ኢዮብ
18 ሹሃዊው በልዳዶስ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦
2 “እንዲህ ያለ ንግግር መናገራችሁን* የምትቀጥሉት እስከ መቼ ነው?
በተወሰነ መጠን ልታስተውሉ ይገባል፤ ያን ጊዜ እኛ እንናገራለን።
5 አዎ፣ የክፉዎች ብርሃን ይጠፋል፤
የእሳቱም ነበልባል አይበራም።+
6 በድንኳኑ ውስጥ ያለው ብርሃን በእርግጥ ይጨልማል፤
በላዩ ያለው መብራትም ይጠፋል።
7 ብርታት የተሞላበት እርምጃው ያጥራል፤
የገዛ ዕቅዱም ይጥለዋል።+
8 እግሩ ወደ መረብ ይመራዋልና፤
በመረቡም ገመድ ይተበተባል።
9 ወጥመድ ተረከዙን ይይዘዋል፤
ወስፈንጥርም ያጠምደዋል።+
10 በመሬት ላይ ሸምቀቆ በስውር ይቀመጥለታል፤
ወጥመድም በመንገዱ ላይ ይጠብቀዋል።
11 ሽብር ከሁሉም አቅጣጫ ፍርሃት ይለቅበታል፤+
እግር በእግርም ያሳድደዋል።
13 ቆዳው ተበልቷል፤
እጅግ ቀሳፊ የሆነ በሽታ* እጆቹንና እግሮቹን ይበላል።
16 ሥሮቹ ከእሱ በታች ይደርቃሉ፤
ቅርንጫፎቹ ደግሞ ከእሱ በላይ ይጠወልጋሉ።
17 መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፤
በጎዳናም ላይ ስሙ አይታወቅም።*
18 ከብርሃን ወደ ጨለማ ይወሰዳል፤
ፍሬያማ ከሆነችውም ምድር ይባረራል።
19 በሕዝቡ መካከል ልጆችም ሆኑ ዘሮች አይኖሩትም፤
በሚኖርበት ስፍራም* የሚተርፍ ሰው አይኖረውም።
20 የሚጠፋበት ቀን ሲደርስ በምዕራብ ያሉ ሰዎች ይደነግጣሉ፤
በምሥራቅ ያሉ ሰዎችም በፍርሃት ይዋጣሉ።
21 የክፉ አድራጊ ድንኳኖች፣
አምላክን የማያውቁ ሰዎች ስፍራም እንዲህ ያለ ነገር ይደርስባቸዋል።”