ኢሳይያስ
28 ጎልታ ለምትታየው* ለኤፍሬም+ ሰካራሞች አክሊል* ወዮላት!
ይህች የምታምር ጌጥ በወይን ጠጅ የተሸነፉ ሰዎች በሚኖሩበት
ለም ሸለቆ አናት ላይ የምትገኝ የምትጠወልግ አበባ ናት።
2 እነሆ፣ ይሖዋ ጠንካራና ብርቱ የሆነውን ይልካል።
እሱም እንደ ነጎድጓዳማ የበረዶ ውሽንፍር፣ እንደ አጥፊ አውሎ ነፋስ፣
ኃይለኛ ጎርፍ እንደሚያስከትል ነጎድጓዳማ ውሽንፍር
በኃይል አሽቀንጥሮ ወደ ምድር ይጥላታል።
ሰውም ባያት ጊዜ ቀጥፎ ወዲያውኑ ይውጣታል።
5 በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከሕዝቡ መካከል ለተረፉት ሰዎች የሚያምር አክሊልና ውብ የአበባ ጉንጉን ይሆናል።+ 6 በፍርድ ወንበር ለተቀመጠውም የፍትሕ መንፈስ፣ የከተማዋ በር ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ለሚመክቱም የብርታት ምንጭ ይሆናል።+
7 እነዚህም ከወይን ጠጅ የተነሳ መንገድ ይስታሉ፤
ከሚያሰክር መጠጥ የተነሳም ይንገዳገዳሉ።
ካህኑና ነቢዩ ከጠጡት መጠጥ የተነሳ መንገድ ይስታሉ፤
ከወይን ጠጅ የተነሳ ግራ ይጋባሉ፤
ከሚያሰክር መጠጥ የተነሳም ይንገዳገዳሉ፤
የሚያዩት ራእይ መንገድ ያስታቸዋል፤
ፍርድ ሲሰጡም ይሳሳታሉ።+
8 ገበታቸው ሁሉ በሚያስጸይፍ ትውከት ተሞልቷል፤
ያልተበላሸ ቦታም የለም።
9 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ “እውቀትን የሚያካፍለው ለማን ነው?
መልእክቱንስ የሚያስረዳው ለማን ነው?
ገና ወተት ለተዉ፣
ጡትም ለጣሉ ሕፃናት ነው?
11 ስለዚህ በሚንተባተቡ ሰዎች አንደበትና በባዕድ ቋንቋ ለዚህ ሕዝብ ይናገራል።+ 12 በአንድ ወቅት “ይህ የእረፍት ቦታ ነው። የዛለው እንዲያርፍ አድርጉ፤ ይህ የእፎይታ ቦታ ነው” ብሏቸው ነበር፤ እነሱ ግን ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም።+ 13 የይሖዋም ቃል ለእነሱ
16 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
በእሱ የሚያምን አይደናገጥም።+
የውሸት መጠጊያውን፣ በረዶ ጠራርጎ ይወስደዋል፤
ውኃዎቹም መደበቂያ ቦታውን ያጥለቀልቁታል።
በድንገት የሚያጥለቀልቀው ጎርፍ ሲያልፍ
ድምጥማጣችሁን ያጠፋል።
የተነገረውን ነገር እንዲረዱ የሚያደርገው ሽብር ብቻ ነው።”*
20 እግር ተዘርግቶ እንዳይተኛ አልጋው አጭር ነውና፤
ተሸፋፍኖም እንዳይተኛ ጨርቁ በጣም ጠባብ ነው።
21 ይሖዋ ተግባሩን ይኸውም እንግዳ የሆነ ተግባሩን ያከናውን ዘንድ
እንዲሁም ሥራውን ይኸውም ያልተለመደ ሥራውን ይሠራ ዘንድ+
በጰራጺም ተራራ እንዳደረገው ይነሳልና፤
አለዚያ እስራቱ ይበልጥ ይጠብቅባችኋል፤
ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ
23 ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ድምፄንም ስሙ፤
ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጡ፤ በጥሞናም አዳምጡ።
24 ገበሬ ዘር ከመዝራቱ በፊት ቀኑን ሙሉ ሲያርስ ይውላል?
ደግሞስ ጓሉን ሲከሰክስና መሬቱን ሲያለሰልስ ይከርማል?+
25 ከዚህ ይልቅ መሬቱን ከደለደለ በኋላ
ጥቁር አዝሙድና ከሙን አይዘራም?
ስንዴውን፣ ማሽላውንና ገብሱንስ በቦታ በቦታቸው አይዘራም?
ደግሞስ አጃውን+ ዳር ላይ አይዘራም?
ጥቁር አዝሙድ በበትር፣
ከሙንም በዘንግ ይወቃል።
28 ሰው የዳቦ እህል እንዲደቅ ያደርጋል?