“ነቅታችሁ ኑሩ”
1 ኢየሱስ የዚህን የነገሮች ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች ልዩ የሚያደርጓቸውን ታላላቅ ክንውኖች ከገለጸ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “ነቅታችሁ ኑሩ” በማለት አጥብቆ አሳስቧቸዋል። (ማር. 13:33 NW ) ይሁን እንጂ ክርስቲያኖች ንቁ መሆን ያለባቸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም የምንኖረው በሰው ልጆች ታሪክ በጣም አደገኛ በሆነው ወቅት ላይ ነው። በመንፈሳዊ ድብታ እንዲይዘን መፍቀድ የለብንም። መንፈሳዊ ድብታ ከያዘን ግን ይሖዋ በዚህ በመጨረሻ ዘመን እንድንሠራው ለሰጠን ሥራ አድናቆት ልናጣ እንችላለን። ይህ እንድንሠራው የተሰጠን ሥራ ምንድን ነው?
2 ይሖዋ የሰው ልጅ ብቸኛ ተስፋ ስለሆነው መንግሥቱ የሚናገረውን ምሥራች በመላው ምድር ላይ ለማወጅ በሕዝቡ እየተጠቀመ ነው። ከአምላክ ድርጅት ጋር ተቀራርበን መሥራታችን የጊዜውን ሁኔታ ያስተዋልንና ሌሎች ‘የዘላለምን ሕይወት ቃል’ እንዲሰሙ የመርዳቱን አስፈላጊነት የተገነዘብን እውነተኛ ክርስቲያኖች መሆናችንን የሚያሳውቅ ነው። (ዮሐ. 6:68) በጣም አስፈላጊ በሆነው በዚህ ሥራ በቅንዓት በመካፈል በመንፈሳዊ ንቁ መሆናችንን እናሳያለን።
3 ለመስበክ ተገፋፉ:- የይሖዋ ምሥክሮች እንደመሆናችን መጠን ስለ አገልግሎታችን አዎንታዊ የሆነ አመለካከት ሊኖረን ይገባል። ለአምላክና ለጎረቤቶቻችን ያለን ፍቅር በስብከቱ ሥራ የበኩላችንን እንድናደርግ ይገፋፋናል። (1 ቆሮ. 9:16, 17) እንዲህ ስናደርግ ራሳችንንም ሆነ የሚሰሙንን እናድናለን። (1 ጢሞ. 4:16) ለሰው ልጆች ከሁሉ የተሻለ መስተዳድር ስለሆነው የአምላክ መንግሥት ምሥራች በመስበኩ ሥራ በተቻለ መጠን አዘውትረን ለመካፈልና የሚያስፈልገውን ያህል ረዘም ያለ ሰዓት ለማገልገል ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ!
4 ታላቁ መከራ የሚጀምረው የስብከቱ ሥራ እየተከናወነ እንዳለ መሆኑን ማወቃችን የአገልግሎታችንን አጣዳፊነት የሚያጎላ እውነታ ነው። ቀኑንና ሰዓቱን አለማወቃችን በጸሎት በይሖዋ ላይ በመደገፍ ሁል ጊዜ ንቁዎችና ዝግጁ ሆነን እንድንገኝ ይጠይቅብናል። (ኤፌ. 6:18) የስብከቱ ሥራ አድማሱን እያሰፋ መሄዱን ይቀጥላል። ይሁን እንጂ ይህ በሰው ልጅ ታሪክ ታላቅ የሆነው የምሥክርነት ሥራ በቅርቡ ወደ ታላቅ መደምደሚያው ይደርሳል።
5 ኢየሱስ “ነቅታችሁ ኑሩ” ሲል የሰጠውን ትእዛዝ በታማኝነት እንከተል። ይህ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ዛሬ በጣም አንገብጋቢ ሆኗል። ለዚህ ትእዛዝ በጥድፊያ ስሜት ምላሽ እንስጥ። ዛሬም ሆነ ዘወትር መንፈሳዊነታችንን በቁም ነገር የምንመለከት፣ ንቁዎች እንዲሁም በይሖዋ አገልግሎት በትጋት የምንሳተፍ እንሁን። አዎን፣ “እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደሌሎቹ አናንቀላፋ።”—1 ተሰ. 5:6