የዮሐንስ የመጀመሪያው ደብዳቤ
2 የተወደዳችሁ ልጆቼ፣ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ኃጢአት* እንዳትሠሩ ነው። ማንም ኃጢአት ቢሠራ ግን በአብ ዘንድ ረዳት* አለን፤ እሱም ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።+ 2 እሱ ለእኛ ኃጢአት+ የቀረበ የማስተሰረያ* መሥዋዕት ነው፤+ ሆኖም ለእኛ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ ኃጢአት ጭምር ነው።+ 3 ደግሞም ትእዛዛቱን መፈጸማችንን ከቀጠልን እሱን የምናውቅ መሆናችንን በዚህ እንረዳለን። 4 “እሱን አውቀዋለሁ” እያለ ትእዛዛቱን የማይፈጽም ሰው ቢኖር ውሸታም ነው፤ እውነትም በዚህ ሰው ውስጥ የለም። 5 ሆኖም የእሱን ቃል የሚጠብቅ ማንም ቢኖር የአምላክ ፍቅር በእርግጥ በዚህ ሰው ላይ ፍጹም በሆነ መንገድ ይታያል።+ ከእሱ ጋር አንድነት እንዳለንም በዚህ እናውቃለን።+ 6 ከእሱ ጋር ያለኝን አንድነት ጠብቄ እኖራለሁ የሚል፣ እሱ በተመላለሰበት መንገድ የመመላለስ ግዴታ አለበት።+
7 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ የምጽፍላችሁ ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበራችሁን የቆየውን ትእዛዝ እንጂ አዲስ ትእዛዝ አይደለም።+ ይህ የቆየው ትእዛዝ የሰማችሁት ቃል ነው። 8 ይሁንና በእሱም ሆነ በእናንተ ዘንድ እውነት የሆነውን አዲስ ትእዛዝ እጽፍላችኋለሁ፤ ምክንያቱም ጨለማው እያለፈና እውነተኛው ብርሃን አሁንም እንኳ እያበራ ነው።+
9 በብርሃን ውስጥ እንዳለ እየተናገረ ወንድሙን የሚጠላ+ አሁንም በጨለማ ውስጥ ነው።+ 10 ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ውስጥ ይኖራል፤+ በእሱም ዘንድ ምንም የሚያሰናክል ነገር የለም። 11 ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ውስጥ ነው፤ በጨለማም ይመላለሳል፤+ ደግሞም ጨለማው ዓይኑን ስላሳወረው ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።+
12 ልጆቼ ሆይ፣ የምጽፍላችሁ ለእሱ ስም ሲባል ኃጢአታችሁ ይቅር ስለተባለላችሁ ነው።+ 13 አባቶች ሆይ፣ የምጽፍላችሁ ከመጀመሪያ ያለውን እሱን ስላወቃችሁት ነው። እናንተ ወጣት ወንዶች፣ የምጽፍላችሁ ክፉውን ስላሸነፋችሁት ነው።+ ልጆች ሆይ፣ የምጽፍላችሁ አብን ስላወቃችሁት ነው።+ 14 አባቶች ሆይ፣ የምጽፍላችሁ ከመጀመሪያ ያለውን እሱን ስላወቃችሁት ነው። እናንተ ወጣት ወንዶች፣ የምጽፍላችሁ ጠንካሮች ስለሆናችሁ፣+ የአምላክ ቃል በልባችሁ ስለሚኖርና+ ክፉውን ስላሸነፋችሁት ነው።+
15 ዓለምንም ሆነ በዓለም ውስጥ ያሉትን ነገሮች አትውደዱ።+ ማንም ዓለምን የሚወድ ከሆነ የአብ ፍቅር በውስጡ የለም፤+ 16 ምክንያቱም በዓለም ያለው ነገር ሁሉ ይኸውም የሥጋ ምኞት፣+ የዓይን አምሮትና+ ኑሮዬ ይታይልኝ ማለት* ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመነጭ አይደለም። 17 ከዚህም በተጨማሪ ዓለምም ሆነ ምኞቱ ያልፋሉ፤+ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።+
18 ልጆቼ ሆይ፣ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ እንደሰማችሁትም ፀረ ክርስቶስ እየመጣ ነው፤+ አሁንም እንኳ ብዙ ፀረ ክርስቶሶች መጥተዋል፤+ ከዚህም በመነሳት ይህ የመጨረሻው ሰዓት መሆኑን እናውቃለን። 19 በእኛ መካከል ነበሩ፤ ሆኖም ከእኛ ወገን ስላልነበሩ ትተውን ሄደዋል።+ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር። ሆኖም ከእኛ ወገን የሆኑት ሁሉም አለመሆናቸው በግልጽ ይታይ ዘንድ ከእኛ ተለይተው ወጡ።+ 20 እናንተ ግን ቅዱስ ከሆነው ከእሱ የመንፈስ ቅብዓት አግኝታችኋል፤+ ደግሞም ሁላችሁም እውቀት አላችሁ። 21 የምጽፍላችሁ እውነትን+ ስለማታውቁ ሳይሆን እውነትን ስለምታውቁና ከእውነት ምንም ዓይነት ውሸት ስለማይወጣ ነው።+
22 ኢየሱስን፣ ክርስቶስ አይደለም ብሎ ከሚክድ በቀር ውሸታም ማን ነው?+ ይህ አብንና ወልድን የሚክደው ፀረ ክርስቶስ ነው።+ 23 ወልድን የሚክድ ሁሉ በአብ ዘንድም ተቀባይነት የለውም።+ ወልድን አምኖ የሚቀበል ሁሉ+ ግን በአብም ዘንድ ተቀባይነት አለው።+ 24 በእናንተ በኩል ግን ከመጀመሪያ የሰማችሁት በልባችሁ ይኑር።+ ከመጀመሪያ የሰማችሁት በልባችሁ የሚኖር ከሆነ እናንተም ከወልድና ከአብ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ትኖራላችሁ። 25 ከዚህም በተጨማሪ እሱ ራሱ የገባልን የተስፋ ቃል የዘላለም ሕይወት ነው።+
26 እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ሊያሳስቷችሁ ከሚሞክሩት ሰዎች የተነሳ ነው። 27 እናንተ ግን ከእሱ የተቀበላችሁት የመንፈስ ቅብዓት+ በውስጣችሁ ይኖራል፤ በመሆኑም ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ከእሱ ያገኛችሁት ይህ ቅብዓት ስለ ሁሉም ነገር እያስተማራችሁ ነው፤+ ደግሞም እውነት እንጂ ውሸት አይደለም። ይህ ቅብዓት ባስተማራችሁ መሠረት ከእሱ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ።+ 28 እንግዲህ ልጆቼ፣ እሱ በሚገለጥበት ጊዜ የመናገር ነፃነት+ እንዲኖረንና እሱ በሚገኝበት ወቅት ለኀፍረት ተዳርገን ከእሱ እንዳንርቅ ከእሱ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ። 29 እሱ ጻድቅ መሆኑን ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእሱ የተወለደ መሆኑን ታውቃላችሁ።+