ሶፎንያስ
ጽድቅን ፈልጉ፤ የዋህነትን* ፈልጉ።
ምናልባት በይሖዋ የቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።+
4 ጋዛ የተተወች ከተማ ትሆናለችና፤
አስቀሎንም ባድማ ትሆናለች።+
5 “በባሕሩ ዳርቻ ለሚኖረው ሕዝብ ይኸውም ለከሪታውያን ብሔር ወዮለት!+
የይሖዋ ቃል በአንተ ላይ ነው።
የፍልስጤማውያን ምድር የሆንሽው ከነአን ሆይ፣ አጠፋሻለሁ፤
አንድም ነዋሪ አይተርፍም።
6 የባሕሩ ዳርቻም መሰማሪያ ይሆናል፤
ለእረኞች የውኃ ጉድጓድና ለበጎች ከድንጋይ የተሠራ ጉረኖ ይኖረዋል።
7 ከይሁዳ ቤት ለቀሩት ሰዎች መኖሪያ ስፍራ ይሆናል፤+
በዚያም የግጦሽ ቦታ ያገኛሉ።
በምሽት በአስቀሎን ቤቶች ውስጥ ይተኛሉ።
9 ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣
“ሞዓብ እንደ ሰዶም፣+
አሞናውያንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤+
ሳማ የወረሰው ምድርና የጨው ጉድጓድ ይሆናሉ፤ ለዘለቄታውም ባድማ ሆነው ይቀራሉ።+
የሕዝቤ ቀሪዎች ይዘርፏቸዋል፤
ከገዛ ብሔሬ የቀሩት ሰዎችም ይወርሷቸዋል።
10 ከኩራታቸው የተነሳ ይህ ይደርስባቸዋል፤+
ምክንያቱም በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ሕዝብ ላይ ተሳልቀዋል፤ ራሳቸውንም ከፍ ከፍ አድርገዋል።
12 እናንተም ኢትዮጵያውያን በሰይፌ ትገደላላችሁ።+
14 መንጎች ይኸውም ሁሉም ዓይነት የዱር እንስሳት* በውስጧ ይተኛሉ።
ሻላ* እና ጃርት በፈራረሱት ዓምዶቿ መካከል ያድራሉ።
የዝማሬ ድምፅ በመስኮት ይሰማል።
ደጃፍ ላይ ፍርስራሽ ይኖራል፤
የአርዘ ሊባኖስ እንጨቶቹ እንዲጋለጡ ያደርጋልና።
15 በልቧ ‘እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም’ ስትል የነበረችው
ያለስጋት የተቀመጠችው ኩሩዋ ከተማ ይህች ናት።
ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች!
የዱር እንስሳት የሚተኙባት ስፍራ ሆናለች።
በእሷ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ያፏጫል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።”+