ምሳሌ
30 የያቄ ልጅ አጉር ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለዑካል የተናገራቸው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘሉ ቃላት።
2 እኔ ከማንም የባሰ አላዋቂ ነኝ፤+
ሰው ሊኖረው የሚገባው ማስተዋልም የለኝም።
3 ጥበብን አልተማርኩም፤
እጅግ ቅዱስ የሆነው አምላክ እውቀትም የለኝም።
4 ወደ ሰማይ የወጣ፣ ከዚያም የወረደ ማን ነው?+
ነፋስን በእፍኙ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው?
ውኃን በልብሱ የጠቀለለ ማን ነው?+
ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው? ታውቅ እንደሆነ ንገረኝ።
5 የአምላክ ቃል ሁሉ የነጠረ ነው።+
እሱ፣ መጠጊያቸው ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው።+
7 ሁለት ነገር እንድታደርግልኝ እለምንሃለሁ።
እነሱንም ከመሞቴ በፊት አትንፈገኝ።
ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ።
ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ* አትፍቀድ።
10 እንዳይረግምህና በደለኛ ሆነህ እንዳትገኝ
በጌታው ፊት የአገልጋዩን ስም አታጥፋ።+
11 አባቱን የሚረግም፣
እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ።+
13 እጅግ ትዕቢተኛ ዓይን ያለው ትውልድ አለ፤
ዓይኖቹም በታላቅ እብሪት ይመለከታሉ!+
15 አልቅቶች “ስጡን! ስጡን!” እያሉ የሚጮኹ ሁለት ሴቶች ልጆች አሏቸው።
ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤
ደግሞም “በቃኝ!” የማያውቁ አራት ነገሮች አሉ።
18 ከመረዳት አቅሜ በላይ የሆኑ* ሦስት ነገሮች አሉ፤
የማልገነዘባቸውም አራት ነገሮች አሉ፦
19 ንስር በሰማያት የሚበርበት መንገድ፣
እባብ በዓለት ላይ የሚሄድበት መንገድ፣
መርከብ በባሕር ላይ የሚጓዝበት መንገድ፣
ሰውም ከሴት ልጅ ጋር የሚሄድበት መንገድ ናቸው።
20 የአመንዝራ ሴት መንገድ ይህ ነው፦
በልታ አፏን ከጠራረገች በኋላ
“ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም” ትላለች።+
21 ምድርን የሚያናውጡ ሦስት ነገሮች አሉ፤
መታገሥ የማትችላቸውም አራት ነገሮች አሉ፦
29 ግርማ የተላበሰ አረማመድ ያላቸው ሦስት ፍጥረታት አሉ፤
አዎ፣ እየተጎማለሉ የሚሄዱ አራት ፍጥረታት አሉ፦