ኢዮብ
34 ኤሊሁም መልስ መስጠቱን በመቀጠል እንዲህ አለ፦
2 “እናንተ ጥበበኞች፣ ቃሌን አዳምጡ፤
እናንተ ብዙ እውቀት ያላችሁ ስሙኝ።
3 ምላስ* የምግብን ጣዕም እንደሚለይ ሁሉ፣
ጆሮም ቃላትን ያመዛዝናል።
4 ትክክለኛ የሆነውን ነገር እናመዛዝን፤
መልካም የሆነውን ነገር በመካከላችን እንወስን።
6 ሊበየንብኝ የሚገባውን ፍርድ በተመለከተ እዋሻለሁ?
በደል ባልሠራም እንኳ በላዬ ላይ ያለው ቁስል የማይሽር ነው።’+
7 ፌዝን እንደ ውኃ የሚጠጣ፣
እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?
8 ክፉ ድርጊት ከሚፈጽሙ ጋር ተወዳጅቷል፤
ከክፉዎችም ጋር ገጥሟል።+
9 ኢዮብ ‘ሰው አምላክን ለማስደሰት መሞከሩ
ምንም ፋይዳ የለውም’ ብሏልና።+
10 ስለዚህ እናንተ አስተዋዮች* ስሙኝ፦
‘እውነተኛው አምላክ ክፉ ነገር ያደርጋል፤
ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በደል ይፈጽማል’ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው!+
11 ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋልና፤+
መንገዱም ያስከተለበትን መዘዝ እንዲቀበል ያደርገዋል።
13 ምድርን እንዲገዛ ያደረገው ማን ነው?
በመላው ዓለም* ላይ የሾመውስ ማን ነው?
14 እሱ ትኩረቱን* በእነሱ ላይ ቢያደርግ፣
መንፈሳቸውንና እስትንፋሳቸውን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፣+
15 ሰዎች* ሁሉ በአንድነት በጠፉ፣
የሰውም ዘር ወደ አፈር በተመለሰ ነበር።+
16 ስለዚህ ማስተዋል ካለህ ለዚህ ነገር ትኩረት ስጥ፤
የምናገረውንም በጥሞና አዳምጥ።
17 ፍትሕን የሚጠላ ሰው፣ ገዢ ሊሆን ይገባል?
ወይስ ጻድቅ የሆነውን ኃያል ሰው ትኮንነዋለህ?
18 ንጉሥን ‘የማትረባ ነህ፣’
ታላላቅ የሆኑ ሰዎችንስ ‘ክፉዎች ናችሁ’ ትላለህ?+
20 እነሱ በእኩለ ሌሊት ድንገት ሊሞቱ ይችላሉ፤+
በኃይል ተንቀጥቅጠው ሕይወታቸው ያልፋል፤
ኃያላን የሆኑትም እንኳ ይወገዳሉ፤ ይሁንና ይህ የሚሆነው በሰው እጅ አይደለም።+
21 የአምላክ ዓይኖች የሰውን መንገድ ይመለከታሉና፤+
ደግሞም እርምጃውን ሁሉ ያያል።
23 አምላክ፣ ማንኛውም ሰው በፊቱ ለፍርድ እንዲቀርብ፣
የተወሰነ ጊዜ አልቀጠረምና።
24 ምርመራ ማድረግ ሳያስፈልገው ኃያላንን ይሰባብራል፤
በእነሱም ቦታ ሌሎችን ይተካል።+
26 በክፋታቸው የተነሳ፣
ሁሉም ማየት በሚችልበት ቦታ ይመታቸዋል፤+
27 ምክንያቱም እሱን ከመከተል ወደኋላ ብለዋል፤+
መንገዶቹንም ሁሉ ችላ ብለዋል፤+
28 ድሃው ወደ እሱ እንዲጮኽ ያደርጋሉ፤
እሱም የምስኪኖችን ጩኸት ይሰማል።+
29 አምላክ ዝም ሲል ማን ሊወቅሰው ይችላል?
ፊቱን በሚሰውርበት ጊዜ ማን ሊያየው ይችላል?
ይህን ያደረገው በአንድ ብሔር ላይም ሆነ በአንድ ሰው ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም፤
30 ይህም አምላክ የለሽ የሆነ* ሰው እንዳይገዛ፣+
ወይም በሕዝቡ ላይ ወጥመድ እንዳይዘረጋ ነው።
31 አምላክን እንዲህ የሚል ሰው ይኖራል?
‘የሠራሁት ጥፋት ባይኖርም ተቀጥቻለሁ፤+
32 ማየት የተሳነኝን ነገር አስተምረኝ፤
የሠራሁት ጥፋት ካለ ዳግመኛ አልሠራም።’
33 ፍርዱን አልቀበልም ስትል አንተ በምትፈልገው መንገድ ሊክስህ ይገባል?
መወሰን ያለብህ አንተ እንጂ እኔ አይደለሁም።
ስለዚህ አንተ በደንብ የምታውቀውን ነገር ንገረኝ።
36 ኢዮብ እስከ መጨረሻው ድረስ ይፈተን!*
እንደ ክፉ ሰዎች መልስ ሰጥቷልና።