የጴጥሮስ የመጀመሪያው ደብዳቤ
3 በተመሳሳይም እናንተ ሚስቶች፣ ለቃሉ የማይታዘዙ ባሎች ካሉ ያለቃል በሚስቶቻቸው ምግባር እንዲማረኩ+ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤+ 2 ሊማረኩ የሚችሉትም ንጹሕ ምግባራችሁንና+ የምታሳዩትን ጥልቅ አክብሮት ሲመለከቱ ነው። 3 ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በማጌጥ ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ የወርቅ ጌጣጌጦች በማድረግ+ ወይም ያማረ ልብስ በመልበስ አይሁን፤ 4 ከዚህ ይልቅ ውበታችሁ የማይጠፋውን ጌጥ ይኸውም በአምላክ ፊት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የሰከነና ገር መንፈስ የተላበሰ+ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁን። 5 ተስፋቸውን በአምላክ ላይ የጣሉ በቀድሞ ጊዜ የነበሩ ቅዱሳን ሴቶች ራሳቸውን ለባሎቻቸው በማስገዛት በዚህ ዓይነት ሁኔታ ራሳቸውን ያስውቡ ነበርና፤ 6 ሣራም አብርሃምን ጌታዬ እያለች በመጥራት ትታዘዘው ነበር።+ እናንተም መልካም ማድረጋችሁን ከቀጠላችሁና በፍርሃት ካልተሸነፋችሁ+ ልጆቿ ናችሁ።
7 በተመሳሳይም እናንተ ባሎች ከእነሱ ጋር በእውቀት* አብራችሁ ኑሩ። እነሱም ከእናንተ ጋር የሕይወትን ጸጋ አብረው ስለሚወርሱ+ ጸሎታችሁ እንዳይታገድ ከእናንተ ይበልጥ እንደ ተሰባሪ ዕቃ የሆኑትን ሴቶችን አክብሯቸው።+
8 በመጨረሻም ሁላችሁም የአስተሳሰብ አንድነት* ይኑራችሁ፤+ የሌላውን ስሜት የምትረዱ ሁኑ፤ የወንድማማች መዋደድ ይኑራችሁ፤ ከአንጀት የምትራሩ ሁኑ፤+ ትሑታን ሁኑ።+ 9 ክፉን በክፉ+ ወይም ስድብን በስድብ አትመልሱ።+ ከዚህ ይልቅ ባርኩ፤+ የተጠራችሁት ይህን ጎዳና በመከተል በረከትን እንድትወርሱ ነውና።
10 ስለዚህ “ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ ሰው በምላሱ ክፉ ነገር ከመናገር፣+ በከንፈሩም ከማታለል ይቆጠብ። 11 ክፉ ከሆነ ነገር ይራቅ፤+ መልካም የሆነውንም ያድርግ፤+ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተለውም።+ 12 የይሖዋ* ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮዎቹም ምልጃቸውን ይሰማሉ፤+ የይሖዋ* ፊት ግን ክፉ ነገሮችን በሚያደርጉ ላይ ነው።”+
13 መልካም ነገር ለማድረግ ቀናተኞች ብትሆኑ ጉዳት የሚያደርስባችሁ ማን ነው?+ 14 ሆኖም ለጽድቅ ስትሉ መከራ ብትቀበሉ ደስተኞች ናችሁ።+ ይሁን እንጂ እነሱ የሚፈሩትን እናንተ አትፍሩ፤* ደግሞም አትሸበሩ።+ 15 ነገር ግን ክርስቶስን እንደ ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ ስላላችሁ ተስፋ፣ ምክንያት እንድታቀርቡ ለሚጠይቃችሁ ሰው ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር ዝግጁ ሁኑ፤ ይህን ስታደርጉ ግን በገርነት* መንፈስና+ በጥልቅ አክብሮት ይሁን።+
16 ስለ እናንተ መጥፎ ነገር የሚናገሩ ሰዎች፣ የክርስቶስ ተከታዮች እንደመሆናችሁ መጠን በምታሳዩት መልካም ምግባር+ የተነሳ ስለ እናንተ በሚናገሩት በማንኛውም መጥፎ ነገር እንዲያፍሩ+ ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ።+ 17 ክፉ ነገር ሠርታችሁ መከራ ከምትቀበሉ+ ይልቅ የአምላክ ፈቃድ ከሆነ፣ መልካም ነገር ሠርታችሁ መከራ ብትቀበሉ ይሻላልና።+ 18 ጻድቅ የሆነው ክርስቶስ እንኳ ለዓመፀኞች+ ሲል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመሞት+ ከኃጢአት ነፃ አውጥቷቸዋልና። ይህን ያደረገው እናንተን ወደ አምላክ ለመምራት ነው።+ ሥጋ ሆኖ ተገደለ፤+ ሆኖም መንፈስ ሆኖ ሕያው ሆነ።+ 19 በዚህ ሁኔታ እያለም ሄዶ በእስር ላሉት መናፍስት ሰበከላቸው፤*+ 20 እነዚህ መናፍስት ቀደም ሲል ማለትም በኖኅ ዘመን ጥቂት ሰዎች ይኸውም ስምንት ነፍሳት* በውኃው መካከል አልፈው የዳኑበት+ መርከብ እየተሠራ በነበረበት ጊዜ፣+ አምላክ በትዕግሥት እየጠበቀ ሳለ* ሳይታዘዙ የቀሩ ናቸው።+
21 አሁንም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነው ጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካኝነት እናንተን እያዳናችሁ ነው። ጥምቀት የሰውነትን እድፍ የሚያስወግድ ሳይሆን ጥሩ ሕሊና ለማግኘት ለአምላክ የሚቀርብ ልመና ነው።+ 22 ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሄደ ሲሆን አሁን በአምላክ ቀኝ ይገኛል፤+ እንዲሁም መላእክት፣ ሥልጣናትና ኃይላት እንዲገዙለት ተደርጓል።+