የጴጥሮስ ሁለተኛው ደብዳቤ
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፣ በአምላካችን ጽድቅ እንዲሁም በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ አማካኝነት እኛ ያገኘነውን ዓይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉ፦
2 ስለ አምላክና ስለ ጌታችን ኢየሱስ በምትቀስሙት ትክክለኛ እውቀት+ አማካኝነት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 3 መለኮታዊ ኃይሉ፣ በገዛ ክብሩና በጎነቱ ስለጠራን አምላክ ባገኘነው ትክክለኛ እውቀት+ ለአምላክ ያደርን ሆነን ለመኖር የሚረዱንን ነገሮች ሁሉ ሰጥቶናል።* 4 በእነዚህ ነገሮች አማካኝነት ክቡርና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋ ሰጥቶናል፤*+ ይህን ያደረገውም የመጥፎ ምኞት* ውጤት ከሆነው ከዓለም ብልሹ ምግባር አምልጣችሁ፣ በዚህ ተስፋ አማካኝነት ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ ነው።+
5 በመሆኑም ልባዊ ጥረት በማድረግ+ በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ጨምሩ፤+ በበጎነት ላይ እውቀትን፣+ 6 በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፣+ ራስን በመግዛት ላይ ጽናትን፣ በጽናት ላይ ለአምላክ ማደርን፣+ 7 ለአምላክ በማደር ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣ በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።+ 8 እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና ቢትረፈረፉ፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ትክክለኛ እውቀት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ይጠብቋችኋል።+
9 እነዚህ ነገሮች የሚጎድሉት ማንኛውም ሰው ብርሃን ላለማየት ዓይኑን የጨፈነ ዕውር ሰው* ነው፤+ ደግሞም ከቀድሞ ኃጢአቱ መንጻቱን ረስቷል።+ 10 በመሆኑም ወንድሞች፣ መጠራታችሁንና+ መመረጣችሁን አስተማማኝ ለማድረግ ከበፊቱ ይበልጥ ትጉ፤ እነዚህን ነገሮች የምታደርጉ ከሆነ ፈጽሞ አትወድቁምና።+ 11 እንዲያውም በእጅጉ ትባረካላችሁ፤ ጌታችንና አዳኛችን ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥትም+ ትገባላችሁ።+
12 ስለዚህ ምንም እንኳ እነዚህን ነገሮች የምታውቁና በተማራችሁት እውነት ጸንታችሁ የቆማችሁ ብትሆኑም፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ሁልጊዜ እናንተን ከማሳሰብ ወደኋላ አልልም። 13 በዚህ ድንኳን*+ እስካለሁ ድረስ እናንተን በማሳሰብ ማነቃቃት ተገቢ ይመስለኛል፤+ 14 ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጽ እንዳሳወቀኝ ይህ ድንኳን የሚወገድበት ጊዜ እንደቀረበ አውቃለሁ።+ 15 እኔ ከሄድኩ በኋላ እነዚህን ነገሮች ማስታወስ* እንድትችሉ ሁልጊዜ አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ አደርጋለሁ።
16 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መገኘት ያሳወቅናችሁ በብልሃት የተፈጠረ ተረት ተከትለን ሳይሆን ግርማውን በገዛ ዓይናችን አይተን ነው።+ 17 ከግርማዊው ክብር “እኔ ራሴ በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው”+ የሚል ቃል* ለእሱ በተነገረ ጊዜ ከአባታችንና ከአምላካችን ክብርና ሞገስ ተቀብሏል። 18 ከእሱ ጋር በቅዱሱ ተራራ በነበርንበት ጊዜ ይህ ቃል ከሰማይ ሲመጣ ሰምተናል።
19 በመሆኑም ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ጎህ እስኪቀድና የንጋት ኮከብ+ እስኪወጣ ድረስ በጨለማ ቦታ፣ በልባችሁ ውስጥ ለሚበራ መብራት+ የምትጠነቀቁትን ያህል ለትንቢታዊው ቃል ትኩረት መስጠታችሁ መልካም ነው። 20 በመጀመሪያ ደረጃ፣ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ያለው ትንቢት ሁሉ በሰው ሐሳብ ላይ የተመሠረተ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። 21 መቼም ቢሆን ትንቢት በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤+ ከዚህ ይልቅ ሰዎች ከአምላክ የተቀበሉትን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው* ተናገሩ።+