ኢሳይያስ
“በጽድቅ የምናገር፣
ለማዳን የሚያስችል ታላቅ ኃይል ያለኝ እኔ ነኝ።”
2 መጎናጸፊያህ የቀላውና
ልብሶችህ በመጭመቂያ ውስጥ ወይን እንደሚረግጥ ሰው ልብስ የሆኑት ለምንድን ነው?+
3 “በወይን መጭመቂያው ውስጥ ወይኑን ብቻዬን ረገጥኩ።
ከሕዝቦች መካከል ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም።
በቁጣዬም ረጋገጥኳቸው፤
በታላቅ ቁጣዬም ጨፈላለቅኳቸው።+
ደማቸውም ልብሶቼ ላይ ተረጨ፤
ልብሴንም ሁሉ በከልኩ።
5 ተመለከትኩ፤ ሆኖም እርዳታ የሚሰጥ አልነበረም፤
ማንም ድጋፍ ባለመስጠቱ ደነገጥኩ።
7 ይሖዋ በምሕረቱና ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅሩ
ለእኛ ባደረገልን ነገሮች ሁሉ+
ይኸውም ለእስራኤል ቤት ባደረጋቸው በርካታ መልካም ነገሮች የተነሳ
የይሖዋን የታማኝ ፍቅር መግለጫዎች፣
ደግሞም ሊወደሱ የሚገባቸውን የይሖዋን ሥራዎች እናገራለሁ።
8 እሱ እንዲህ ብሏልና፦ “እነሱ በእርግጥ ሕዝቤ፣ የማይከዱ* ወንዶች ልጆች ናቸው።”+
ስለዚህ አዳኝ ሆነላቸው።+
10 እነሱ ግን ዓመፁ፤+ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ።+
11 እነሱም የጥንቱን ዘመን፣
አገልጋዩ ሙሴ የኖረበትን ጊዜ አስታወሱ፦
“ከመንጋው እረኞች+ ጋር ከባሕሩ ያወጣቸው የት አለ?+
በእሱ ውስጥ ቅዱስ መንፈሱን ያኖረው፣+
12 የከበረ ክንዱ ከሙሴ ቀኝ እጅ ጋር እንዲሄድ ያደረገው፣+
ለራሱ ዘላለማዊ ስም ለማትረፍ+
ውኃዎቹን በፊታቸው የከፈለው፣+
13 አውላላ ሜዳ* ላይ እንዳለ ፈረስ፣
በሚናወጡ ውኃዎች* መካከል
ሳይደናቀፉ እንዲሄዱ ያደረገው የት አለ?
እነዚህን ነገሮች ነፍገኸኛል።
ስምህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ “እኛን የተቤዠ” የሚል ነው።+
17 ይሖዋ ሆይ፣ ከመንገዶችህ ወጥተን እንድንቅበዘበዝ የፈቀድከው* ለምንድን ነው?
አንተን እንዳንፈራ ልባችን እንዲደነድን የፈቀድከው* ለምንድን ነው?+
ስለ አገልጋዮችህ፣
ርስትህ ስለሆኑትም ነገዶች ስትል ተመለስ።+
18 ቅዱስ ሕዝብህ ለጥቂት ጊዜ ወርሶት ነበር።
ጠላቶቻችን መቅደስህን ረግጠዋል።+
19 እኛ ለረጅም ጊዜ፣ ፈጽሞ እንዳልገዛኻቸው፣
ጨርሶ በስምህ እንዳልተጠሩ ሰዎች ሆነናል።