የዳዊት ማህሌት።
15 ይሖዋ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ በእንግድነት የሚስተናገድ ማን ነው?
በተቀደሰ ተራራህ የሚኖር ማን ነው?+
2 ያለነቀፋ የሚመላለስ፣+
ትክክል የሆነውን የሚያደርግ፣+
በልቡም እውነትን የሚናገር ሰው ነው።+
3 በአንደበቱ ስም አያጠፋም፤+
በባልንጀራው ላይ መጥፎ ነገር አይሠራም፤+
የወዳጆቹንም ስም አያጎድፍም።+
4 ነውረኛ የሆነን ሰው ሁሉ ይንቃል፤+
ይሖዋን የሚፈሩትን ግን ያከብራል።
ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን አያጥፍም።+
5 ገንዘቡን በወለድ አያበድርም፤+
ንጹሕ የሆነውን ሰው ለመወንጀልም ጉቦ አይቀበልም።+
እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ ፈጽሞ አይናወጥም።+