መዝሙር
ጭቆና የደረሰበት ሰው ተስፋ በቆረጠና* ጭንቀቱን በይሖዋ ፊት ባፈሰሰ ጊዜ ያቀረበው ጸሎት።+
2 የሚያስጨንቅ ሁኔታ ባጋጠመኝ ጊዜ ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+
3 የሕይወት ዘመኔ እንደ ጭስ እየበነነ ነው፤
አጥንቶቼም እንደ ምድጃ ከስለዋል።+
4 እህል መብላት ረስቻለሁና፤
ልቤ እንደ ሣር ጠውልጓል፤ ደርቋልም።+
6 የምድረ በዳ ሻላ* መሰልኩ፤
በፍርስራሽ ክምር መካከል እንዳለች ጉጉት ሆንኩ።
8 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይሳለቁብኛል።+
የሚያፌዙብኝ ሰዎች ስሜን ለእርግማን ይጠቀሙበታል።
9 አመድን እንደ ምግብ እበላለሁና፤+
የምጠጣውም ነገር ከእንባ ጋር ተቀላቅሏል፤+
10 ይህም የሆነው ከቁጣህና ከንዴትህ የተነሳ ነው፤
እኔን ለመጣል ወደ ላይ አንስተኸኛልና።
15 ብሔራት የይሖዋን ስም፣
የምድር ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።+
19 ይሖዋ ከፍ ካለው ቅዱስ ስፍራው ወደ ታች ይመለከታልና፤+
ከሰማይ ሆኖ ወደ ታች ምድርን ያያል፤
20 ይህም የእስረኛውን ሲቃ ለመስማት፣+
ሞት የተፈረደባቸውንም ነፃ ለማውጣት ነው፤+
21 በመሆኑም የይሖዋ ስም በጽዮን፣
ውዳሴውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤+
22 ይህም የሚሆነው ሕዝቦችና መንግሥታት
ይሖዋን ለማገልገል አንድ ላይ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ነው።+
23 ያለጊዜዬ ኃይል አሳጣኝ፤
የሕይወት ዘመኔን አሳጠረ።
26 እነሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤
ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ።
እንደ ልብስ ትቀይራቸዋለህ፤ እነሱም ያልፋሉ።
27 አንተ ግን ያው ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።+
28 የአገልጋዮችህ ልጆች ያለስጋት ይኖራሉ፤
ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”+