ኢዮብ
4 ንጹሕ ካልሆነ ሰው፣ ንጹሕ የሆነ ሰው መውለድ የሚችል ማን ነው?+
ማንም የለም!
6 እንደ ቅጥር ሠራተኛ ጊዜውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ፣
እረፍት ያገኝ ዘንድ ዓይንህን ከእሱ ላይ መልስ።+
7 ዛፍ እንኳ ተስፋ አለውና።
ቢቆረጥ መልሶ ያቆጠቁጣል፤
ቅርንጫፎቹም ማደጋቸውን ይቀጥላሉ።
10 ሰው ግን ይሞታል፤ አቅም አጥቶም ይጋደማል፤
ሰው ሲሞት የት ይገኛል?+
11 ውኃ ከባሕር ውስጥ ይጠፋል፤
ወንዝም ፈስሶ ይደርቃል።
12 ሰውም ያንቀላፋል፤ ደግሞም አይነሳም።+
ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቁም፤
ከእንቅልፋቸውም አይነሱም።+
14 ሰው ከሞተ በኋላ ዳግመኛ በሕይወት ሊኖር ይችላል?+
እፎይታ የማገኝበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ፣
የግዳጅ አገልግሎት በምፈጽምበት ዘመን ሁሉ በትዕግሥት እጠብቃለሁ።+
የእጅህን ሥራ ትናፍቃለህ።*
16 አሁን ግን እርምጃዬን ሁሉ ትቆጥራለህ፤
ኃጢአቴን ብቻ ትመለከታለህ።
17 መተላለፌ በከረጢት ውስጥ ታሽጓል፤
በደሌንም በሙጫ ታሽጋለህ።
18 ተራራ እንደሚወድቅና ተፈረካክሶ እንደሚጠፋ፣
ቋጥኝም ከስፍራው እንደሚወገድ፣
19 ውኃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣
ጎርፍም የምድርን አፈር አጥቦ እንደሚወስድ፣
አንተም ሟች የሆነውን ሰው ተስፋ አጥፍተሃል።
20 እስኪጠፋ ድረስ በእሱ ላይ ታይልበታለህ፤+
ገጽታውን ለውጠህ ታሰናብተዋለህ።
21 ልጆቹ ክብር ቢያገኙም እሱ ይህን አያውቅም፤
ውርደት ሲደርስባቸውም ልብ አይልም።+
22 ሕመም የሚሰማው በሥጋ ሳለ ብቻ ነው፤
የሚያዝነው* በሕይወት ሳለ ብቻ ነው።”