ኢሳይያስ
ስሜን ላልጠራ ብሔር ‘እነሆኝ፤ እነሆኝ!’ አልኩ።+
መልካም ባልሆነ መንገድ ወደሚሄዱ+
ግትር ሰዎች ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ፤+
3 እነሱ ዘወትር በፊቴ እኔን የሚያስከፋ ነገር ይፈጽማሉ፤+
በአትክልት ቦታዎች ይሠዋሉ፤+ በጡቦችም ላይ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ።
እነዚህ ሰዎች በአፍንጫዬ እንዳለ ጭስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድ እሳት ናቸው።
6 እነሆ፣ በፊቴ ተጽፏል፤
እኔ ዝም አልልም፤
ከዚህ ይልቅ እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ፤+
ብድራቱን ሙሉ በሙሉ እመልስባቸዋለሁ፤*
7 ይህን የማደርገው እነሱ በሠሩት በደልና አባቶቻቸው በሠሩት በደል የተነሳ ነው”+ ይላል ይሖዋ።
8 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“አዲስ ወይን፣ በወይን ዘለላ ውስጥ ሲገኝ
አንድ ሰው ‘በውስጡ ጥሩ ነገር* ስላለ አታጥፋው’ እንደሚል፣
እኔም ለአገልጋዮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤
ሁሉንም አላጠፋቸውም።+
12 በመሆኑም ዕጣችሁ በሰይፍ መውደቅ ይሆናል፤+
ሁላችሁም ለመታረድ ታጎነብሳላችሁ፤+
ምክንያቱም ስጣራ አልመለሳችሁም፤
ስናገር አልሰማችሁም፤+
በዓይኔ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ማድረጋችሁን ቀጠላችሁ፤
እኔ የማልደሰትበትንም ነገር መረጣችሁ።”+
13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፣ አገልጋዮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ።+
እነሆ፣ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ፤+ እናንተ ግን ትጠማላችሁ።
እነሆ፣ አገልጋዮቼ ሐሴት ያደርጋሉ፤+ እናንተ ግን ኀፍረት ትከናነባላችሁ።+
15 የተመረጡት አገልጋዮቼ ለእርግማን የሚጠቀሙበት ስም ትታችሁ ታልፋላችሁ፤
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋም እያንዳንዳችሁን ይገድላችኋል፤
የራሱን አገልጋዮች ግን በሌላ ስም ይጠራቸዋል፤+
16 ስለዚህ በምድር ላይ በረከትን የሚሻ ሁሉ
በእውነት አምላክ* ይባረካል፤
በምድር ላይ መሐላ የሚምልም ሁሉ
18 በመሆኑም በምፈጥረው ነገር ለዘላለም ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ።
እነሆ፣ ኢየሩሳሌምን ለደስታ፣
ሕዝቧንም ለሐሴት እፈጥራለሁና።+
20 “ከእንግዲህ በዚያ፣ ለጥቂት ቀን ብቻ የሚኖር ሕፃንም ሆነ
ዕድሜ የማይጠግብ አረጋዊ አይኖርም።
መቶ ዓመት ሞልቶት የሚሞት ማንኛውም ሰው ገና በልጅነቱ እንደተቀጨ ይቆጠራል፤
ኃጢአተኛው መቶ ዓመት ቢሞላውም እንኳ ይረገማል።*
22 እነሱ በሠሩት ቤት ሌላ ሰው አይኖርም፤
እነሱ የተከሉትንም ሌላ ሰው አይበላውም።
የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፤+
የመረጥኳቸው አገልጋዮቼም በእጃቸው ሥራ የተሟላ እርካታ ያገኛሉ።
24 ገና ሳይጣሩ እመልስላቸዋለሁ፤
እየተናገሩ ሳሉ እሰማቸዋለሁ።
በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳትም ሆነ ጥፋት አያደርሱም”+ ይላል ይሖዋ።