ሶፎንያስ
1 በይሁዳ ንጉሥ በአምዖን+ ልጅ በኢዮስያስ+ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያህ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኩሺ ልጅ፣ ወደ ሶፎንያስ* የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦
2 “ማንኛውንም ነገር ሙሉ በሙሉ ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ” ይላል ይሖዋ።+
3 “ሰውንና እንስሳን ጠራርጌ አጠፋለሁ።
4 “በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይ
እጄን እዘረጋለሁ፤
የባአልን ቀሪዎች* ሁሉና የባዕድ አምላክ ካህናትን ስም
ከሌሎቹ ካህናት ጋር ከዚህ ስፍራ ፈጽሜ አስወግዳለሁ፤+
5 በቤት ጣሪያዎች ላይ ሆነው ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትን+
እንዲሁም በአንድ በኩል ለይሖዋ እየሰገዱና ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል እየገቡ+
በሌላ በኩል ግን ለማልካም ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል የሚገቡትን አጠፋለሁ፤+
6 ደግሞም ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ የሚሉትን፣+
ይሖዋን የማይፈልጉትን ወይም እሱን የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።”+
7 በሉዓላዊው ጌታ በይሖዋ ፊት ዝም በሉ፤ የይሖዋ ቀን ቀርቧልና።+
ይሖዋ መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውን ቀድሷል።
12 በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤
ደግሞም ቸልተኛ የሆኑትንና*
በልባቸው ‘ይሖዋ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።+
13 ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይወድማሉ።+
ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሆኖም አይኖሩባቸውም፤
ወይንም ይተክላሉ፤ ሆኖም የወይን ጠጁን አይጠጡም።+
ቅርብ ነው፤ ደግሞም በፍጥነት እየቀረበ ነው!*+
በዚያ ተዋጊው ይጮኻል።+
የጭንቀትና የሥቃይ ቀን፣+
የአውሎ ነፋስና የጥፋት ቀን፣
የጨለማና የጭጋግ ቀን፣+
የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤+
16 በተመሸጉ ከተሞችና በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ባሉ ረጃጅም ማማዎች ላይ+
የቀንደ መለከትና የጦርነት ሁካታ ድምፅ የሚሰማበት ቀን ይሆናል።+
ደማቸው እንደ አቧራ፣
አንጀታቸውም እንደ ፋንድያ ይፈስሳል።+