ኤርምያስ
2 የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2 “ሂድና ኢየሩሳሌም ጆሮዋ እየሰማ ይህን አውጅ፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“በወጣትነትሽ ጊዜ ለአምላክ ያደርሽ እንደነበርሽ፣*+
ደግሞም ለጋብቻ በታጨሽበት ጊዜ ያሳየሽውን ፍቅር፣+
ዘር በማይዘራበት ምድር፣ በምድረ በዳ
እንዴት እንደተከተልሽኝ በሚገባ አስታውሳለሁ።+
3 እስራኤል ለይሖዋ የተቀደሰ፣+ የመከሩ በኩር ነበር።”’
‘እሱን የሚውጥ ሁሉ በደለኛ ይሆናል።
በእነሱም ላይ ጥፋት ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።”+
4 የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ፣
የይሖዋን ቃል ስሙ።
5 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
በምድረ በዳ፣ በረሃማ በሆነና+
ጉድጓድ ባለበት ምድር፣
በድርቅ በተጠቃና+ ድቅድቅ ጨለማ በዋጠው ምድር
እንዲሁም ማንም ሰው በማይጓዝበትና
ሰው በማይኖርበት ምድር
የመራን ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም።
7 በዚያን ጊዜ እኔ ፍሬዋንና በውስጧ ያሉትን ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንድትበሉ
የፍራፍሬ ዛፎች ወዳሉባት ምድር አመጣኋችሁ።+
እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤
ርስቴንም አስጸያፊ ነገር አደረጋችሁት።+
8 ካህናቱ ‘ይሖዋ የት አለ?’ ብለው አልጠየቁም፤+
9 ‘በመሆኑም ከእናንተ ጋር ገና እሟገታለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤
‘ከልጅ ልጆቻችሁም ጋር እሟገታለሁ።’
10 ‘እስቲ ወደ ኪቲም+ የባሕር ዳርቻዎች* ተሻግራችሁ ተመልከቱ።
አዎ፣ መልእክተኞችን ወደ ቄዳር+ ልካችሁ ጉዳዩን በጥሞና መርምሩ፤
እንዲህ ያለ ነገር ተፈጽሞ እንደሆነ እዩ።
11 አማልክቱን፣ አማልክት ባልሆኑት ለውጦ የሚያውቅ ብሔር አለ?
የገዛ ሕዝቤ ግን ክብሬን ምንም ጥቅም በሌለው ነገር ለውጧል።+
14 ‘እስራኤል፣ አገልጋይ ወይም የቤት ውልድ ባሪያ ነው?
ታዲያ እንዲበዘበዝ የተደረገው ለምንድን ነው?
15 ደቦል አንበሶች በእሱ ላይ አገሡ፤+
በኃይለኛ ድምፅ ጮኹበት።
ምድሩን የሚያስፈራ ቦታ አደረጉት።
ከተሞቹ ማንም እንዳይኖርባቸው በእሳት ተቃጠሉ።
16 የኖፍና*+ የጣፍነስ+ ሕዝቦች፣ መሃል አናትሽን ይበላሉ።
19 ከክፋትሽ ትምህርት ልታገኚ ይገባል፤
ታማኝነት በማጉደል የፈጸምሻቸው ድርጊቶችም ወቀሳ ያስከትሉብሻል።
20 ‘ከረጅም ጊዜ በፊት ቀንበርሽን ሰባበርኩ፤+
የታሰርሽበትንም ሰንሰለት በጣጠስኩ።
አንቺ ግን “አንተን አላገለግልም” አልሽ፤
21 እኔ፣ እንደ ምርጥ ቀይ የወይን ተክል፣ ሙሉ በሙሉ ንጹሕ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤+
ታዲያ በፊቴ እንዲህ ተለውጠሽ የተበላሸ ባዕድ የወይን ተክል የሆንሽው እንዴት ነው?’+
23 ‘ራሴን አላረከስኩም።
ባአልንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ?
በሸለቆው ውስጥ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ።
ያደረግሽውን ነገር ልብ በይ።
ስሜቷ ሲነሳሳ ማን ሊመልሳት ይችላል?
የሚፈልጓት ሁሉ እሷን ለማግኘት ብዙ ድካም አይጠይቅባቸውም።
በመራቢያዋ ወቅት* ያገኟታል።
25 እግርሽ እስኪነቃ አትዙሪ፤
ጉሮሮሽም በውኃ ጥም አይቃጠል።
አንቺ ግን ‘አይሆንም! ምንም ተስፋ የሌለው ነገር ነው!+
27 ዛፉን ‘አንተ አባቴ ነህ’፤+
ድንጋዩንም ‘የወለድከኝ አንተ ነህ’ ይላሉ።
ለእኔ ግን ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጥተውኛል።+
ጥፋት ሲመጣባቸውም
‘ተነስተህ አድነን!’ ይላሉ።+
28 ለራስህ የሠራሃቸው አማልክት ታዲያ የት አሉ?+
ጥፋት ሲደርስብህ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ ይነሱ፤
ይሁዳ ሆይ፣ አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋልና።+
29 ‘አሁንም ከእኔ ጋር የምትሟገቱት ለምንድን ነው?
ሁላችሁም በእኔ ላይ ያመፃችሁት ለምንድን ነው?’+ ይላል ይሖዋ።
30 ልጆቻችሁን የመታሁት በከንቱ ነው።+
31 የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ልብ በሉ።
እኔ ለእስራኤል፣ እንደ ምድረ በዳ
ወይም ድቅድቅ ጨለማ እንደዋጠው ምድር ሆኛለሁ?
የእኔ ሕዝብ የሆኑት እነዚህ ሰዎች ‘እኛ ወደፈለግንበት እንሄዳለን።
ከእንግዲህ ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላሉ?+
32 ለመሆኑ አንዲት ድንግል ጌጣጌጧን፣
ሙሽሪትስ ጌጠኛ መቀነቷን* ትረሳለች?
የገዛ ሕዝቤ ግን ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ቀናት ረስቶኛል።+
33 አንቺ ሴት፣ ፍቅረኛ ለማግኘት መንገድሽን ምንኛ በጥበብ አመቻቸሽ!
የክፋትን መንገዶች ተምረሻል።+
35 አንቺ ግን ‘እኔ ንጹሕ ነኝ።
በእርግጥ ቁጣው ከእኔ ተመልሷል’ ትያለሽ።
‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ስለምትዪ፣
በአንቺ ላይ ፍርድ አመጣለሁ።
36 መንገድሽን በመለዋወጥ የምትፈጽሚውን ድርጊት አቅልለሽ የምትመለከቺው ለምንድን ነው?