የዳዊት ማህሌት።
143 ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+
እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና አዳምጥ።
እንደ ታማኝነትህና እንደ ጽድቅህ መጠን መልስልኝ።
2 ሕያው የሆነ ማንኛውም ሰው በፊትህ ጻድቅ ሊሆን ስለማይችል፣+
አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበው።
3 ጠላት ያሳድደኛልና፤
ሕይወቴንም አድቆ ከአፈር ደባልቋታል።
ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሞቱ ሰዎች በጨለማ ቦታ እንድኖር አድርጎኛል።
4 መንፈሴ በውስጤ ዛለ፤+
ልቤ በውስጤ ደነዘዘ።+
5 የጥንቱን ዘመን አስታውሳለሁ፤
ባከናወንካቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤+
የእጆችህን ሥራ በታላቅ ጉጉት አውጠነጥናለሁ።
6 እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤
እንደ ደረቅ ምድር አንተን ተጠማሁ።+ (ሴላ)
7 ይሖዋ ሆይ፣ ፈጥነህ መልስልኝ።+
ጉልበቴ ተሟጠጠ።+
ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤+
አለዚያ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ።+
8 በአንተ ታምኛለሁና፣
በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን ልስማ።
ፊቴን ወደ አንተ አዞራለሁና፣
ልሄድበት የሚገባውን መንገድ አሳውቀኝ።+
9 ይሖዋ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ።
የአንተን ጥበቃ እሻለሁ።+
10 አንተ አምላኬ ስለሆንክ፣
ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ።+
መንፈስህ ጥሩ ነው፤
በደልዳላ መሬት ይምራኝ።
11 ይሖዋ ሆይ፣ ለስምህ ስትል በሕይወት አቆየኝ።
በጽድቅህ ከጭንቅ ታደገኝ።+
12 በታማኝ ፍቅርህ ጠላቶቼን አስወግዳቸው፤+
አገልጋይህ ነኝና፣+
የሚያጎሳቁሉኝን ሰዎች ሁሉ አጥፋቸው።+