53 ከእኛ የሰማውን ነገር ያመነ ማን ነው?+
የይሖዋስ ክንድ+ ለማን ተገለጠ?+
2 እሱ በፊቱ እንደ ቅርንጫፍ፣+ በደረቅ ምድር እንዳለ ሥር ይበቅላል።
የሚያምር ቁመናም ሆነ ግርማ ሞገስ የለውም፤+
ባየነውም ጊዜ መልኩ አልሳበንም።
3 ሰዎች የናቁትና ያገለሉት፣+
ሥቃይን ያየ፣ ሕመምንም የሚያውቅ ሰው ነበር።
ፊቱ የተሰወረብን ያህል ነበር።
ሰዎች ናቁት፤ እኛም ከቁብ አልቆጠርነውም።+
4 በእርግጥም እሱ ራሱ ሕመማችንን ተሸከመ፤+
ሥቃያችንንም ተቀበለ።+
እኛ ግን እንደተቀሰፈ፣ በአምላክ እንደተመታና እንደተጎሳቆለ አድርገን ቆጠርነው።
5 እሱ ግን ስለ መተላለፋችን+ ተወጋ፤+
ስለ በደላችን ደቀቀ።+
በእሱ ላይ የደረሰው ቅጣት ለእኛ ሰላም አስገኘልን፤+
በእሱም ቁስል የተነሳ እኛ ተፈወስን።+
6 ሁላችንም እንደ በጎች ተቅበዘበዝን፤+
እያንዳንዳችን በየራሳችን መንገድ ሄድን፤
ይሖዋም የሁላችንንም በደል እሱ እንዲሸከም አደረገ።+
7 ግፍ ተፈጸመበት፤+ መከራም ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነ፤+
ነገር ግን አፉን አልከፈተም።
እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤+
በሸላቾቿ ፊት ዝም እንደምትል በግ፣
እሱም አፉን አልከፈተም።+
8 ፍትሕ ተነፈገ፤ በአግባቡም ሳይዳኝ ተወሰደ፤
ትኩረት ሰጥቶ ትውልዱን በዝርዝር ለማወቅ የሚሞክር ማን ነው?
ከሕያዋን ምድር ተወግዷልና፤+
በሕዝቤ መተላለፍ የተነሳ ተመታ።+
9 ምንም ዓይነት በደል አልፈጸመም፤
እንዲሁም ከአንደበቱ የማታለያ ቃል አልወጣም፤+
ሆኖም በሚሞትበት ጊዜ የመቃብር ቦታው
ከክፉዎችና+ ከሀብታሞች+ ጋር ይሆናል።
10 ይሁንና እሱን ማድቀቅ የይሖዋ ፈቃድ ነበር፤ ለሕመም እንዲዳረግም ፈቅዷል።
ሕይወቱን የበደል መባ አድርገህ የምታቀርበው ከሆነ+
ዘሩን ያያል፤ ዘመኑን ያስረዝማል፤+
እንዲሁም በእሱ አማካኝነት ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት ነገር ይከናወናል።+
11 በእሱ ላይ ከደረሰው ሥቃይ የተነሳ፣ በሚያየው መልካም ነገር ይደሰታል።
ጻድቅ አገልጋዬ+ በእውቀቱ አማካኝነት
ብዙ ሰዎች ጻድቅ ሆነው እንዲቆጠሩ ይረዳል፤+
በደላቸውንም ይሸከማል።+
12 ስለዚህ ከብዙዎች ጋር ድርሻውን እሰጠዋለሁ፤
ምርኮውን ከኃያላን ጋር ይካፈላል፤
ሕይወቱን እስከ ሞት ድረስ አፍስሷልና፤+
ከሕግ ተላላፊዎችም ጋር ተቆጥሯል፤+
የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸክሟል፤+
ስለ ሕግ ተላላፊዎችም ማልዷል።+