ከፍተኛ ጥራት ያለው ሕክምና የትኛው ነው?
ሜዲካል ዳይሬክተርና አኒስቲዚዮሎጂስት የሆኑት ዶክተር ማይክል ሮዝ “እንደ እውነቱ ከሆነ ደም ሳይወስድ የታከመ ማንኛውም ሕመምተኛ፣ አለ የሚባለው ከፍተኛ ጥራት ያለው ሕክምና ተደርጎለታል” በማለት ተናግረዋል። ‘ያለ ደም የሚሰጠው ሕክምና’ የትኞቹን የአሠራር ሂደቶችና በደም ምትክ የሚሰጡ አማራጭ የሕክምና ዓይነቶች ያጠቃልላል? ከቀዶ ሕክምና ጋር በተያያዘ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ማድረግ እንድትችል ስለእነዚህ ጉዳዮች በደንብ ማወቅ ያስፈልግሃል። በመጀመሪያ ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባለውን ፊልም ተመልከትና ከዚህ በታች በቀረቡት ጥያቄዎች አማካኝነት እውቀትህን ፈትሽ።—ማሳሰቢያ:- ቪዲዮው ቀዶ ሕክምና ሲደረግ የሚያሳዩ ክፍሎች ስላሉት ወላጆች ትናንሽ ልጆች ፊልሙን ሊያዩት ይገባ እንደሆነና እንዳልሆነ አመዛዝነው መወሰን ይኖርባቸዋል።
(1) የይሖዋ ምሥክሮች ደም የማይወስዱበት ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው? (2) በሕክምና ረገድ የይሖዋ ምሥክሮች ፍላጎት ምንድን ነው? (3) ታካሚዎች ምን መሠረታዊ መብት አላቸው? (4) አንድ ሰው በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምናን መምረጡ አስተዋይ እንዲሁም ኃላፊነት የሚሰማው መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው? (5) ከባድ የሆነ የደም መፍሰስ ሲያጋጥም ሐኪሞች ሊያከናውኗቸው የሚገቡ ሁለት ተቀዳሚ ተግባራት የትኞቹ ናቸው? (6) በደም ምትክ የሚሠራባቸውን የሕክምና ዘዴዎች በተመለከተ አራቱ መሠረታዊ ደንቦች ምንድን ናቸው? (7) ዶክተሮች (ሀ) ብዙ ደም እንዳይፈስ (ለ) ቀይ የደም ሴሎች እንዳይባክኑ (ሐ) ሰውነት ደም እንዲያመርት (መ) የፈሰሰው ደም እንዲተካ የሚያደርጉት በምን መንገድ ነው? (8) (ሀ) ሄሞዳይሉሽን (ለ) ሴል ሳልቬጅ የሚባሉት የሕክምና ዓይነቶች አሠራራቸው እንዴት እንደሆነ ግለጽ? (9) ማንኛውንም በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና በሚመለከት ማወቅ ያለባችሁ ነገር ምንድን ነው? (10) ያለ ደም ከባድ የሆኑና የተወሳሰቡ ቀዶ ሕክምናዎችን ማድረግ ይቻላል? (11) በሕክምናው መስክ ምን አበረታች እድገት እየተገኘ ነው?
በፊልሙ ላይ የቀረቡትን አንዳንድ የሕክምና አማራጮች መቀበልም ሆነ አለመቀበል እያንዳንዱ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ በሠለጠነ ሕሊናው ተጠቅሞ የሚያደርገው የግል ውሳኔ ነው። ለእናንተም ሆነ ለልጆቻችሁ የትኛውን በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና እንደምትቀበሉ ወስናችኋል? የይሖዋ ምሥክር ላልሆኑ የቤተሰባችሁ አባላትም ስለ ውሳኔያችሁና ለምን እንደዚህ ዓይነት ውሳኔ እንዳደረጋችሁ በዝርዝር ልትነግሯቸው ይገባል።—በሰኔ 15, 2004 እና በጥቅምት 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ የወጡትን “የአንባቢያን ጥያቄዎች” ተመልከት።