የማቴዎስ ወንጌል
19 ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ከገሊላ ወጥቶ ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳሉት የይሁዳ ድንበሮች መጣ።+ 2 እጅግ ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ እሱም በዚያ ፈወሳቸው።
3 ፈሪሳውያንም ወደ እሱ መጥተው ሊፈትኑት በማሰብ “አንድ ሰው በማንኛውም ምክንያት ሚስቱን እንዲፈታ ሕግ ይፈቅድለታል?” ሲሉ ጠየቁት።+ 4 እሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ “ፈጣሪ ከመጀመሪያውም ወንድና ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው አላነበባችሁም?+ 5 ‘ከዚህ የተነሳ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’ ብሎ እንደተናገረስ አላነበባችሁም?+ 6 በመሆኑም ከዚህ በኋላ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። ስለዚህ አምላክ ያጣመረውን* ማንም ሰው አይለያየው።”+ 7 እነሱም “ታዲያ ሙሴ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ሰጥቶ እንዲፈታት ያዘዘው ለምንድን ነው?” አሉት።+ 8 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴ የልባችሁን ደንዳናነት አይቶ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ፈቀደላችሁ+ እንጂ ከመጀመሪያው እንዲህ አልነበረም።+ 9 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፆታ ብልግና* ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።”+
10 ደቀ መዛሙርቱም “በባልና በሚስት መካከል ያለው ሁኔታ እንዲህ ከሆነስ አለማግባት ይመረጣል” አሉት። 11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ስጦታው ያላቸው ካልሆኑ በስተቀር ይህን ሁሉም ሰው ሊቀበለው አይችልም።+ 12 ምክንያቱም ጃንደረባ ሆነው የሚወለዱ አሉ፤ ሰው የሰለባቸው ጃንደረቦችም አሉ፤ እንዲሁም ለመንግሥተ ሰማያት ሲሉ ራሳቸውን ጃንደረባ ያደረጉ ጃንደረቦችም አሉ። ይህን ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው።”+
13 ከዚያም ኢየሱስ እጁን እንዲጭንባቸውና* እንዲጸልይላቸው ትናንሽ ልጆችን ወደ እሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው።+ 14 ይሁን እንጂ ኢየሱስ “ልጆቹን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ እንዳይመጡ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ነውና” አለ።+ 15 እጁንም ከጫነባቸው* በኋላ ከዚያ ስፍራ ተነስቶ ሄደ።
16 ከዚያም አንድ ወጣት ወደ እሱ መጥቶ “መምህር፣ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ጥሩ ነገር ማድረግ ይኖርብኛል?” አለው።+ 17 እሱም “ስለ ጥሩ ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? ጥሩ የሆነው አምላክ ብቻ ነው።+ ሆኖም ሕይወት ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ዘወትር ትእዛዛቱን ጠብቅ” አለው።+ 18 እሱም “የትኞቹን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “አትግደል፣+ አታመንዝር፣+ አትስረቅ፣+ በሐሰት አትመሥክር፣+ 19 አባትህንና እናትህን አክብር+ እንዲሁም ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ።”+ 20 ወጣቱም “እነዚህን ሁሉ ስጠብቅ ኖሬአለሁ፤ ታዲያ አሁን የሚጎድለኝ ነገር ምንድን ነው?” አለው። 21 ኢየሱስም “ፍጹም* መሆን ከፈለግክ ሂድና ንብረትህን ሸጠህ ገንዘቡን ለድሆች ስጥ፤ በሰማይም ውድ ሀብት ታገኛለህ፤+ ደግሞም መጥተህ ተከታዬ ሁን” አለው።+ 22 ወጣቱም ይህን ሲሰማ ብዙ ንብረት ስለነበረው እያዘነ ሄደ።+ 23 ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ሀብታም ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት እጅግ አስቸጋሪ ይሆንበታል።+ 24 ዳግመኛም እላችኋለሁ፣ ሀብታም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።”+
25 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲሰሙ በጣም ተገርመው “በዚህ ዓይነትማ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ።+ 26 ኢየሱስም ትኩር ብሎ እያያቸው “ይህ በሰዎች ዘንድ አይቻልም፤ በአምላክ ዘንድ ግን ሁሉ ነገር ይቻላል” አላቸው።+
27 ከዚያም ጴጥሮስ መልሶ “እነሆ፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከትለንሃል፤ ታዲያ የምናገኘው ምን ይሆን?” አለው።+ 28 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ሁሉም ነገር አዲስ በሚሆንበት ጊዜ* የሰው ልጅ፣ ክብራማ በሆነው ዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ እኔን የተከተላችሁኝ እናንተ በ12 ዙፋኖች ላይ ተቀምጣችሁ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።+ 29 እንዲሁም ስለ ስሜ ሲል ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እህቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለም ሕይወትም ይወርሳል።+