15 የለዘበ መልስ ቁጣን ያበርዳል፤+
ክፉ ቃል ግን ቁጣን ያነሳሳል።+
2 የጥበበኞች ምላስ እውቀትን በሚገባ ይጠቀማል፤+
የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይገልጣል።
3 የይሖዋ ዓይኖች በሁሉም ቦታ ናቸው፤
ክፉዎችንም ሆነ ጥሩ ሰዎችን ይመለከታሉ።+
4 የረጋ አንደበት የሕይወት ዛፍ ነው፤+
ጠማማ ንግግር ግን ተስፋ ያስቆርጣል።
5 ሞኝ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፤+
ብልህ ግን እርማትን ይቀበላል።+
6 በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ሀብት አለ፤
የክፉ ሰው ምርት ግን ችግር ያስከትልበታል።+
7 የጥበበኞች ከንፈር እውቀትን ታስፋፋለች፤+
የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።+
8 ይሖዋ የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤+
የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል።+
9 ይሖዋ የክፉውን መንገድ ይጸየፋል፤+
ጽድቅን የሚከታተለውን ግን ይወደዋል።+
10 ከመንገድ የሚወጣ ሰው፣ ተግሣጽ መጥፎ ነገር ይመስለዋል፤+
ወቀሳን የሚጠላ ሁሉ ግን ይሞታል።+
11 መቃብርና የጥፋት ቦታ በይሖዋ ፊት ወለል ብለው ይታያሉ።+
የሰዎች ልብማ በፊቱ ምንኛ የተገለጠ ነው!+
12 ፌዘኛ የሚያርመውን ሰው አይወድም።+
ጥበበኞችን አያማክርም።+
13 ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፤
የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይደቁሳል።+
14 አስተዋይ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፤+
የሞኞች አፍ ግን ቂልነትን ይመገባል።+
15 ጎስቋላ ሰው ዘመኑ ሁሉ አስከፊ ነው፤+
ደስተኛ ልብ ያለው ሰው ግን ሁልጊዜ ግብዣ ላይ ያለ ያህል ነው።+
16 ከጭንቀት ጋር ከሚገኝ ብዙ ሀብት ይልቅ
ይሖዋን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።+
17 ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይልቅ
ፍቅር ባለበት አትክልት መብላት ይሻላል።+
18 ግልፍተኛ ሰው ጭቅጭቅ ይፈጥራል፤+
ቶሎ የማይቆጣ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።+
19 የሰነፍ መንገድ እንደ እሾህ አጥር ነው፤+
የቅኖች መንገድ ግን እንደተስተካከለ አውራ ጎዳና ነው።+
20 ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤+
ሞኝ ግን እናቱን ያቃልላል።+
21 ማስተዋል የጎደለው ሰው ሞኝነት ያስደስተዋል፤+
ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ቀጥተኛውን መንገድ ተከትሎ ይሄዳል።+
22 መመካከር ከሌለ የታቀደው ነገር ሳይሳካ ይቀራል፤
በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል።+
23 ሰው ትክክለኛውን መልስ በመስጠት ሐሴት ያደርጋል፤+
በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃልም ምንኛ መልካም ነው!+
24 ጥልቅ ማስተዋል ያለው ሰው ወደ መቃብር ከመውረድ ይድን ዘንድ
የሕይወት መንገድ ወደ ላይ ይመራዋል።+
25 ይሖዋ የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤+
የመበለቲቱን ወሰን ግን ያስከብራል።+
26 ይሖዋ የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤+
ያማረ ቃል ግን በፊቱ ንጹሕ ነው።+
27 በማጭበርበር የተገኘ ትርፍ የሚያጋብስ ሰው በቤተሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤+
ጉቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።+
28 የጻድቅ ልብ፣ መልስ ከመስጠቱ በፊት ያሰላስላል፤+
የክፉዎች አፍ ግን መጥፎ ነገር ይዘከዝካል።
29 ይሖዋ ከክፉዎች እጅግ የራቀ ነው፤
የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።+
30 ብሩህ ዓይን ልብን ደስ ያሰኛል፤
መልካም ዜናም አጥንትን ያበረታል።+
31 ሕይወት የሚያስገኝ ወቀሳን የሚሰማ፣
በጥበበኛ ሰዎች መካከል ይኖራል።+
32 ተግሣጽን ገሸሽ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ሕይወቱን ያቃልላል፤+
ወቀሳን የሚሰማ ሁሉ ግን ማስተዋል ያገኛል።+
33 ይሖዋን መፍራት ጥበብን ያስተምራል፤+
ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።+