ሆሴዕ
10 “እስራኤል ፍሬ የሚሰጥ እየተበላሸ* ያለ ወይን ነው።+
መሠዊያዎቻቸውን የሚሰባብር፣ ዓምዶቻቸውንም የሚያፈራርስ አለ።
3 እነሱም ‘ንጉሥ የለንም፤+ ይሖዋን አልፈራንምና።
ንጉሥ ቢኖረንስ ምን ሊያደርግልን ይችላል?’ ይላሉ።
5 የሰማርያ ነዋሪዎች በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ስጋት ያድርባቸዋል።+
ሕዝቡም ሆኑ በእሱና በክብሩ ሐሴት ያደረጉት የባዕድ አምላክ ካህናት
ለእሱ ያዝናሉ፤
ከእነሱ ተለይቶ በግዞት ይወሰዳልና።
6 ለአንድ ታላቅ ንጉሥ እንደሚቀርብ ስጦታ ወደ አሦር ይወሰዳል።+
ኤፍሬም ውርደት ይከናነባል፤
እስራኤልም በተከተለው ምክር የተነሳ ያፍራል።+
8 የእስራኤል ኃጢአት+ የሆኑት በቤትአዌን+ የሚገኙ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ይወድማሉ።+
መሠዊያዎቻቸውን እሾህና አሜኬላ ይወርሷቸዋል።+
ሰዎች ተራሮቹን ‘ሸሽጉን!’
ኮረብቶቹንም ‘በላያችን ውደቁ!’ ይሏቸዋል።+
9 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ከጊብዓ ዘመን ጀምሮ ኃጢአት ሠርታችኋል።+
እነሱ በዚያ ጸንተዋል።
በጊብዓ የተካሄደው ጦርነት የዓመፅን ልጆች አልፈጃቸውም።*
10 በፈለግኩ ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ።
ሁለቱ በደሎቻቸው በላያቸው በሚጫኑበት ጊዜ*
ሕዝቦች በእነሱ ላይ ይሰበሰባሉ።
11 ኤፍሬም ማበራየት የምትወድ የተገራች ጊደር ነው፤
በመሆኑም ያማረ አንገቷን አተረፍኩ።
ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ለእሱ ያለሰልሳል።
12 ለራሳችሁ የጽድቅን ዘር ዝሩ፤ ታማኝ ፍቅርንም እጨዱ።
14 በሕዝባችሁ ላይ ሁከት ይነሳል፤
እናቶች ከልጆቻቸው ጋር በተጨፈጨፉበት* የውጊያ ቀን
ሻልማን፣ ቤትአርቤልን እንዳወደመ ሁሉ፣
የተመሸጉ ከተሞቻችሁ በሙሉ ይወድማሉ።+
15 ቤቴል ሆይ፣ ክፋትሽ ታላቅ ስለሆነ እንዲሁ ይደረግብሻል።+