የምስጋና ማህሌት።
100 ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለይሖዋ እልል በሉ።+
2 ይሖዋን በደስታ አገልግሉት።+
በእልልታ ወደ ፊቱ ቅረቡ።
3 ይሖዋ፣ አምላክ መሆኑን እወቁ።+
የሠራን እሱ ነው፤ እኛም የእሱ ንብረት ነን።+
እኛ ሕዝቡና የማሰማሪያው በጎች ነን።+
4 በምስጋና ወደ በሮቹ፣
በውዳሴም ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ።+
ምስጋና አቅርቡለት፤ ስሙንም አወድሱ።+
5 ይሖዋ ጥሩ ነውና፤+
ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም፣
ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።+