አሞጽ
5 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ እንደ ሙሾ* አድርጌ የምናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦
2 ‘ድንግሊቱ እስራኤል ወድቃለች፤
ዳግመኛም አትነሳም።
በገዛ ምድሯ ተጥላለች፤
የሚያነሳትም የለም።’
3 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
‘አንድ ሺህ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማ መቶ ሰዎች ብቻ ይቀሯታል፤
መቶ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማም አሥር ሰዎች ብቻ ይቀሯታል። ይህ በእስራኤል ቤት ላይ ይደርሳል።’+
4 “ይሖዋ ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦
‘እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+
8 የኪማ ኅብረ ከዋክብትንና* የከሲል ኅብረ ከዋክብትን* የሠራው፣+
ድቅድቅ ጨለማን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጠው፣
ቀኑንም እንደ ሌሊት ጨለማ የሚያደርገው፣+
ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድ
የባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣+
ስሙ ይሖዋ ነው።
9 የተመሸጉትን ቦታዎች በማውደም፣
ብርቱ በሆነው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣል።
10 እነሱ በከተማዋ በር ላይ ሆነው የሚወቅሱትን ይጠላሉ፤
እውነት የሚናገሩትንም ይጸየፋሉ።+
11 ድሃው ለእርሻ ቦታው ኪራይ* እንዲከፍል ስለምታደርጉ፣
እህሉንም በግብር መልክ ስለምትወስዱ፣+
በተጠረበ ድንጋይ በሠራችሁት ቤት ውስጥ አትኖሩም፤+
ደግሞም ከተከላችኋቸው ምርጥ የወይን ተክሎች የሚገኘውን የወይን ጠጅ አትጠጡም።+
12 ዓመፃችሁ* ምን ያህል እንደበዛና
ኃጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደሆነ አውቃለሁና፤
ጻድቁን ትጨቁናላችሁ፤
ጉቦ* ትቀበላላችሁ፤
በከተማዋም በር ላይ የድሆችን መብት ትነፍጋላችሁ።+
13 ስለሆነም ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች በዚያን ጊዜ ዝም ይላሉ፤
የመከራ ጊዜ ይሆናልና።+
የሠራዊት አምላክ ይሖዋም
እንደተናገራችሁት ከእናንተ ጋር ይሆናል።+
የሠራዊት አምላክ ይሖዋ
ከዮሴፍ ለቀሩት ሰዎች ሞገሱን ያሳያቸው ይሆናል።’+
16 “ስለዚህ ይሖዋ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘በየአደባባዩ ዋይታ ይሆናል፤
በየመንገዱም ሰዎች “ወዮ! ወዮ!” ይላሉ።
ገበሬዎችን ለለቅሶ፣
አስለቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ።’
17 ‘በየወይን እርሻውም ዋይታ ይኖራል፤+
እኔ በመካከልህ አልፋለሁና’ ይላል ይሖዋ።
የይሖዋ ቀን ለእናንተ ምን ያመጣ ይሆን?+
ያ ቀን ጨለማ እንጂ ብርሃን አይሆንም።+
19 ይህም ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፣
ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያስደግፍም እባብ እንደሚነድፈው ዓይነት ይሆናል።
20 የይሖዋ ቀን ብርሃን የሌለበት ድቅድቅ ጨለማ ይሆን የለም?
ደግሞስ የብርሃን ጸዳል የሌለበት ጨለማ ይሆን የለም?
22 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የስጦታ መባዎች ብታቀርቡልኝ እንኳ
እነዚህ መባዎች አያስደስቱኝም፤+
ለኅብረት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡ እንስሳትም በሞገስ ዓይን አልመለከትም።+
23 የተደበላለቁ መዝሙሮችህን ከእኔ አርቅ፤
በባለ አውታር መሣሪያዎች የምትጫወተውንም ዜማ መስማት አልፈልግም።+
24 ፍትሕ እንደ ውኃ፣+
ጽድቅም ያለማቋረጥ እንደሚወርድ ጅረት ይፍሰስ።
25 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ በቆያችሁበት ጊዜ
መሥዋዕትና የስጦታ መባ አቅርባችሁልኝ ነበር?+