ቤተሰብ የሚወያይበት
ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
መሳፍንት 7:15-22ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት ነገሮች መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።
1. ․․․․․
2. ․․․․․
3. ․․․․․
ለውይይት፦
ጌዴዎንና አብረውት የነበሩት ሰዎች በጦርነቱ ያሸነፉት ለምንድን ነው? ጌዴዎንና አብረውት የነበሩት ሰዎች ደፋር የነበሩት ለምንድን ነው? አንተስ እንደ ጌዴዎን ደፋር መሆን የሚያስፈልግህ መቼ ሊሆን ይችላል?
ስለ ንጉሥ ዳዊት ምን የምታውቀው ነገር አለ?
4. የዳዊት ታላላቅ ወንድሞች ስንት ነበሩ?
ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 16:10, 11ን አንብብ።
․․․․․
5. ከዳዊት ወንድሞች መካከል የሁሉም ታላቅ ማን ይባላል?
ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 17:28ን አንብብ።
․․․․․
ለውይይት፦
የዳዊት ታላቅ ወንድም ዳዊትን የተቆጣው ለምን ይመስልሃል? ወንድሞችህንና እህቶችህን በደግነት ማናገር ያለብህ ለምንድን ነው?
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
ከዚህ እትም
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።
ገጽ 4 ጋብቻ ምን ዓይነት ጥምረት ነው? ማቴዎስ 19:․․․
ገጽ 9 “መከበሪያ” የሚሆነው ምን ማድረግ ነው? ምሳሌ 19:․․․
ገጽ 12 ልብ ምንድን ነው? ኤርምያስ 17:․․․
ገጽ 22 እምነት ምንድን ነው? ዕብራውያን 11:․․․
● መልሱ በገጽ 15 ላይ ይገኛል
በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. ቀንደ መለከቶች።
2. ማሰሮዎች።
3. ችቦዎች።
4. ሰባት።
5. ኤልያብ።