መዝሙር
ምድር ደስ ይበላት።+
ብዙ ደሴቶችም ሐሴት ያድርጉ።+
4 የመብረቅ ብልጭታዎቹ በመሬት ላይ አበሩ፤
ምድር ይህን አይታ ተንቀጠቀጠች።+
5 ተራሮች በይሖዋ ፊት፣
በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።+
6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤
ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ።+
7 ማንኛውንም የተቀረጸ ምስል የሚያመልኩ ሁሉ፣
ከንቱ በሆኑ አማልክታቸው የሚኩራሩ ይፈሩ።+
9 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በመላው ምድር ላይ ልዑል ነህና፤
ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃል።+
10 እናንተ ይሖዋን የምትወዱ፣ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ።+
12 እናንተ ጻድቃን፣ በይሖዋ ሐሴት አድርጉ፤
ለቅዱስ ስሙም* ምስጋና አቅርቡ።