር ቁጥር የላቸውም።+
8 ምድራቸውም ከንቱ በሆኑ አማልክት ተጥለቅልቃለች።+
የገዛ እጃቸው ለሠራው፣
የገዛ ጣታቸውም ላበጀው ነገር ይሰግዳሉ።
9 በመሆኑም ሰው አንገቱን ይደፋል፤ ኀፍረትም ይከናነባል፤
አንተም ይቅር ልትላቸው አትችልም።
በዚያም ቀን ይሖዋ ብቻ ከፍ ከፍ ይደረጋል።
ቀኑ ትዕቢተኛና ኩሩ በሆነው ሁሉ ላይ፣
ከፍ ባለውም ሆነ ዝቅ ባለው ሁሉ ላይ ይመጣል፤+
13 ታላላቅ በሆኑትና ከፍ ከፍ ባሉት አርዘ ሊባኖሶች ሁሉ ላይ
እንዲሁም በባሳን የባሉጥ ዛፎች ሁሉ ላይ፣
14 ታላላቅ በሆኑት ተራሮች ሁሉና
በረጃጅም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣
15 ረጅም በሆነ ማማ ሁሉና ጠንካራ በሆነ ግንብ ሁሉ ላይ፣
በሚያማምሩ ጀልባዎች ሁሉ ላይ ይደርሳል።
17 ትዕቢተኛ ሰው ይዋረዳል፤
እብሪተኞችም አንገታቸውን ይደፋሉ።*
በዚያም ቀን ይሖዋ ብቻ ከፍ ከፍ ይደረጋል።
18 ከንቱ የሆኑት አማልክት ሙሉ በሙሉ ይወገዳሉ።+
20 በዚያ ቀን፣ ሰዎች በፊታቸው ይሰግዱ ዘንድ
ለራሳቸው የሠሯቸውን ከንቱ የሆኑ የብርና የወርቅ አማልክት
21 ይሖዋ ምድርን በሽብር ለማንቀጥቀጥ በሚነሳበት ጊዜ፣
አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳና
ከታላቅ ግርማው የተነሳ
በዓለት ዋሻዎችና
በቋጥኝ ስንጥቆች ውስጥ ይደበቃሉ።
22 ለራሳችሁ ስትሉ፣
ከአፍንጫው እንደሚወጣ እስትንፋስ በሆነ ሰው* አትታመኑ።
ለመሆኑ እሱ ያን ያህል ቦታ እንዲሰጠው የሚያደርግ ምን ነገር አለ?