ኢሳይያስ
40 “አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ” ይላል አምላካችሁ።+
ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ከይሖዋ እጅ ሙሉ* ዋጋ ተቀብላለች።”+
3 አንድ ሰው በምድረ በዳ እንዲህ ብሎ ይጮኻል፦
4 ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤
ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል።
ወጣ ገባውም መሬት ይስተካከል፤
ጎርበጥባጣውም ምድር ሸለቋማ ሜዳ ይሁን።+
6 አዳምጥ! አንድ ሰው “ጮክ ብለህ ተናገር!” አለ።
ሌላውም “ምን ብዬ ልናገር?” አለ።
“ሥጋ ሁሉ* ለምለም ሣር ነው።
ታማኝ ፍቅሩ ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።+
ሕዝቡ በእርግጥ ለምለም ሣር ነው።
አንቺ ለኢየሩሳሌም ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣
ድምፅሽን በኃይል ከፍ አድርጊ።
ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ አትፍሪ።
ለይሁዳ ከተሞች “እነሆ፣ አምላካችሁ” በማለት አስታውቂ።+
እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤
የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ።+
ግልገሎቹን በክንዱ ይሰበስባል፤
በእቅፉም ይሸከማቸዋል።
ግልገሎቻቸውን የሚያጠቡትን በቀስታ ይመራል።+
14 ማስተዋል ለማግኘት ከማን ጋር ተማከረ?
የፍትሕን መንገድ ያስተማረው
አሊያም እውቀትን ያካፈለው ማን ነው?
ደግሞስ የእውነተኛ ማስተዋልን ጎዳና ያሳየው ማን ነው?+
እነሆ፣ ደሴቶችን እንደ ደቃቅ አፈር ያነሳቸዋል።
18 አምላክን ከማን ጋር ታወዳድሩታላችሁ?+
ከየትኛውስ ምስል ጋር ታነጻጽሩታላችሁ?+
20 አንድ ሰው መዋጮ አድርጎ ለመስጠት
የማይበሰብስ ዛፍ ይመርጣል።+
የማይወድቅ ምስል ቀርጾ እንዲያዘጋጅለት
በእጅ ጥበብ ሥራ የተካነ ባለሙያ ይፈልጋል።+
21 ይህን አታውቁም?
ደግሞስ አልሰማችሁም?
ከመጀመሪያ አንስቶስ አልተነገራችሁም?
የምድር መሠረት ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ማስረጃስ አላስተዋላችሁም?+
እሱ ሰማያትን እንደ ስስ ጨርቅ ይዘረጋል፤
እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይወጥራቸዋል።+
23 ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ያስወግዳል፤
የምድር ፈራጆችንም* እንዳልነበሩ ያደርጋል።
25 “እኩያው እሆን ዘንድ ከማን ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱሱ።
26 “ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንስታችሁ ተመልከቱ።
እነዚህን ነገሮች የፈጠረ ማን ነው?+
እንደ ሠራዊት በቁጥር የሚመራቸው እሱ ነው፤
ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።+
ገደብ ከሌለው ብርቱ ጉልበቱና ከሚያስደምመው ኃይሉ+ የተነሳ
አንዳቸውም አይጎድሉም።
28 ይህን አታውቅም? ደግሞስ አልሰማህም?
የምድር ዳርቻዎች ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነው።+
እሱ ፈጽሞ አይደክምም ወይም አይዝልም።+
እንደ ንስር በክንፍ ወደ ላይ ይወጣሉ።+
ይሮጣሉ፣ አይዝሉም፤
ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።”+