ኢሳይያስ
“እኔ ተቤዥቼሃለሁና+ አትፍራ።
በስምህ ጠርቼሃለሁ።
አንተ የእኔ ነህ።
በእሳት መካከል ስትሄድ አትቃጠልም፤
ነበልባሉም አይፈጅህም።
3 እኔ ይሖዋ አምላክህ፣
የእስራኤል ቅዱስ፣ አዳኝህ ነኝና።
ግብፅን ለአንተ ቤዛ አድርጌ ሰጥቻለሁ፤
ኢትዮጵያንና ሴባን በአንተ ምትክ ሰጥቻለሁ።
ስለዚህ በአንተ ምትክ ሰዎችን፣
በሕይወትህም* ምትክ ብሔራትን እሰጣለሁ።
ዘርህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤
ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።+
ደቡብንም እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘አታግታቸው።
ከመካከላቸው ይህን ሊናገር የሚችል ማን አለ?
ወይስ የመጀመሪያዎቹን ነገሮች ሊነግሩን ይችላሉ?*+
ትክክል መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ምሥክሮቻቸውን ያቅርቡ፤
ወይም ሰምተው ‘ይህ እውነት ነው!’ ይበሉ።”+
ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤
ከእኔም በኋላ የለም።+
11 እኔ፣ አዎ እኔ ይሖዋ ነኝ፤+ ከእኔ በቀር አዳኝ የለም።”+
ስለዚህ እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” ይላል ይሖዋ፤ “እኔም አምላክ ነኝ።+
እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ሊያግድ የሚችል ማን ነው?”+
14 እናንተን የሚቤዠው+ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ+ እንዲህ ይላል፦
15 እኔ ይሖዋ የእናንተ ቅዱስ፣+ የእስራኤል ፈጣሪ፣+ ንጉሣችሁ ነኝ።”+
16 ይሖዋ ይኸውም
በባሕር መካከል መንገድ የሚያበጀው፣
በሚናወጡ ውኃዎችም መካከል ጎዳና የሚዘረጋው፣+
ሠራዊቱንና ኃያላን ተዋጊዎቹን በአንድነት የሚያወጣው አምላክ እንዲህ ይላል፦
“ይተኛሉ፤ አይነሱምም።+
እንደሚነድ የጧፍ ክር ተዳፍነው ይጠፋሉ።”
18 “የቀድሞዎቹን ነገሮች አታስታውሱ፤
ያለፈውንም ነገር አታውጠንጥኑ።
ይህን አታስተውሉም?
20 የዱር አውሬ፣ ቀበሮዎችና
ሰጎኖች ያከብሩኛል፤
በምድረ በዳ ውኃ፣
በበረሃም ወንዞችን እሰጣለሁና፤+
ይህን የማደርገው የመረጥኩት ሕዝቤ+ እንዲጠጣ፣
21 ለራሴ የሠራሁትም ሕዝብ እንዲጎነጭ ነው፤
ሕዝቤ ውዳሴዬን እንዲያውጅ ይህን አደርጋለሁ።+
23 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ በግ አላመጣህልኝም፤
ወይም መሥዋዕቶች በማቅረብ አላከበርከኝም።
ስጦታ እንድታመጣልኝ አላስገደድኩህም፤
ነጭ ዕጣን አቅርብልኝ ብዬም አላሰለቸሁህም።+
ከዚህ ይልቅ ኃጢአትህን አሸክመኸኛል፤
በምትፈጽማቸውም በደሎች አሰልችተኸኛል።+
26 እስቲ አስታውሰኝ፤ ጉዳያችንን አቅርበን እንሟገት፤
ትክክለኛ መሆንህን ለማረጋገጥ በበኩልህ ጉዳይህን ተናገር።