ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባለውን ፊልም ማየት አለብህ
ያለ ደም በሚሰጥ ሕክምና መስክ ስላሉት አማራጮች ምን ያህል ግንዛቤ አለህ? ያለ ደም ሕክምና ማድረግ የሚቻልባቸውን ዘዴዎችና እነዚህም ዘዴዎች እንዴት እንደሚሠሩ ምን ያህል ታውቃለህ? ይህን የቪዲዮ ፊልም ተመልከትና በሚከተሉት ጥያቄዎች አማካኝነት እውቀትህን ፈትሽ።—ማሳሰቢያ:- ቪዲዮው ቀዶ ሕክምና ሲደረግ የሚያሳዩ ክፍሎች ስላሉት ወላጆች ከትናንሽ ልጆች ጋር ሆነው ቪዲዮውን በሚያዩበት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።
(1) የይሖዋ ምሥክሮች ደም የማይወስዱበት ዋነኛ ምክንያት ምንድን ነው? ይህ መሠረታዊ መመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የት ቦታ ላይ ይገኛል? (2) በሕክምና ረገድ ፍላጎታችን ምንድን ነው? (3) ታካሚዎች ምን መሠረታዊ መብት አላቸው? (4) አንድ ሰው ደም አልወስድም ማለቱ አስተዋይ አይደለም ወይም ኃላፊነት አይሰማውም ሊያሰኘው የማይችለው ለምንድን ነው? (5) ከባድ የሆነ የደም መፍሰስ ሲያጋጥም ሐኪሞች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ሁለት ቀዳሚ ተግባራት የትኞቹ ናቸው? (6) ደም መውሰድ ሊያስከትላቸው የሚችሉ አንዳንድ የጤና ችግሮች ምንድን ናቸው? (7) ሐኪሞች በቀዶ ሕክምና ወቅት ብዙ ደም እንዳይፈስ ለማድረግ እንዴት ባሉ ዘዴዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ? (8) ማንኛውንም በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና በሚመለከት ሕመምተኞች ማወቅ ያለባቸው ነገር ምንድን ነው? (9) ደም ሳይሰጥ ከባድ የሆኑና የተወሳሰቡ ቀዶ ሕክምናዎችን ማድረግ ይቻላል? (10) ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ የሕክምና ባለሞያዎች ለይሖዋ ምሥክሮች ምን ለማድረግ ፈቃደኛ ሆነዋል? ውሎ አድሮ ለሁሉም ታካሚዎች ተግባራዊ መሆኑ የማይቀረው የሕክምና ዘዴ የትኛው ነው?
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፣ የይሖዋ ምሥክር ካልሆኑ የትዳር ጓደኞች ወይም ከዘመዶች፣ ከሥራ ባልደረባዎች፣ ከመምህራን እና ከትምህርት ቤት ጓደኞች ጋር ሆኖ ይህን ቪዲዮ መመልከቱ ጠቃሚ እንደሆነ አያጠራጥርም። በቪዲዮው ላይ የቀረበውን ማንኛውንም ዓይነት የሕክምና አማራጭ ለመቀበል የሚደረገው ምርጫ ለእያንዳንዱ ግለሰብ የተተወ ሲሆን ጉዳዩን ከሕሊና ጋር በጥንቃቄ ካገናዘቡ በኋላ የሚደረግ ውሳኔ ነው።—በሰኔ 15 እና ጥቅምት 15, 2000 መጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ የወጡትን “የአንባብያን ጥያቄዎች” ተመልከት።