አንደኛ ዜና መዋዕል
5 የያፌት ወንዶች ልጆች ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዳይ፣ ያዋን፣ ቱባል፣+ መሼቅ+ እና ቲራስ+ ነበሩ።
6 የጎሜር ወንዶች ልጆች አሽከናዝ፣ ሪፋት እና ቶጋርማ+ ነበሩ።
7 የያዋን ወንዶች ልጆች ኤሊሻ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም እና ሮዳኒም ነበሩ።
8 የካም ወንዶች ልጆች ኩሽ፣+ ሚጽራይም፣ ፑጥ እና ከነአን+ ነበሩ።
9 የኩሽ ወንዶች ልጆች ሴባ፣+ ሃዊላ፣ ሳብታ፣ ራአማ እና ሳብተካ ነበሩ።
የራአማ+ ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን+ ነበሩ።
10 ኩሽ ናምሩድን+ ወለደ። እሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኃያል ሰው ነበር።
11 ሚጽራይም ሉድን፣+ አናሚምን፣ ለሃቢምን፣ ናፊቱሂምን፣+ 12 ጳትሩሲምን፣+ ካስሉሂምን (ፍልስጤማውያን+ የተገኙት ከእሱ ነው) እንዲሁም ካፍቶሪምን+ ወለደ።
13 ከነአን የበኩር ልጁን ሲዶናን፣+ ሄትን+ 14 እንዲሁም ኢያቡሳዊውን፣+ አሞራዊውን፣+ ገርጌሻዊውን፣+ 15 ሂዋዊውን፣+ አርቃዊውን፣ ሲናዊውን፣ 16 አርዋዳዊውን፣+ ጸማራዊውን እና ሃማታዊውን ወለደ።
18 አርፋክስድ ሴሎምን+ ወለደ፤ ሴሎምም ኤቤርን ወለደ።
19 ኤቤር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የአንደኛው ስም ፋሌቅ*+ ነበር፤ ምክንያቱም በእሱ የሕይወት ዘመን ምድር ተከፋፍላ* ነበር። የወንድሙ ስም ደግሞ ዮቅጣን ነበር።
20 ዮቅጣን አልሞዳድን፣ ሸሌፍን፣ ሃጻርማዌትን፣ ያራህን፣+ 21 ሃዶራምን፣ ዑዛልን፣ ዲቅላን፣ 22 ኦባልን፣ አቢማዔልን፣ ሳባን፣ 23 ኦፊርን፣+ ሃዊላን+ እና ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ነበሩ።
28 የአብርሃም ወንዶች ልጆች ይስሐቅ+ እና እስማኤል+ ነበሩ።
29 የቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው የሚከተለው ነው፦ የእስማኤል የበኩር ልጅ ነባዮት+ ከዚያም ቄዳር፣+ አድበዔል፣ ሚብሳም፣+ 30 ሚሽማ፣ ዱማ፣ ማሳ፣ ሃዳድ፣ ቴማ፣ 31 የጡር፣ ናፊሽ እና ቄድማ። እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ነበሩ።
32 የአብርሃም ቁባት የነበረችው ኬጡራ+ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዚምራን፣ ዮቅሻን፣ ሚዳን፣ ምድያም፣+ ይሽባቅ እና ሹሃ+ ነበሩ።
የዮቅሻን ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን+ ነበሩ።
33 የምድያም ወንዶች ልጆች ኤፋ፣+ ኤፌር፣ ሃኖክ፣ አቢዳዕ እና ኤልዳዓ ነበሩ።
እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
34 አብርሃም ይስሐቅን+ ወለደ። የይስሐቅ ወንዶች ልጆች ኤሳው+ እና እስራኤል+ ነበሩ።
35 የኤሳው ወንዶች ልጆች ኤሊፋዝ፣ ረኡዔል፣ የኡሽ፣ ያላም እና ቆሬ+ ነበሩ።
36 የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆች ቴማን፣+ ኦማር፣ ጸፎ፣ ጋታም፣ ቀናዝ፣ ቲምና እና አማሌቅ+ ነበሩ።
37 የረኡዔል ወንዶች ልጆች ናሃት፣ ዛራ፣ ሻማህ እና ሚዛህ+ ነበሩ።
38 የሴይር+ ወንዶች ልጆች ሎጣን፣ ሾባል፣ ጺብኦን፣ አና፣ ዲሾን፣ ኤጼር እና ዲሻን+ ነበሩ።
39 የሎጣን ወንዶች ልጆች ሆሪ እና ሆማም ነበሩ። የሎጣን እህት ቲምና+ ትባል ነበር።
40 የሾባል ወንዶች ልጆች አልዋን፣ ማናሃት፣ ኤባል፣ ሼፎ እና ኦናም ነበሩ።
የጺብኦን ወንዶች ልጆች አያ እና አና+ ነበሩ።
41 የአና ልጅ* ዲሾን ነበር።
የዲሾን ወንዶች ልጆች ሄምዳን፣ ኤሽባን፣ ይትራን እና ኬራን+ ነበሩ።
42 የኤጼር+ ወንዶች ልጆች ቢልሃን፣ ዛአዋን እና አቃን ነበሩ።
የዲሻን ወንዶች ልጆች ዑጽ እና አራን+ ነበሩ።
43 እነዚህ በእስራኤላውያን*+ ላይ የትኛውም ንጉሥ መግዛት ከመጀመሩ በፊት በኤዶም+ ምድር ይገዙ የነበሩ ነገሥታት ናቸው፦ የቢዖር ልጅ ቤላ፣ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። 44 ቤላ ሲሞት የቦስራው+ የዛራ ልጅ ዮባብ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 45 ዮባብ ሲሞት ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሁሻም በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 46 ሁሻም ሲሞት ምድያምን በሞዓብ ምድር* ድል ያደረገው የቤዳድ ልጅ ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማው ስም አዊት ይባል ነበር። 47 ሃዳድ ሲሞት የማስረቃው ሳምላ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 48 ሳምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የረሆቦቱ ሻኡል በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 49 ሻኡል ሲሞት የአክቦር ልጅ ባአልሀናን በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 50 ባአልሀናን ሲሞት ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማውም ስም ጳኡ ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣቤል ሲሆን እሷም የመዛሃብ ሴት ልጅ የማጥሬድ ልጅ ናት። 51 ከዚያም ሃዳድ ሞተ።
የኤዶም አለቆች፣* አለቃ ቲምና፣ አለቃ አልዋህ፣ አለቃ የቴት፣+ 52 አለቃ ኦሆሊባማ፣ አለቃ ኤላህ፣ አለቃ ፒኖን፣ 53 አለቃ ቀናዝ፣ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ሚብጻር፣ 54 አለቃ ማግዲኤል እና አለቃ ኢራም ነበሩ። እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ።
2 የእስራኤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ሮቤል፣+ ስምዖን፣+ ሌዊ፣+ ይሁዳ፣+ ይሳኮር፣+ ዛብሎን፣+ 2 ዳን፣+ ዮሴፍ፣+ ቢንያም፣+ ንፍታሌም፣+ ጋድ+ እና አሴር።+
3 የይሁዳ ወንዶች ልጆች ኤር፣ ኦናን እና ሴሎም ነበሩ። እነዚህ ሦስቱ ከከነአናዊቷ ከሹአ ሴት ልጅ የተወለዱለት ናቸው።+ የይሁዳ የበኩር ልጅ የሆነው ኤር ግን ይሖዋን አሳዘነ፤ እሱም ቀሰፈው።+ 4 የይሁዳ ምራት ትዕማር+ ፋሬስን+ እና ዛራን ወለደችለት። የይሁዳ ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ አምስት ነበሩ።
5 የፋሬስ ወንዶች ልጆች ኤስሮን እና ሃሙል+ ነበሩ።
6 የዛራ ወንዶች ልጆች ዚምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ካልኮል እና ዳራ ነበሩ። በአጠቃላይ አምስት ነበሩ።
7 የካርሚ ልጅ* አካር* ነበር፤ እሱም ለጥፋት ከተለየው ነገር ጋር በተያያዘ እምነት በማጉደሉ በእስራኤል ላይ መዓት* አምጥቷል።+
8 የኤታን ልጅ* አዛርያስ ነበር።
9 ለኤስሮን የተወለዱለት ወንዶች ልጆች የራህምኤል፣+ ራም+ እና ከሉባይ* ነበሩ።
10 ራም አሚናዳብን+ ወለደ፤ አሚናዳብ የይሁዳ ዘሮች አለቃ የሆነውን ነአሶንን+ ወለደ። 11 ነአሶን ሳልማን+ ወለደ። ሳልማ ቦዔዝን+ ወለደ። 12 ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ። ኢዮቤድ እሴይን+ ወለደ። 13 እሴይ የበኩር ልጁን ኤልያብን፣ ሁለተኛውን ልጁን አቢናዳብን፣+ ሦስተኛውን ልጁን ሺምአን፣+ 14 አራተኛውን ልጁን ናትናኤልን፣ አምስተኛውን ልጁን ራዳይን፣ 15 ስድስተኛውን ልጁን ኦጼምን እና ሰባተኛውን ልጁን ዳዊትን+ ወለደ። 16 እህቶቻቸው ጽሩያ እና አቢጋኤል+ ነበሩ። የጽሩያ ወንዶች ልጆች ሦስት ሲሆኑ እነሱም አቢሳ፣+ ኢዮዓብ+ እና አሳሄል+ ነበሩ። 17 አቢጋኤልም አሜሳይን+ ወለደች፤ የአሜሳይ አባት እስማኤላዊው የቴር ነበር።
18 የኤስሮን ልጅ ካሌብ* ከሚስቱ ከአዙባ እና ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ የእሷም ወንዶች ልጆች የሼር፣ ሾባብ እና አርዶን ነበሩ። 19 አዙባ ስትሞት ካሌብ ኤፍራታን+ አገባ፤ እሷም ሁርን+ ወለደችለት። 20 ሁር ዖሪን ወለደ። ዖሪ ባስልኤልን+ ወለደ።
21 ከዚያም ኤስሮን የጊልያድ+ አባት ከሆነው ከማኪር+ ሴት ልጅ ጋር ግንኙነት ፈጸመ። እሷን ያገባት በ60 ዓመቱ ነበር፤ እሷም ሰጉብን ወለደችለት። 22 ሰጉብ ያኢርን+ ወለደ፤ እሱም በጊልያድ+ ምድር 23 ከተሞች ነበሩት። 23 በኋላም ገሹር+ እና ሶርያ+ ቄናትንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞች ጨምሮ ሃዎትያኢርን+ ይኸውም 60 ከተሞችን ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የጊልያድ አባት የሆነው የማኪር ዘሮች ነበሩ።
24 ኤስሮን+ በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮን ሚስት የሆነችው አቢያህ፣ የተቆአ+ አባት የሆነውን አሽሁርን+ ወለደችለት።
25 የኤስሮን የበኩር ልጅ የራህምኤል የወለዳቸው ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም እና አኪያህ ነበሩ። 26 የራህምኤል፣ አታራ የተባለች ሌላ ሚስት አገባ። እሷም የኦናም እናት ነበረች። 27 የየራህምኤል የበኩር ልጅ የራም ወንዶች ልጆች ማአጽ፣ ያሚን እና ኤቄር ነበሩ። 28 የኦናም ወንዶች ልጆች ሻማይ እና ያዳ ነበሩ። የሻማይ ወንዶች ልጆች ናዳብ እና አቢሹር ነበሩ። 29 የአቢሹር ሚስት አቢሃይል ትባል ነበር፤ እሷም አህባንን እና ሞሊድን ወለደችለት። 30 የናዳብ ወንዶች ልጆች ሰሌድ እና አፋይም ነበሩ። ሆኖም ሰሌድ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። 31 የአፋይም ልጅ* ይሽኢ ነበር። የይሽኢ ልጅ* ሸሻን ነበር፤ የሸሻን ልጅ* አህላይ ነበር። 32 የሻማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች የቴር እና ዮናታን ነበሩ። የቴር ግን ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። 33 የዮናታን ወንዶች ልጆች ፐሌት እና ዛዛ ነበሩ። እነዚህ የየራህምኤል ዘሮች ነበሩ።
34 ሸሻን ሴቶች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። ሸሻን፣ ያርሃ የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው። 35 ሸሻን ለአገልጋዩ ለያርሃ ሴት ልጁን ዳረለት፤ እሷም አታይን ወለደችለት። 36 አታይ ናታንን ወለደ። ናታን ዛባድን ወለደ። 37 ዛባድ ኤፍላልን ወለደ። ኤፍላል ኢዮቤድን ወለደ። 38 ኢዮቤድ ኢዩን ወለደ። ኢዩ አዛርያስን ወለደ። 39 አዛርያስ ሄሌጽን ወለደ። ሄሌጽ ኤልዓሳን ወለደ። 40 ኤልዓሳ ሲስማይን ወለደ። ሲስማይ ሻሉምን ወለደ። 41 ሻሉም የቃምያህን ወለደ። የቃምያህ ኤሊሻማን ወለደ።
42 የየራህምኤል ወንድም የካሌብ*+ ወንዶች ልጆች፣ የዚፍ አባት የሆነው የበኩር ልጁ ሜሻ እንዲሁም የኬብሮን አባት የማሬሻህ ወንዶች ልጆች ነበሩ። 43 የኬብሮን ወንዶች ልጆች ቆሬ፣ ታጱአ፣ ራቄም እና ሼማ ነበሩ። 44 ሼማ የዮርቀአምን አባት ራሃምን ወለደ። ራቄም ሻማይን ወለደ። 45 የሻማይ ልጅ ማኦን ነበር። ማኦን ቤትጹርን+ ወለደ። 46 የካሌብ ቁባት ኤፋ ካራንን፣ ሞጻንና ጋዜዝን ወለደች። ካራን ጋዜዝን ወለደ። 47 የያህዳይ ወንዶች ልጆች ረጌም፣ ኢዮዓታም፣ ጌሻን፣ ጴሌጥ፣ ኤፋ እና ሻአፍ ነበሩ። 48 የካሌብ ቁባት ማአካ ሸበርን እና ቲርሃናን ወለደች። 49 ከጊዜ በኋላም የማድማናን+ አባት ሻአፍን እንዲሁም የማክበናን እና የጊባዓን+ አባት ሻዌን ወለደች። የካሌብ+ ሴት ልጅ አክሳ+ ትባል ነበር። 50 የካሌብ ዘሮች እነዚህ ነበሩ።
የኤፍራታ+ የበኩር ልጅ የሆነው የሁር+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የቂርያትየአሪም+ አባት ሾባል፣ 51 የቤተልሔም+ አባት ሳልማ እና የቤትጋዴር አባት ሃሬፍ። 52 የቂርያትየአሪም አባት የሾባል ልጆች ሃሮኤ እና የመኑሆት ሰዎች እኩሌታ ነበሩ። 53 የቂርያትየአሪም ወገኖች ይትራውያን፣+ ፑታውያን፣ ሹማታውያን እና ሚሽራውያን ነበሩ። ጾራውያን+ እና ኤሽታዖላውያን+ የተገኙት ከእነዚህ ወገኖች ነው። 54 የሳልማ ልጆች ቤተልሔም፣+ ነጦፋውያን፣ አትሮት ቤት ዮአብ፣ የማናሃታውያን ሰዎች እኩሌታና ጾራውያን ነበሩ። 55 በያቤጽ የሚኖሩት የጸሐፍት ወገኖች ቲራታውያን፣ ሺመአታውያን እና ሱካታውያን ነበሩ። እነዚህ የሬካብ+ ቤት አባት ከሆነው ከሃማት የተገኙት ቄናውያን+ ናቸው።
3 ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦+ የበኩር ልጁ አምኖን፤+ እናቱ ኢይዝራኤላዊቷ አኪኖዓም+ ነበረች፤ ሁለተኛው ልጁ ዳንኤል፤ እናቱ ቀርሜሎሳዊቷ አቢጋኤል+ ነበረች፤ 2 የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማአካ የወለደው ሦስተኛው ልጁ አቢሴሎም፤+ ከሃጊት የወለደው አራተኛው ልጁ አዶንያስ፤+ 3 አምስተኛው ልጁ ሰፋጥያህ፤ እናቱ አቢጣል ነበረች፤ ስድስተኛው ልጁ ይትረአም፤ እናቱ የዳዊት ሚስት ኤግላ ነበረች። 4 እነዚህ ስድስቱ በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ናቸው፤ በዚያም ለ7 ዓመት ከ6 ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌም ደግሞ 33 ዓመት ነገሠ።+
5 በኢየሩሳሌም የተወለዱለት እነዚህ ናቸው፦+ ሺምአ፣ ሾባብ፣ ናታን+ እና ሰለሞን፤+ የእነዚህ የአራቱ ልጆች እናት የአሚዔል ልጅ ቤርሳቤህ+ ነበረች። 6 ሌሎቹ ዘጠኝ ወንዶች ልጆች ደግሞ ይብሃር፣ ኤሊሻማ፣ ኤሊፌሌት፣ 7 ኖጋ፣ ኔፌግ፣ ያፊአ፣ 8 ኤሊሻማ፣ ኤሊያዳ እና ኤሊፌሌት ናቸው። 9 ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ የዳዊት ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ እህታቸውም ትዕማር+ ትባል ነበር።
10 የሰለሞን ልጅ ሮብዓም፣+ የሮብዓም ልጅ አቢያህ፣+ የአቢያህ ልጅ አሳ፣+ የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ፣+ 11 የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም፣+ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣+ የአካዝያስ ልጅ ኢዮዓስ፣+ 12 የኢዮዓስ ልጅ አሜስያስ፣+ የአሜስያስ ልጅ አዛርያስ፣+ የአዛርያስ ልጅ ኢዮዓታም፣+ 13 የኢዮዓታም ልጅ አካዝ፣+ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣+ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ፣+ 14 የምናሴ ልጅ አምዖን፣+ የአምዖን ልጅ ኢዮስያስ።+ 15 የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ዮሃናን፣ ሁለተኛው ልጁ ኢዮዓቄም፣+ ሦስተኛው ልጁ ሴዴቅያስ+ እና አራተኛው ልጁ ሻሉም ነበሩ። 16 የኢዮዓቄም ወንዶች ልጆች ልጁ ኢኮንያን+ እና ልጁ ሴዴቅያስ ነበሩ። 17 የእስረኛው የኢኮንያን ወንዶች ልጆች ሰላትያል፣ 18 ማልኪራም፣ ፐዳያህ፣ ሸናጻር፣ የቃምያህ፣ ሆሻማ እና ነዳብያህ ነበሩ። 19 የፐዳያህ ወንዶች ልጆች ዘሩባቤል+ እና ሺምአይ ነበሩ፤ የዘሩባቤል ወንዶች ልጆችም መሹላም እና ሃናንያህ ነበሩ (ሸሎሚትም እህታቸው ነበረች)፤ 20 ሌሎቹ አምስት ወንዶች ልጆች ደግሞ ሃሹባ፣ ኦሄል፣ ቤራክያህ፣ ሃሳድያህ እና ዮሻብሄሴድ ነበሩ። 21 የሃናንያህ ወንዶች ልጆች ደግሞ ጰላጥያህ እና የሻያህ ነበሩ፤ የየሻያህ ልጅ* ረፋያህ ነበር፤ የረፋያህ ልጅ* አርናን ነበር፤ የአርናን ልጅ* አብድዩ ነበር፤ የአብድዩ ልጅ* ሸካንያህ ነበር፤ 22 የሸካንያህ ዘሮች ሸማያህና የሸማያህ ልጆች ናቸው፤ እነሱም ሃጡሽ፣ ይግዓል፣ ባሪያህ፣ ነአርያህ እና ሻፋጥ ሲሆኑ በአጠቃላይ ስድስት ነበሩ። 23 የነአርያህ ወንዶች ልጆች ኤሊዮዔናይ፣ ሂዝቅያህ እና አዝሪቃም ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። 24 የኤሊዮዔናይ ወንዶች ልጆች ደግሞ ሆዳውያህ፣ ኤልያሺብ፣ ፐላያህ፣ አቁብ፣ ዮሃናን፣ ደላያህ እና አናኒ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ።
4 የይሁዳ ወንዶች ልጆች ፋሬስ፣+ ኤስሮን፣+ ካርሚ፣ ሁር+ እና ሾባል+ ነበሩ። 2 የሾባል ልጅ ረአያህ ያሃትን ወለደ፤ ያሃት አሁማይን እና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾራውያን+ ቤተሰቦች ናቸው። 3 የኤጣም+ አባት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይድባሽ (የእህታቸውም ስም ሃጽሌልጶኒ ይባል ነበር)፤ 4 ጰኑኤል የጌዶር አባት ነው፤ ኤጼር ደግሞ የሁሻ አባት ነው። እነዚህ የኤፍራታ የበኩር ልጅና የቤተልሔም+ አባት የሆነው የሁር+ ወንዶች ልጆች ነበሩ። 5 የተቆአ+ አባት አሽሁር፣+ ሄላ እና ናዕራ የሚባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት። 6 ናዕራ አሁዛምን፣ ሄፌርን፣ ተመናይን እና ሃሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የናዕራ ወንዶች ልጆች ናቸው። 7 የሄላ ወንዶች ልጆች ደግሞ ጸረት፣ ይጽሃር እና ኤትናን ናቸው። 8 ቆጽ አኑብን እና ጾበባን ወለደ፤ ደግሞም የሃሩም ልጅ የሆነው የአሃርሔል ቤተሰቦች የተገኙት ከእሱ ነው።
9 ያቤጽ ከወንድሞቹ ይበልጥ የተከበረ ሰው ነበር፤ እናቱም “በሥቃይ ወለድኩት” ስትል ያቤጽ* የሚል ስም አወጣችለት። 10 ያቤጽ እንዲህ ሲል የእስራኤልን አምላክ ተማጸነ፦ “እንድትባርከኝና ግዛቴን እንድታሰፋልኝ እንዲሁም ጉዳት እንዳይደርስብኝ እጅህ ከእኔ ጋር እንድትሆንና ከጥፋት እንድትጠብቀኝ እለምንሃለሁ!” አምላክም የለመነውን ሰጠው።
11 የሹሃ ወንድም ከሉብ መሂርን ወለደ፤ መሂርም ኤሽቶንን ወለደ። 12 ኤሽቶን ቤትራፋን፣ ፓሰአህን እና የኢርናሃሽ አባት የሆነውን ተሂናን ወለደ። እነዚህ የረካ ሰዎች ነበሩ። 13 የቀናዝ ወንዶች ልጆች ኦትኒኤል+ እና ሰራያህ ነበሩ፤ የኦትኒኤል ልጅ* ደግሞ ሃታት ነበር። 14 መኦኖታይ ኦፍራን ወለደ። ሰራያህ የገሃራሺም* አባት የሆነውን ኢዮዓብን ወለደ፤ እንዲህ ተብለው የተጠሩት የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ስለነበሩ ነው።
15 የየፎኒ ልጅ የካሌብ+ ወንዶች ልጆች ኢሩ፣ ኤላህ እና ናአም ነበሩ፤ የኤላህ ልጅ* ቀናዝ ነበር። 16 የይሃሌልዔል ወንዶች ልጆች ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲሪያ እና አሳርኤል ነበሩ። 17 የኤዝራ ወንዶች ልጆች የቴር፣ መሬድ፣ ኤፌር እና ያሎን ነበሩ፤ እሷ* ሚርያምን፣ ሻማይን እና የኤሽተሞዓ አባት የሆነውን ይሽባን ወለደች። 18 (አይሁዳዊት ሚስቱ ደግሞ የጌዶርን አባት የሬድን፣ የሶኮን አባት ሄቤርን እና የዛኖሃን አባት የቁቲኤልን ወለደች።) እነዚህ የመሬድ ሚስት የሆነችው የፈርዖን ልጅ የቢትያ ወንዶች ልጆች ናቸው።
19 የናሃም እህት የሆነችው የሆዲያህ ሚስት ወንዶች ልጆች የጋርሚያዊው የቀኢላና የማአካታዊው የኤሽተሞዓ አባቶች ነበሩ። 20 የሺሞን ወንዶች ልጆች አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሃናን እና ቲሎን ነበሩ። የይሽኢ ወንዶች ልጆች ዞሄት እና ቤንዞሄት ነበሩ።
21 የይሁዳ ልጅ የሆነው የሴሎም+ ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የለቃ አባት ኤር፣ የማሬሻህ አባት ላአዳ እንዲሁም (ጥራት ያለው ጨርቅ የሚያመርቱት ሠራተኞች ወገን የሆኑት) የአሽቤዓ ቤት ሰዎች፣ 22 ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ሞዓባውያን ሴቶችን ያገቡት ዮአስ እና ሳራፍ እንዲሁም ያሹቢላሔም። እነዚህ መዛግብት ጥንታዊ ናቸው።* 23 እነሱም በነጣኢም እና በገዴራ የሚኖሩ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ። ለንጉሡ እየሠሩ በዚያ ይኖሩ ነበር።
24 የስምዖን+ ወንዶች ልጆች ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪብ፣ ዛራ እና ሻኡል+ ናቸው። 25 የሻኡል ልጅ ሻሉም፣ የሻሉም ልጅ ሚብሳም እና የሚብሳም ልጅ ሚሽማ ነበሩ። 26 ሃሙኤል የሚሽማ ልጅ ነበር፤ የሃሙኤል ልጅ ዛኩር፣ የዛኩር ልጅ ሺምአይ ነበር። 27 ሺምአይ 16 ወንዶችና 6 ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ከቤተሰቦቻቸውም መካከል እንደ ይሁዳ ሰዎች ብዙ ልጆች ያለው አልነበረም።+ 28 እነሱ የኖሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ቤርሳቤህ፣+ ሞላዳ፣+ ሃጻርሹአል፣+ 29 ባላ፣ ኤጼም፣+ ቶላድ፣ 30 ባቱኤል፣+ ሆርማ፣+ ጺቅላግ፣+ 31 ቤትማርካቦት፣ ሃጻርሱሲም፣+ ቤትቢርኢ እና ሻአራይም። ዳዊት እስከ ነገሠበት ጊዜ ድረስ በእነዚህ ከተሞች ይኖሩ ነበር።
32 ሰፈሮቻቸው ኤጣም፣ አይን፣ ሪሞን፣ ቶከን እና አሻን+ ሲሆኑ በአጠቃላይ አምስት ከተሞች ነበሩ፤ 33 በእነዚህም ከተሞች ዙሪያ ያሉት ሰፈሮቻቸው እስከ ባአል ድረስ ይደርሱ ነበር። የትውልድ መዝገባቸውና የመኖሪያ ቦታዎቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። 34 በተጨማሪም መሾባብ፣ ያምሌክ፣ የአሜስያስ ልጅ ዮሻ፣ 35 ኢዩኤል፣ የአሲዔል ልጅ፣ የሰራያህ ልጅ፣ የዮሽቢያህ ልጅ ኢዩ፣ 36 ኤሊዮዔናይ፣ ያዕቆባ፣ የሾሃያህ፣ አሳያህ፣ አዲዔል፣ የሲሚኤል፣ በናያህ፣ 37 የሸማያህ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፣ የየዳያህ ልጅ፣ የአሎን ልጅ፣ የሺፊ ልጅ ዚዛ፤ 38 እነዚህ በስም የተዘረዘሩት ሰዎች የየቤተሰቦቻቸው አለቆች ናቸው፤ የወገኖቻቸውም ቁጥር እየበዛ ሄደ። 39 እነሱም ለመንጎቻቸው የግጦሽ መሬት ለማግኘት እስከ ጌዶር መግቢያ፣ በሸለቆው በስተ ምሥራቅ በኩል እስካለው ስፍራ ድረስ ሄዱ። 40 በመጨረሻም ለም የሆነ ጥሩ የግጦሽ መሬት አገኙ፤ ምድሪቱም እጅግ ሰፊ እንዲሁም ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚያ የሚኖሩት የካም+ ዝርያዎች ነበሩ። 41 እነዚህ በስም የተዘረዘሩት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ+ ዘመን መጥተው የካም ዝርያዎችን ድንኳንና በዚያ ይኖሩ የነበሩትን መኡኒማውያንን መቱ። ፈጽመውም አጠፏቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ ደብዛቸው የለም፤ በዚያ ለመንጎቻቸው የሚሆን የግጦሽ መሬት ስለነበር በእነሱ ቦታ ላይ ሰፈሩ።
42 ከስምዖናውያን መካከል የተወሰኑት ይኸውም 500 ወንዶች በይሽኢ ወንዶች ልጆች በጰላጥያህ፣ በነአርያህ፣ በረፋያህ እና በዑዚኤል መሪነት ወደ ሴይር+ ተራራ ወጡ። 43 እነሱም ከአማሌቃውያን+ መካከል አምልጠው የቀሩትን ሰዎች መቱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይኖራሉ።
5 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሆነው የሮቤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሱ በኩር ቢሆንም እንኳ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ+ የብኩርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ+ ወንዶች ልጆች ተሰጠ፤ ከዚህም የተነሳ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የብኩርና መብት እንዳለው ተደርጎ አልተመዘገበም። 2 ይሁዳ+ ከወንድሞቹ የሚበልጥ ከመሆኑም ሌላ መሪ+ የሚሆነው የተገኘው ከእሱ ነው፤ ሆኖም የብኩርና መብቱን ያገኘው ዮሴፍ ነበር። 3 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ+ ነበሩ። 4 ሸማያህ የኢዩኤል ልጅ ነበር፤ የሸማያህ ልጅ ጎግ፣ የጎግ ልጅ ሺምአይ፣ 5 የሺምአይ ልጅ ሚክያስ፣ የሚክያስ ልጅ ረአያህ፣ የረአያህ ልጅ ባአል፣ 6 የባአል ልጅ ቤኤራህ ነበር፤ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ የሮቤላውያን አለቃ የሆነውን ቤኤራህን በግዞት ወሰደው። 7 ወንድሞቹ በየቤተሰቦቻቸውና በየዘር ሐረጋቸው ሲዘረዘሩ እንደሚከተለው ነው፦ መሪ የሆነው የኢዔል፣ ዘካርያስ፣ 8 የኢዩኤል ልጅ፣ የሼማ ልጅ፣ የአዛዝ ልጅ ቤላ፤ እሱ ከአሮዔር+ አንስቶ እስከ ነቦ እንዲሁም እስከ በዓልመዖን+ ድረስ ይኖር ነበር። 9 መንጎቻቸው በጊልያድ ምድር+ እጅግ በዝተው ስለነበር በስተ ምሥራቅ በኤፍራጥስ ወንዝ+ በኩል እስካለው፣ ምድረ በዳው እስከሚጀምርበት ቦታ ድረስ ሰፈረ። 10 በሳኦል ዘመን በአጋራውያን ላይ ጦርነት ከፍተው ድል መቷቸው፤ በመሆኑም ከጊልያድ በስተ ምሥራቅ ባለው ክልል ሁሉ በድንኳኖቻቸው ውስጥ ኖሩ።
11 ከእነሱ ጋር የሚዋሰኑት የጋድ ዘሮች ደግሞ ከባሳን አንስቶ እስከ ሳልካ+ ባለው ምድር ላይ ኖሩ። 12 ኢዩኤል መሪ ነበር፤ ሁለተኛው ሻፋም ሲሆን ያናይ እና ሻፋጥ ደግሞ በባሳን መሪዎች ነበሩ። 13 ከአባቶቻቸው ቤት የሆኑት ወንድሞቻቸውም ሚካኤል፣ መሹላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዚአ እና ኤቤር ሲሆኑ በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ። 14 እነዚህ የቡዝ ልጅ፣ የያህዶ ልጅ፣ የየሺሻይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የያሮሃ ልጅ፣ የሁሪ ልጅ፣ የአቢሃይል ወንዶች ልጆች ነበሩ። 15 የአባቶቻቸው ቤት መሪ የጉኒ ልጅ፣ የአብዲዔል ልጅ አሂ ነበር። 16 እነሱም በጊልያድ፣+ በባሳን፣+ በእነሱ ሥር* ባሉት ከተሞች እንዲሁም በሳሮን የግጦሽ መሬቶች ሁሉ እስከ ዳርቻዎቻቸው ድረስ ተቀመጡ። 17 እነዚህ ሁሉ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓታም+ እና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም*+ ዘመን በትውልድ መዝገቡ ላይ ሰፈሩ።
18 ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ 44,760 ኃያላን ተዋጊዎችን ያቀፈ ሠራዊት ነበራቸው፤ እነሱም ጋሻና ሰይፍ የታጠቁ፣ ደጋን ያነገቡና* ለውጊያ የሠለጠኑ ነበሩ። 19 እነዚህ ተዋጊዎች በአጋራውያን፣+ በየጡር፣ በናፊሽ+ እና በኖዳብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። 20 በጦርነቱ ወቅት አምላክ እንዲረዳቸው ስለጠየቁ እንዲሁም በእሱ ስለታመኑና+ እሱም ልመናቸውን ስለሰማ ከእነሱ ጋር በሚዋጉበት ጊዜ እርዳታ አገኙ፤ በመሆኑም አጋራውያንና ከእነሱ ጋር የነበሩት ሁሉ እጃቸው ላይ ወደቁ። 21 እነሱም መንጎቻቸውን ይኸውም 50,000 ግመሎች፣ 250,000 በጎችና 2,000 አህዮች እንዲሁም 100,000 ሰዎች* ማረኩ። 22 የተዋጋላቸው እውነተኛው አምላክ ስለነበር+ ተገድለው የወደቁት ብዙ ነበሩ። በግዞት+ እስከተወሰዱበትም ጊዜ ድረስ በእነሱ ቦታ ላይ ኖሩ።
23 የምናሴ ነገድ እኩሌታ+ ዘሮች ከባሳን እስከ በዓልሄርሞን፣ እስከ ሰኒር እንዲሁም እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ባለው ምድር ላይ ኖሩ። ቁጥራቸውም እጅግ ብዙ ነበር። 24 የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች እነዚህ ነበሩ፦ ኤፌር፣ ይሽኢ፣ ኤሊዔል፣ አዝርዔል፣ ኤርምያስ፣ ሆዳውያህ እና ያህዲኤል፤ እነዚህ ሰዎች ኃያላን ተዋጊዎችና ስመ ገናና ሲሆኑ የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ። 25 ሆኖም ለአባቶቻቸው አምላክ ታማኞች ሳይሆኑ ቀሩ፤ ደግሞም አምላክ ከፊታቸው ካጠፋቸው ከምድሪቱ ሕዝቦች አማልክት ጋር አመነዘሩ።+ 26 በመሆኑም የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፑልን መንፈስ አነሳሳ+ (የአሦርን ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን+ መንፈስ ማለት ነው)፤ እሱም ሮቤላውያንን፣ ጋዳውያንንና የምናሴ ነገድ እኩሌታን በግዞት ወደ ሃላህ፣ ወደ ሃቦር፣ ወደ ሃራ እና ወደ ጎዛን+ ወንዝ ወሰዳቸው፤ እስከ ዛሬም በዚያ ይገኛሉ።
6 የሌዊ+ ወንዶች ልጆች ጌድሶን፣ ቀአት+ እና ሜራሪ+ ነበሩ። 2 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣+ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ነበሩ። 3 የአምራም+ልጆች* አሮን፣+ ሙሴ+ እና ሚርያም+ ነበሩ። የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብ፣ አቢሁ፣+ አልዓዛር+ እና ኢታምር+ ነበሩ። 4 አልዓዛር ፊንሃስን+ ወለደ፤ ፊንሃስ አቢሹዓን ወለደ። 5 አቢሹዓ ቡቂን ወለደ፤ ቡቂ ዑዚን ወለደ። 6 ዑዚ ዘራህያህን ወለደ፤ ዘራህያህ መራዮትን ወለደ። 7 መራዮት አማርያህን ወለደ፤ አማርያህ አኪጡብን+ ወለደ። 8 አኪጡብ ሳዶቅን+ ወለደ፤ ሳዶቅ አኪማዓስን+ ወለደ። 9 አኪማዓስ አዛርያስን ወለደ፤ አዛርያስ ዮሃናንን ወለደ። 10 ዮሃናን አዛርያስን ወለደ። እሱም ሰለሞን በኢየሩሳሌም በገነባው ቤት ውስጥ ካህን ሆኖ ያገለግል ነበር።
11 አዛርያስ አማርያህን ወለደ፤ አማርያህ አኪጡብን ወለደ። 12 አኪጡብ ሳዶቅን+ ወለደ፤ ሳዶቅ ሻሉምን ወለደ። 13 ሻሉም ኬልቅያስን+ ወለደ፤ ኬልቅያስ አዛርያስን ወለደ። 14 አዛርያስ ሰራያህን+ ወለደ፤ ሰራያህ የሆጼዴቅን+ ወለደ። 15 ይሖዋ፣ ይሁዳና ኢየሩሳሌም በናቡከደነጾር እጅ በግዞት እንዲወሰዱ ሲያደርግ የሆጼዴቅም በግዞት ተወሰደ።
16 የሌዊ ወንዶች ልጆች ጌርሳም፣* ቀአት እና ሜራሪ ነበሩ። 17 የጌርሳም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ሊብኒ እና ሺምአይ።+ 18 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ነበሩ። 19 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ።
የሌዋውያን ቤተሰቦች በየአባቶቻቸው ስም ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው፦+ 20 ጌርሳም፣+ የጌርሳም ልጅ ሊብኒ፣ የሊብኒ ልጅ ያሃት፣ የያሃት ልጅ ዚማ፣ 21 የዚማ ልጅ ዮአህ፣ የዮአህ ልጅ ኢዶ፣ የኢዶ ልጅ ዛራ፣ የዛራ ልጅ የአትራይ። 22 የቀአት ወንዶች ልጆች፦* አሚናዳብ፣ የአሚናዳብ ልጅ ቆሬ፣+ የቆሬ ልጅ አሲር፣ 23 የአሲር ልጅ ሕልቃና፣ የሕልቃና ልጅ ኤቢያሳፍ፣+ የኤቢያሳፍ ልጅ አሲር፤ 24 የአሲር ልጅ ታሃት፣ የታሃት ልጅ ዑሪኤል፣ የዑሪኤል ልጅ ዖዝያ፣ የዖዝያ ልጅ ሻኡል። 25 የሕልቃና ወንዶች ልጆች አማሳይ እና አሂሞት ነበሩ። 26 ጾፋይ የሕልቃና ልጅ ነበር፤ የጾፋይ ልጅ ናሃት፣ 27 የናሃት ልጅ ኤልያብ፣ የኤልያብ ልጅ የሮሃም እና የየሮሃም ልጅ ሕልቃና+ ነበር። 28 የሳሙኤል+ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ኢዩኤልና ሁለተኛው አቢያህ+ ነበሩ። 29 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፦* ማህሊ፣+ የማህሊ ልጅ ሊብኒ፣ የሊብኒ ልጅ ሺምአይ፣ የሺምአይ ልጅ ዖዛ፣ 30 የዖዛ ልጅ ሺምአ፣ የሺምአ ልጅ ሃጊያህ፣ የሃጊያህ ልጅ አሳያህ።
31 ዳዊት፣ ታቦቱ በይሖዋ ቤት ከተቀመጠ በኋላ በዚያ የሚዘመረውን መዝሙር እንዲመሩ የሾማቸው እነዚህ ነበሩ።+ 32 እነሱ ሰለሞን የይሖዋን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪገነባ+ ድረስ በማደሪያ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ከመዝሙር ጋር የተያያዘ ኃላፊነት ተሰጣቸው፤ በተሰጣቸውም ኃላፊነት መሠረት አገልግሎታቸውን ያከናውኑ ነበር።+ 33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር አብረው የሚያገለግሉት ሰዎች እነዚህ ነበሩ፦ ከቀአታውያን መካከል ዘማሪው ሄማን፣+ የኢዩኤል+ ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣ 34 የሕልቃና+ ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ፣ የኤሊዔል ልጅ፣ የቶአ ልጅ፣ 35 የጹፍ ልጅ፣ የሕልቃና ልጅ፣ የማሃት ልጅ፣ የአማሳይ ልጅ፣ 36 የሕልቃና ልጅ፣ የኢዩኤል ልጅ፣ የአዛርያስ ልጅ፣ የሶፎንያስ ልጅ፣ 37 የታሃት ልጅ፣ የአሲር ልጅ፣ የኤቢያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ፣ 38 የይጽሃር ልጅ፣ የቀአት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የእስራኤል ልጅ ነበር።
39 ወንድሙ አሳፍ+ በቀኙ በኩል ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የቤራክያህ ልጅ፣ የሺምአ ልጅ፣ 40 የሚካኤል ልጅ፣ የባአሴያህ ልጅ፣ የማልኪያህ ልጅ፣ 41 የኤትኒ ልጅ፣ የዛራ ልጅ፣ የአዳያህ ልጅ፣ 42 የኤታን ልጅ፣ የዚማ ልጅ፣ የሺምአይ ልጅ፣ 43 የያሃት ልጅ፣ የጌርሳም ልጅ፣ የሌዊ ልጅ ነበር።
44 ወንድሞቻቸው የሆኑት የሜራሪ+ ዘሮች በስተ ግራ የነበሩ ሲሆን ኤታን+ በዚያ ነበር፤ እሱም የቂሺ ልጅ፣ የአብዲ ልጅ፣ የማሉክ ልጅ፣ 45 የሃሻብያህ ልጅ፣ የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣ 46 የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣ የሼሜር ልጅ፣ 47 የማህሊ ልጅ፣ የሙሺ ልጅ፣ የሜራሪ ልጅ፣ የሌዊ ልጅ ነበር።
48 ሌዋውያን ወንድሞቻቸው በእውነተኛው አምላክ ቤት፣ በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ ሁሉንም አገልግሎት እንዲያከናውኑ ተሹመው ነበር።*+ 49 አሮንና ወንዶች ልጆቹ+ የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች ጋር የተያያዙትን ሥራዎች በማከናወን ለእስራኤል ቤት ለማስተሰረይ፣+ የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያና+ በዕጣን መሠዊያው+ ላይ የሚጨስ መሥዋዕት አቀረቡ። 50 የአሮን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፦+ የአሮን ልጅ አልዓዛር፣+ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ፣ የፊንሃስ ልጅ አቢሹዓ፣ 51 የአቢሹዓ ልጅ ቡቂ፣ የቡቂ ልጅ ዑዚ፣ የዑዚ ልጅ ዘራህያህ፣ 52 የዘራህያህ ልጅ መራዮት፣ የመራዮት ልጅ አማርያህ፣ የአማርያህ ልጅ አኪጡብ፣+ 53 የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅ፣+ የሳዶቅ ልጅ አኪማዓስ።
54 በክልላቸው ውስጥ በሰፈሮቻቸው* የሚገኙት የመኖሪያ ቦታዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፦ የቀአታውያን ቤተሰብ የሆኑት የአሮን ዘሮች የመጀመሪያው ዕጣ ደረሳቸው፤ 55 በይሁዳ ምድር የምትገኘውን ኬብሮንን+ በዙሪያዋ ካሉት የግጦሽ መሬቶች ጋር ሰጧቸው። 56 ይሁንና የከተማዋን እርሻና ሰፈሮቿን ለየፎኒ ልጅ ለካሌብ+ ሰጡ። 57 ለአሮንም ዘሮች የመማጸኛ ከተሞችን፣*+ ኬብሮንን+ እንዲሁም ሊብናንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ያቲርን፣+ ኤሽተሞዓንና የግጦሽ መሬቶቿን ሰጡ፤+ 58 ሂሌንንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ደቢርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ 59 አሻንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ቤትሼሜሽንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጡ፤ 60 ከቢንያም ነገድም ጌባና+ የግጦሽ መሬቶቿ፣ አለሜትና የግጦሽ መሬቶቿ እንዲሁም አናቶትና+ የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጣቸው። ለወገኖቻቸው የተሰጡት ከተሞቻቸው በአጠቃላይ 13 ከተሞች ነበሩ።+
61 ለቀሩት ቀአታውያን ከሌላው ነገድ ቤተሰብና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ+ ላይ አሥር ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው።
62 ለጌርሳማውያን በየቤተሰቦቻቸው ከይሳኮር ነገድ፣ ከአሴር ነገድ፣ ከንፍታሌም ነገድና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ 13 ከተሞች መደቡላቸው።+
63 ለሜራራውያን በየቤተሰቦቻቸው ከሮቤል ነገድ፣ ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድ 12 ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው።+
64 በዚህ መንገድ እስራኤላውያን ለሌዋውያኑ እነዚህን ከተሞች ከነግጦሽ መሬታቸው ሰጧቸው።+ 65 በተጨማሪም ከይሁዳ ነገድ፣ ከስምዖን ነገድና ከቢንያም ነገድ በስማቸው የተጠቀሱትን እነዚህን ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው።
66 ከቀአታውያን ቤተሰቦች መካከል የተወሰኑት ከኤፍሬም ነገድ ያገኟቸው የራሳቸው የሆኑ ከተሞች ነበሯቸው።+ 67 እነሱም የመማጸኛ ከተሞቹን፣* ተራራማ በሆነው የኤፍሬም ምድር ያለችውን ሴኬምንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ጌዜርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው፤ 68 ዮቅመአምንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ቤትሆሮንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ 69 አይሎንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ጋትሪሞንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው፤ 70 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ ደግሞ አኔርንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ቢልአምንና የግጦሽ መሬቶቿን ለቀሩት የቀአታውያን ቤተሰቦች ሰጧቸው።
71 ለጌርሳማውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን የምትገኘውን ጎላንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም አስታሮትንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤+ 72 ከይሳኮር ነገድም ቃዴሽንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ዳብራትንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣+ 73 ራሞትንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም አኔምንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ 74 ከአሴር ነገድም ማሻልንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ አብዶንንና የግጦሽ መሬቶቿን፣+ 75 ሁቆቅንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ሬሆብንና+ የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ 76 ከንፍታሌም ነገድም በገሊላ+ የምትገኘውን ቃዴሽንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ ሃሞንንና የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ቂርያታይምንና የግጦሽ መሬቶቿን ሰጧቸው።
77 ለቀሩት ሜራራውያን ከዛብሎን+ ነገድ ላይ ሪሞኖንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ታቦርንና የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው፤ 78 ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፣ በኢያሪኮ ካለው የዮርዳኖስ አካባቢ ከሮቤል ነገድ ላይ በምድረ በዳ የምትገኘው ቤጼርና የግጦሽ መሬቶቿ፣ ያሃጽና+ የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጧቸው፤ 79 ደግሞም ቀደሞትና+ የግጦሽ መሬቶቿ እንዲሁም መፋአትና የግጦሽ መሬቶቿ ተሰጧቸው፤ 80 ከጋድ ነገድ ላይ ደግሞ በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትንና የግጦሽ መሬቶቿን፣ ማሃናይምንና+ የግጦሽ መሬቶቿን፣ 81 ሃሽቦንንና+ የግጦሽ መሬቶቿን እንዲሁም ያዜርንና+ የግጦሽ መሬቶቿን መደቡላቸው።
7 የይሳኮር ወንዶች ልጆች ቶላ፣ ፑሃ፣ ያሹብና ሺምሮን+ ሲሆኑ በአጠቃላይ አራት ነበሩ። 2 የቶላም ወንዶች ልጆች ዑዚ፣ ረፋያህ፣ የሪኤል፣ ያህማይ፣ ይብሳም እና ሸሙኤል ሲሆኑ የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ። የቶላ ዘሮች ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቁጥራቸው 22,600 ነበር። 3 የዑዚ ዘሮች* ይዝራህያህ እና የይዝራህያህ ወንዶች ልጆች ይኸውም ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤልና ይሽሺያህ ናቸው፤ አምስቱም አለቆች* ነበሩ። 4 እነሱም ብዙ ሚስቶችና ወንዶች ልጆች ስለነበሯቸው በየትውልድ ሐረጋቸው ከየአባቶቻቸው ቤት ለመዋጋት ዝግጁ የሆኑ 36,000 ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ነበራቸው። 5 ከይሳኮር ቤተሰቦች በሙሉ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የሰፈሩት ኃያላን ተዋጊዎች የሆኑት ወንድሞቻቸው በአጠቃላይ 87,000 ነበሩ።+
6 የቢንያም+ ወንዶች ልጆች ቤላ፣+ ቤኬር+ እና የዲአዔል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። 7 የቤላ ወንዶች ልጆች ኤጽቦን፣ ዑዚ፣ ዑዚኤል፣ የሪሞት እና ኢሪ ሲሆኑ በአጠቃላይ አምስት ነበሩ፤ እነሱም የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች እንዲሁም ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ፤ በትውልድ ሐረግ መዝገቡም ላይ የሰፈሩት 22,034 ነበሩ።+ 8 የቤኬር ወንዶች ልጆች ዘሚራ፣ ኢዮአስ፣ ኤሊዔዘር፣ ኤሊዮዔናይ፣ ኦምሪ፣ የሬሞት፣ አቢያህ፣ አናቶት እና አለሜት ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ወንዶች ልጆች ናቸው። 9 በየትውልድ ሐረጋቸውና በየዘሮቻቸው የተመዘገቡት በየአባቶቻቸው ቤት ያሉት መሪዎች 20,200 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ። 10 የየዲአዔል+ ወንዶች ልጆች ቢልሃን እና የቢልሃን ወንዶች ልጆች ይኸውም የኡሽ፣ ቢንያም፣ ኤሁድ፣ ኬናአና፣ ዜታን፣ ተርሴስ እና አሂሻሐር ነበሩ። 11 እነዚህ ሁሉ የየዲአዔል ወንዶች ልጆች ሲሆኑ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች እንዲሁም ሠራዊቱን ተቀላቅለው ለመዋጋት ዝግጁ የሆኑ 17,200 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ።
12 የሹፒምና የሁፒም ቤተሰቦች* የኢር+ ልጆች ነበሩ፤ የሁሺም ልጆች ደግሞ የአሄር ዘሮች ነበሩ።
13 የንፍታሌም ወንዶች ልጆች+ ያህጺኤል፣ ጉኒ፣ የጼር እና ሻሉም ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች የባላ+ ዘሮች* ነበሩ።
14 የምናሴ ልጆች፦+ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት አስሪዔል። (እሷ የጊልያድን አባት ማኪርን+ ወለደች። 15 ማኪር፣ ሁፒምንና ሹፒምን ሚስት አጋባቸው፤ የእህቱም ስም ማአካ ይባላል።) ሁለተኛው ሰለጰአድ+ ተብሎ ይጠራል፤ ሆኖም ሰለጰአድ የወለደው ሴት ልጆችን ብቻ ነበር።+ 16 የማኪር ሚስት ማአካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፔሬሽ አለችው፤ የወንድሙም ስም ሼሬሽ ይባል ነበር፤ ወንዶች ልጆቹም ዑላም እና ራቄም ነበሩ። 17 የዑላም ልጅ* ቤዳን ነበር። እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ የጊልያድ ዘሮች ነበሩ። 18 እህቱም ሞሌኬት ትባል ነበር። እሷም ኢሽሆድን፣ አቢዔዜርንና ማህላን ወለደች። 19 የሸሚዳ ወንዶች ልጆችም አሂያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሂ እና አኒዓም ነበሩ።
20 ሹተላ የኤፍሬም+ ልጅ ነበር፤ የሹተላ+ ልጅ ቤሬድ፣ የቤሬድ ልጅ ታሃት፣ የታሃት ልጅ ኤልዓዳ፣ የኤልዓዳ ልጅ ታሃት፣ 21 የታሃት ልጅ ዛባድ፣ የዛባድ ልጅ ሹተላ ነበር፤ ኤጼር እና ኤልዓድም የኤፍሬም ልጆች ነበሩ። እነሱም መንጎች ለመዝረፍ በወረዱ ጊዜ የምድሪቱ ተወላጆች የሆኑት የጌት+ ሰዎች ገደሏቸው። 22 አባታቸው ኤፍሬም ለብዙ ቀናት አለቀሰ፤ ወንድሞቹም እሱን ለማጽናናት ይመጡ ነበር። 23 ከዚያም ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ሆኖም እሷ በወለደች ጊዜ በቤተሰቡ ላይ መከራ ደርሶ ስለነበር ስሙን በሪአ* አለው። 24 የሴት ልጁም ስም ሼኢራ ሲሆን እሷም የታችኛውንና+ የላይኛውን ቤትሆሮንን+ እንዲሁም ዑዜንሼራን የገነባች ነች። 25 ሬፋህ እና ሬሼፍ ወንዶች ልጆቹ ነበሩ፤ ሬሼፍ ቴላህን ወለደ፤ ቴላህ ታሃንን ወለደ፤ 26 ታሃን ላዳንን ወለደ፤ ላዳን አሚሁድን ወለደ፤ አሚሁድ ኤሊሻማን ወለደ፤ 27 ኤሊሻማ ነዌን ወለደ፤ ነዌ ኢያሱን*+ ወለደ።
28 ርስታቸውና ሰፈራቸው ቤቴልንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ በስተ ምሥራቅ ናአራንን፣ በስተ ምዕራብ ደግሞ ጌዜርንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ሴኬምንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ጨምሮ እስከ አያህና* በሥሯ እስካሉት ከተሞች ይደርሳል፤ 29 በምናሴም ዘሮች ወሰን በኩል ቤትሼንና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ ታአናክና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ መጊዶና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች እንዲሁም ዶርና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች ነበሩ። በእነዚህ ስፍራዎች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር።
30 የአሴር ወንዶች ልጆች ይምናህ፣ ይሽዋ፣ ይሽዊ እና በሪአ+ ሲሆኑ እህታቸውም ሴራህ ትባላለች።+ 31 የበሪአ ወንዶች ልጆች ሄቤር እና የቢርዛይት አባት የሆነው ማልኪኤል ነበሩ። 32 ሄቤር ያፍሌጥን፣ ሾሜርን፣ ሆታምንና እህታቸውን ሹአን ወለደ። 33 የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች ፓሳክ፣ ቢምሃል እና አሽዋት ነበሩ። እነዚህ የያፍሌጥ ልጆች ነበሩ። 34 የሼሜር* ወንዶች ልጆች አሂ፣ ሮህጋ፣ የሁባ እና አራም ነበሩ። 35 የወንድሙ የሄሌም* ወንዶች ልጆች ጾፋ፣ ይምና፣ ሼሌሽ እና አማል ነበሩ። 36 የጾፋ ወንዶች ልጆች ሱአ፣ ሃርኔፌር፣ ሹአል፣ ቤሪ፣ ይምራ፣ 37 ቤጼር፣ ሆድ፣ ሻማ፣ ሺልሻ፣ ይትራን እና ቤኤራ ነበሩ። 38 የየቴር ወንዶች ልጆች የፎኒ፣ ፒስጳ እና አራ ነበሩ። 39 የዑላ ወንዶች ልጆች ኤራ፣ ሃኒኤል እና ሪጽያ ነበሩ። 40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ወንዶች ልጆችና የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ናቸው፤ እንዲሁም የተመረጡ ኃያላን ተዋጊዎች ሲሆኑ የሠራዊቱ አለቆች መሪዎች ነበሩ፤ ደግሞም በቤተሰባቸው መዝገብ ላይ እንደተጻፈው+ ለውጊያ ዝግጁ የሆኑ 26,000 ሰዎች+ በሠራዊቱ ውስጥ ይገኙ ነበር።
8 ቢንያም+ የበኩር ልጁን ቤላን፣+ ሁለተኛ ልጁን አሽቤልን፣+ ሦስተኛ ልጁን አሃራሕን፣ 2 አራተኛ ልጁን ኖሃንና አምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ። 3 የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ አዳር፣ ጌራ፣+ አቢሁድ፣ 4 አቢሹዓ፣ ንዕማን፣ አሆዓሕ፣ 5 ጌራ፣ ሼፉፋን እና ሁራም። 6 እነዚህ የኤሁድ ወንዶች ልጆች ይኸውም ወደ ማናሃት በግዞት የተወሰዱ በጌባ+ ይኖሩ የነበሩ ቤተሰቦች መሪዎች ናቸው፦ 7 ንዕማን፣ አኪያህ እና ጌራ፤ ሰዎቹን በዋነኝነት እየመራ ወደ ግዞት የወሰዳቸው ጌራ ነበር፤ እሱም ዑዛን እና አሂሑድን ወለደ። 8 ሻሃራይም ሰዎቹን ከሰደዳቸው በኋላ በሞዓብ ምድር* ልጆች ወለደ። ሁሺም እና ባዓራ ሚስቶቹ ነበሩ።* 9 ከሚስቱ ከሆዴሽ ዮባብን፣ ጺብያን፣ ሜሻን፣ ማልካምን፣ 10 የኡጽን፣ ሳክያህን እና ሚርማን ወለደ። እነዚህ ወንዶች ልጆቹ ሲሆኑ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ።
11 ከሁሺም አቢጡብን እና ኤልጳዓልን ወለደ። 12 የኤልጳዓል ወንዶች ልጆች ኤቤር፣ ሚሻም፣ ኦኖን+ እንዲሁም ሎድንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞች የቆረቆረው ሻሜድ፣ 13 በሪአ እና ሼማ ነበሩ። እነዚህ በአይሎን+ ይኖሩ የነበሩ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ናቸው። የጌትን ነዋሪዎች ያሳደዱት እነሱ ነበሩ። 14 ደግሞም አሂዮ፣ ሻሻቅ፣ የሬሞት፣ 15 ዘባድያህ፣ አራድ፣ ኤዴር፣ 16 ሚካኤል፣ ይሽጳ እና ዮሃ የበሪአ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ 17 ዘባድያህ፣ መሹላም፣ ሂዝቂ፣ ሄቤር፣ 18 ይሽመራይ፣ ይዝሊያ እና ዮባብ የኤልጳዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ 19 ያቂም፣ ዚክሪ፣ ዛብዲ፣ 20 ኤሊዔናይ፣ ጺለታይ፣ ኤሊዔል፣ 21 አዳያህ፣ ቤራያህ እና ሺምራት የሺምአይ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ 22 ይሽጳን፣ ኤቤር፣ ኤሊዔል፣ 23 አብዶን፣ ዚክሪ፣ ሃናን፣ 24 ሃናንያህ፣ ኤላም፣ አንቶቲያህ፣ 25 ይፍደያህ እና ጰኑኤል የሻሻቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ 26 ሻምሸራይ፣ ሸሃሪያህ፣ ጎቶልያ፣ 27 ያአሬሽያህ፣ ኤልያስ እና ዚክሪ የየሮሃም ወንዶች ልጆች ነበሩ። 28 እነዚህ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ተጽፎ በሚገኘው መሠረት የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ። የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበር።
29 የገባኦን አባት የኢዔል በገባኦን+ ይኖር ነበር። የሚስቱ ስም ማአካ ይባል ነበር።+ 30 የበኩር ልጁ አብዶን ሲሆን ሌሎቹ ልጆቹ ደግሞ ጹር፣ ቂስ፣ ባአል፣ ናዳብ፣ 31 ጌዶር፣ አሂዮ እና ዛከር ነበሩ። 32 ሚቅሎት ሺምአህን ወለደ። እነዚህ ሁሉ ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር ሆነው በወንድሞቻቸው አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር።
33 ኔር+ ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን+ ወለደ፤ ሳኦል ዮናታንን፣+ ሜልኪሳን፣+ አቢናዳብን+ እና ኤሽባዓልን*+ ወለደ። 34 የዮናታን ልጅ መሪበኣል*+ ነበር። መሪበኣል ሚክያስን ወለደ።+ 35 የሚክያስ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬአ እና አካዝ ነበሩ። 36 አካዝ የሆአዳን ወለደ፤ የሆአዳ አለሜትን፣ አዝማዌትን እና ዚምሪን ወለደ፤ ዚምሪ ሞጻን ወለደ። 37 ሞጻ ቢንአን ወለደ፤ ቢንአ ራፋህን ወለደ፤ ራፋህ ኤልዓሳን ወለደ፤ ኤልዓሳ አዜልን ወለደ። 38 አዜል ስድስት ወንዶች ልጆች የነበሩት ሲሆን ስማቸውም አዝሪቃም፣ ቦከሩ፣ እስማኤል፣ ሸአርያህ፣ አብድዩ እና ሃናን ነበር። እነዚህ ሁሉ የአዜል ወንዶች ልጆች ነበሩ። 39 የወንድሙ የኤሼቅ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ዑላም፣ ሁለተኛው ልጁ የኡሽ፣ ሦስተኛው ልጁ ኤሊፌሌት ነበሩ። 40 የዑላም ወንዶች ልጆች ቀስተኞችና* ኃያላን ተዋጊዎች የነበሩ ሲሆን 150 ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯቸው። እነዚህ ሁሉ የቢንያም ዘሮች ነበሩ።
9 እስራኤላውያን በሙሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተመዘገቡ፤ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍም ላይ ተጻፉ። ይሁዳም ታማኝ ሆኖ ስላልተገኘ ወደ ባቢሎን በግዞት ተወሰደ።+ 2 በከተሞቻቸው ወደሚገኙት ርስቶቻቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች አንዳንድ እስራኤላውያን፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች* ነበሩ።+ 3 የተወሰኑ የይሁዳ፣+ የቢንያም፣+ የኤፍሬምና የምናሴ ዘሮች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፦ 4 ከይሁዳ ልጅ፣ ከፋሬስ+ ዘሮች መካከል የባኒ ልጅ፣ የኢምሪ ልጅ፣ የኦምሪ ልጅ፣ የአሚሁድ ልጅ ዑታይ። 5 ከሴሎናውያንም የበኩር ልጅ የሆነው አሳያህ እና ወንዶች ልጆቹ። 6 ከዛራ ልጆች+ መካከል ደግሞ፣ የኡዔል እና 690 ወንድሞቻቸው ነበሩ።
7 በዚያ የተቀመጡት የቢንያም ዘሮችም የሚከተሉት ናቸው፦ የሃስኑአ ልጅ፣ የሆዳውያህ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ ሳሉ፤ 8 የየሮሃም ልጅ ይብኔያህ፣ የሚክሪ ልጅ፣ የዑዚ ልጅ ኤላህ፣ የይብኒያህ ልጅ፣ የረኡዔል ልጅ፣ የሰፋጥያህ ልጅ መሹላም። 9 በዘር ሐረጉ መዝገብ ላይ የሰፈሩት ወንድሞቻቸውም 956 ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ወንዶች በየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ።*
10 ከካህናቱም የዳያህ፣ የሆያሪብ፣ ያኪን፣+ 11 የእውነተኛው አምላክ ቤት* መሪ የሆነው የአኪጡብ ልጅ፣ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ፣ የመሹላም ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ አዛርያስ፣ 12 የማልኪያህ ልጅ፣ የጳስኮር ልጅ፣ የየሮሃም ልጅ አዳያህ፣ የኢሜር ልጅ፣ የመሺሌሚት ልጅ፣ የመሹላም ልጅ፣ የያህዜራ ልጅ፣ የአዲዔል ልጅ ማአሳይ፣ 13 እንዲሁም የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑት ወንድሞቻቸው ነበሩ፤ እነሱም 1,760 ሲሆኑ ለእውነተኛው አምላክ ቤት አገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ኃያላንና ብቁ ሰዎች ነበሩ።
14 ከሌዋውያኑም ከሜራሪ ዘሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃሻብያህ ልጅ፣ የአዝሪቃም ልጅ፣ የሃሹብ ልጅ ሸማያህ፣+ 15 ባቅባቃር፣ ሄሬሽ፣ ጋላል፣ የአሳፍ ልጅ፣ የዚክሪ ልጅ፣ የሚካ ልጅ ማታንያህ፣ 16 የየዱቱን ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሸማያህ ልጅ አብድዩ እንዲሁም የሕልቃና ልጅ፣ የአሳ ልጅ ቤራክያህ። እሱም በነጦፋውያን+ ሰፈር ይኖር ነበር።
17 በር ጠባቂዎቹ+ ሻሉም፣ አቁብ፣ ታልሞን እና አሂማን ነበሩ፤ ወንድማቸው ሻሉምም መሪ ነበር፤ 18 እሱም እስከዚያን ጊዜ ድረስ በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በንጉሡ በር ላይ ነበር።+ እነዚህ የሌዋውያንን ሰፈሮች የሚጠብቁ በር ጠባቂዎች ነበሩ። 19 የቆሬ ልጅ፣ የኤቢያሳፍ ልጅ፣ የቆረ ልጅ ሻሉም እና የአባቱ ቤት ወገን የሆኑት ወንድሞቹ ቆሬያውያን የድንኳኑ በር ጠባቂዎች በመሆን በዚያ የሚከናወነውን አገልግሎት በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር፤ አባቶቻቸው ደግሞ የመግቢያው ጠባቂዎች በመሆን የይሖዋን ሰፈር በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር። 20 ከዚህ በፊት የእነሱ መሪ የነበረው የአልዓዛር+ ልጅ ፊንሃስ+ ሲሆን ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር። 21 የመሺሌሚያህ ልጅ ዘካርያስ+ የመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በር ጠባቂ ነበር።
22 በደጆቹ ላይ ቆመው እንዲጠብቁ የተመረጡት በአጠቃላይ 212 ነበሩ። እነሱም በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ተጽፎ በሚገኘው መሠረት+ በሰፈሮቻቸው ውስጥ ይኖሩ ነበር። ዳዊትና ባለ ራእዩ+ ሳሙኤል እነዚህን ሰዎች ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ሾሟቸው። 23 እነሱና ወንዶች ልጆቻቸው የይሖዋን ቤት ይኸውም የማደሪያ ድንኳኑን* በሮች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ 24 በር ጠባቂዎቹ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ በኩል ነበሩ።+ 25 በየሰፈሮቻቸው የሚኖሩት ወንድሞቻቸው ለሰባት ቀናት አብረዋቸው ለማገልገል አልፎ አልፎ ይመጡ ነበር። 26 ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ የሚያገለግሉ አራት የበር ጠባቂ አለቆች* ነበሩ። እነሱም ሌዋውያን ሲሆኑ በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚገኙትን ክፍሎችና* ግምጃ ቤቶች የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።+ 27 በእውነተኛው አምላክ ቤት ዙሪያ በተመደቡበት ቦታ ላይ ሆነው ያድሩ ነበር፤ የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እንዲሁም ቁልፉ የተሰጣቸውና ቤቱን በየጠዋቱ የሚከፍቱት እነሱ ነበሩ።
28 ከእነሱ መካከል የተወሰኑት ለአገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች የመቆጣጠር ኃላፊነት ነበረባቸው፤+ እነሱም ዕቃዎቹን በሚያስገቡበትም ሆነ በሚያወጡበት ጊዜ ይቆጥሯቸው ነበር። 29 የተወሰኑት ደግሞ ሌሎቹን ዕቃዎች፣ ቅዱስ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ፣+ የላመውን ዱቄት፣+ የወይን ጠጁን፣+ ዘይቱን፣+ ነጭ ዕጣኑንና+ የበለሳን ዘይቱን+ እንዲቆጣጠሩ ተሹመው ነበር። 30 ከካህናቱ ልጆች መካከል አንዳንዶቹ የበለሳን ዘይት የተቀላቀለበት ቅባት ያዘጋጁ ነበር። 31 የቆሬያዊው የሻሉም የበኩር ልጅ የሆነው ሌዋዊው ማቲትያህ በምጣድ ላይ ከሚጋገሩት ነገሮች+ ጋር በተያያዘ ታማኝነት በሚጠይቀው ቦታ ላይ ተመድቦ ነበር። 32 ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከቀዓታውያን አንዳንዶቹ የሚነባበረውን ዳቦ*+ በየሰንበቱ የማዘጋጀት+ ኃላፊነት ነበራቸው።
33 እነዚህ የሌዋውያን አባቶች ቤት መሪዎች የሆኑ ዘማሪዎች ነበሩ፤ ከሌሎች ሥራዎች ነፃ እንዲሆኑ የተደረጉት እነዚህ ሰዎች በክፍሎቹ* ውስጥ ይቀመጡ ነበር። ምክንያቱም ቀንም ሆነ ሌሊት በሥራቸው ላይ የመገኘት ኃላፊነት ነበረባቸው። 34 እነዚህ በትውልድ ሐረጉ መዝገብ ላይ እንደሰፈረው የሌዋውያን ቤተሰቦች መሪዎች ነበሩ። የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበር።
35 የገባኦን አባት የኢዔል በገባኦን+ ይኖር ነበር። የሚስቱ ስም ማአካ ይባል ነበር። 36 የበኩር ልጁ አብዶን ሲሆን ሌሎቹ ልጆቹ ደግሞ ጹር፣ ቂስ፣ ባአል፣ ኔር፣ ናዳብ፣ 37 ጌዶር፣ አሂዮ፣ ዘካርያስ እና ሚቅሎት ነበሩ። 38 ሚቅሎት ሺምአምን ወለደ። እነዚህ ሁሉ ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር ሆነው በወንድሞቻቸው አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። 39 ኔር+ ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን+ ወለደ፤ ሳኦል ዮናታንን፣+ ሜልኪሳን፣+ አቢናዳብን+ እና ኤሽባዓልን ወለደ። 40 የዮናታን ልጅ መሪበኣል+ ነበር። መሪበኣል ሚክያስን ወለደ።+ 41 የሚክያስ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታህሬአ እና አካዝ ነበሩ። 42 አካዝ ያራን ወለደ፤ ያራ አለሜትን፣ አዝማዌትንና ዚምሪን ወለደ። ዚምሪ ሞጻን ወለደ። 43 ሞጻ ቢንአን ወለደ፤ ቢንአ ረፋያህን ወለደ፤ ረፋያህ ኤልዓሳን ወለደ፤ ኤልዓሳ አዜልን ወለደ። 44 አዜል ስድስት ወንዶች ልጆች የነበሩት ሲሆን ስማቸውም አዝሪቃም፣ ቦከሩ፣ እስማኤል፣ ሸአርያህ፣ አብድዩ እና ሃናን ነበር። እነዚህ የአዜል ወንዶች ልጆች ነበሩ።
10 ፍልስጤማውያንም ከእስራኤል ጋር እየተዋጉ ነበር። የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦአ ተራራ ላይ ተገደሉ።+ 2 ፍልስጤማውያን ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን እግር በእግር ተከታተሏቸው፤ ፍልስጤማውያንም የሳኦልን ወንዶች ልጆች ዮናታንን፣ አቢናዳብንና ሜልኪሳን+ መተው ገደሏቸው። 3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታ፤ ቀስተኞቹም አገኙት፤ ደግሞም አቆሰሉት።+ 4 ከዚያም ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን “እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው በጭካኔ እንዳያሠቃዩኝ*+ ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበር ፈቃደኛ አልሆነም። በመሆኑም ሳኦል ሰይፉን ወስዶ በላዩ ላይ ወድቆ ሞተ።+ 5 ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ሲያይ እሱም በራሱ ሰይፍ ላይ ወድቆ ሞተ። 6 ስለዚህ ሳኦልም ሆነ ሦስት ወንዶች ልጆቹ ሞቱ፤ የቤቱም ሰዎች ሁሉ አብረው ሞቱ።+ 7 በሸለቆው ውስጥ የነበሩት* የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ሠራዊቱ መሸሹን እንዲሁም ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ጥለው ሸሹ፤ ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው ከተሞቹን ያዙ።
8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።+ 9 ስለሆነም ሳኦልን ገፈፉት፤ ራሱን ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከወሰዱ በኋላ ወሬው ለጣዖቶቻቸውና+ ለሕዝቡ እንዲዳረስ ወደ ፍልስጤም ምድር ሁሉ መልእክት ላኩ። 10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአምላካቸው ቤት* አስቀመጡት፤ ራሱን ደግሞ በዳጎን ቤት+ ላይ ቸነከሩት።
11 በጊልያድ በምትገኘው በኢያቢስ+ የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ ፍልስጤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን ሁሉ ሲሰሙ+ 12 ተዋጊዎቹ ሁሉ ተነሱ፤ የሳኦልንና የልጆቹንም አስከሬን ተሸክመው ወደ ኢያቢስ አመጡ። ከዚያም አፅማቸውን በኢያቢስ በሚገኝ ትልቅ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤+ ለሰባት ቀንም ጾሙ።
13 ስለዚህ ሳኦል ለይሖዋ ታማኝ ሳይሆን በመቅረቱ ሞተ፤ ምክንያቱም የይሖዋን ቃል አልታዘዘም፤+ ደግሞም መናፍስት ጠሪን አማከረ፤+ 14 ይሖዋንም አልጠየቀም። ስለሆነም ለሞት አሳልፎ ሰጠው፤ ንግሥናውም ለእሴይ ልጅ ለዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።+
11 ከጊዜ በኋላ እስራኤላውያን በሙሉ በኬብሮን+ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ተሰብስበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ፣ የሥጋህም ቁራጭ ነን።*+ 2 ባለፉት ዘመናት ሳኦል ንጉሥ በነበረበት ጊዜ እስራኤል ወደ ጦርነት ሲወጣ የምትመራው* አንተ ነበርክ።+ አምላክህ ይሖዋም ‘ሕዝቤን እስራኤልን እረኛ ሆነህ ትጠብቃለህ፤ በሕዝቤ በእስራኤልም ላይ መሪ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”+ 3 በመሆኑም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ንጉሡ ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን ከእነሱ ጋር በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ። ከዚያም በሳሙኤል አማካኝነት በተነገረው የይሖዋ ቃል መሠረት+ ዳዊትን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ቀቡት።+
4 በኋላም ዳዊትና መላው እስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ኢያቡሳውያን+ ይኖሩበት ወደነበረው ምድር ወደ ኢያቡስ+ ሄዱ። 5 የኢያቡስ ነዋሪዎችም ዳዊትን “ፈጽሞ ወደዚህ አትገባም!” በማለት ተሳለቁበት።+ ይሁን እንጂ ዳዊት በአሁኑ ጊዜ የዳዊት ከተማ+ ተብላ የምትጠራውን የጽዮንን+ ምሽግ ያዘ። 6 ስለሆነም ዳዊት “ኢያቡሳውያንን በመጀመሪያ የሚመታ ሰው አለቃና* መኮንን ይሆናል” አለ። የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ+ በመጀመሪያ ወደዚያ ወጣ፤ እሱም አለቃ ሆነ። 7 ከዚያም ዳዊት በምሽጉ ውስጥ መኖር ጀመረ። ከዚህም የተነሳ ስፍራውን የዳዊት ከተማ አሉት። 8 እሱም ከጉብታው* አንስቶ በዙሪያው እስካሉት ቦታዎች ድረስ ከተማዋን ዙሪያዋን ገነባ፤ ኢዮዓብ ደግሞ ቀሪውን የከተማዋን ክፍል መልሶ ሠራ። 9 በዚህ ሁኔታ ዳዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ ሄደ፤+ የሠራዊት ጌታ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር።
10 የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እነሱም ከመላው የእስራኤል ሕዝብ ጋር ሆነው ይሖዋ ለእስራኤል ቃል በገባው መሠረት ንጉሥ+ እንዲሆን ብርቱ ድጋፍ አድርገውለታል። 11 የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች ስም ዝርዝር ይህ ነው፦ የሦስቱ መሪ+ የሆነው የሃክሞናዊው ልጅ ያሾብአም።+ እሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ጊዜ 300 ሰው ገደለ።+ 12 ከእሱ ቀጥሎ የአሆሐያዊው+ የዶዶ ልጅ አልዓዛር ነበር።+ እሱም ከሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች መካከል አንዱ ነው። 13 ፍልስጤማውያን ለጦርነት ተሰብስበው በነበረበት ጊዜ በጳስዳሚም+ ከዳዊት ጋር አብሮ ነበር። በዚያም የገብስ ሰብል የሞላበት መሬት ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጤማውያን የተነሳ ከአካባቢው ሸሹ። 14 እሱ ግን በእርሻው መካከል ካለበት ንቅንቅ ሳይል መሬቱ እንዳይያዝ አደረገ፤ ፍልስጤማውያንንም መታቸው፤ በመሆኑም ይሖዋ ታላቅ ድል አጎናጸፈ።*+
15 የፍልስጤም ሠራዊት በረፋይም ሸለቆ*+ ሰፍሮ በነበረበት ጊዜ፣ ከ30ዎቹ መሪዎች መካከል ሦስቱ ዓለታማ ወደሆነውና ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ አዱላም ዋሻ ወረዱ።+ 16 በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበር፤ የፍልስጤማውያንም ሠራዊት በቤተልሔም ነበር። 17 ከዚያም ዳዊት “በቤተልሔም+ በር አቅራቢያ ካለው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ የምጠጣው ውኃ ባገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ!” በማለት ምኞቱን ገለጸ። 18 በዚህ ጊዜ ሦስቱ ወደ ፍልስጤማውያን ሰፈር ጥሰው በመግባት በቤተልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውኃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ ዳዊት ግን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ውኃውን ለይሖዋ አፈሰሰው። 19 እንዲህም አለ፦ “ለአምላኬ ካለኝ አክብሮት የተነሳ ይህን ማድረግ ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው! ሕይወታቸውን* አደጋ ላይ ጥለው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም ልጠጣ ይገባል?+ ውኃውን ያመጡት በሕይወታቸው* ቆርጠው ነውና።” በመሆኑም ውኃውን ለመጠጣት ፈቃደኛ አልሆነም። ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎቹ ያደረጓቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ።
20 የኢዮዓብ+ ወንድም አቢሳ+ የሌሎች ሦስት ሰዎች መሪ ነበር፤ እሱም ጦሩን ሰብቆ 300 ሰው ገደለ፤ እንደ ሦስቱም ሰዎች ዝነኛ ነበር።+ 21 ከሌሎቹ ሦስት ሰዎች መካከል እሱ ከሁለቱ የበለጠ ታዋቂ ነበር፤ የእነሱም አለቃ ነበር፤ ይሁን እንጂ የመጀመሪያዎቹን ሦስት ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም።
22 የዮዳሄ ልጅ በናያህ+ በቃብጽኤል+ ብዙ ጀብዱ የፈጸመ ደፋር ሰው* ነበር። እሱም የሞዓቡን የአርዔልን ሁለት ወንዶች ልጆች ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በሚጥልበት ዕለት ወደ አንድ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ገደለ።+ 23 ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ* የሆነ እጅግ ግዙፍ+ ግብፃዊ ገደለ። ግብፃዊው የሸማኔ መጠቅለያ+ የሚመስል ጦር በእጁ ይዞ የነበረ ቢሆንም በትር ብቻ ይዞ በመግጠም የግብፃዊውን ጦር ከእጁ ቀምቶ በገዛ ጦሩ ገደለው።+ 24 የዮዳሄ ልጅ በናያህ ያደረጋቸው ነገሮች እነዚህ ነበሩ፤ እሱም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተዋጊዎች ዝነኛ ነበር። 25 ከሠላሳዎቹም ይበልጥ ታዋቂ የነበረ ቢሆንም የሦስቱን ሰዎች ያህል ማዕረግ አላገኘም።+ ይሁን እንጂ ዳዊት የራሱ የክብር ዘብ አለቃ አድርጎ ሾመው።
26 በሠራዊቱ ውስጥ የነበሩት ኃያላን ተዋጊዎች የሚከተሉት ናቸው፦ የኢዮዓብ ወንድም አሳሄል፣+ የቤተልሔሙ የዶዶ ልጅ ኤልሃናን፣+ 27 ሃሮራዊው ሻሞት፣ ጴሎናዊው ሄሌጽ፣ 28 የተቆአዊው የኢቄሽ ልጅ ኢራ፣+ አናቶታዊው አቢዔዜር፣+ 29 ሁሻዊው ሲበካይ፣+ አሆሐያዊው ኢላይ፣ 30 ነጦፋዊው ማህራይ፣+ የነጦፋዊው የባአናህ ልጅ ሄሌድ፣+ 31 ከቢንያማውያን+ ወገን የሆነው የጊብዓው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣ ጲራቶናዊው በናያህ፣ 32 የጋአሽ+ ደረቅ ወንዞች* ሰው የሆነው ሁራይ፣ አርባዊው አቢዔል፣ 33 ባሁሪማዊው አዝማዌት፣ ሻአልቢማዊው ኤሊያህባ፣ 34 የጊዞናዊው የሃሼም ወንዶች ልጆች፣ የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣ 35 የሃራራዊው የሳካር ልጅ አሂዓም፣ የዑር ልጅ ኤሊፋል፣ 36 መከራታዊው ሄፌር፣ ጴሎናዊው አኪያህ፣ 37 ቀርሜሎሳዊው ሄጽሮ፣ የኤዝባይ ልጅ ናአራይ፣ 38 የናታን ወንድም ኢዩኤል፣ የሃግሪ ልጅ ሚብሃር፣ 39 አሞናዊው ጼሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮዓብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮታዊው ናሃራይ፤ 40 ይትራዊው ኢራ፣ ይትራዊው ጋሬብ፣ 41 ሂታዊው ኦርዮ፣+ የአህላይ ልጅ ዛባድ፣ 42 የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ አዲና የሮቤላውያን መሪ ነበር፤ ከእሱም ጋር 30 ሰዎች ነበሩ፤ 43 የማአካ ልጅ ሃናን፣ ሚትናዊው ዮሳፍጥ፣ 44 አስታሮታዊው ዑዚያ፣ የአሮዔራዊው የሆታም ልጆች ሻማ እና የኢዔል፤ 45 የሺምሪ ልጅ የዲአዔል፣ ቲጺያዊው ወንድሙ ዮሃ፤ 46 ማሃዋዊው ኤሊዔል፣ የኤልናዓም ልጆች የሪባይ እና ዮሻውያህ፣ ሞዓባዊው ይትማ፤ 47 ኤሊዔል፣ ኢዮቤድ እና መጾባዊው ያአሲዔል።
12 ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል የተነሳ ተደብቆ ይኖር+ በነበረበት ጊዜ እሱ ወዳለበት ወደ ጺቅላግ+ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ እነሱም በጦርነት ከረዱት ኃያላን ተዋጊዎች መካከል ነበሩ።+ 2 ቀስት የታጠቁ ነበሩ፤ በቀኝ እጃቸውም ሆነ በግራ እጃቸው+ ድንጋይ መወንጨፍ+ ወይም ፍላጻ ማስፈንጠር ይችሉ ነበር። እነሱ ከቢንያም ነገድ+ ሲሆኑ የሳኦል ወንድሞች ነበሩ። 3 መሪያቸው አሂዔዜር ሲሆን ከእሱ ጋር ዮአስ ነበር፤ ሁለቱም የጊብዓዊው+ የሸማህ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ ደግሞም የአዝማዌት ወንዶች ልጆች የዚኤል እና ጴሌጥ፣ ቤራካ፣ አናቶታዊው+ ኢዩ፣ 4 ከሠላሳዎቹ አለቆች+ መካከል ኃያል ተዋጊና የሠላሳዎቹ መሪ የሆነው ገባኦናዊው+ ይሽማያህ፤ በተጨማሪም ኤርምያስ፣ ያሃዚኤል፣ ዮሃናን፣ ገዴራዊው ዮዛባድ፣ 5 ኤልዑዛይ፣ የሪሞት፣ በአልያህ፣ ሸማርያህ፣ ሃሪፋዊው ሰፋጥያህ፣ 6 ቆሬያውያን+ የሆኑት ሕልቃና፣ ይሽሺያህ፣ አዛርዔል፣ ዮኤዘር፣ ያሾብአም፤ 7 የጌዶር ሰው የሆነው የየሮሃም ወንዶች ልጆች ዮኤላ እና ዘባድያህ ነበሩ።
8 አንዳንድ ጋዳውያን ዳዊት ወዳለበት በምድረ በዳ ወደሚገኘው ምሽግ+ መጥተው ከእሱ ጎን ተሰለፉ፤ እነሱም ኃያላን ተዋጊዎችና ለጦርነት የሠለጠኑ ወታደሮች ሲሆኑ ትልቅ ጋሻና ረጅም ጦር ታጥቀው የሚጠባበቁ ነበሩ፤ ፊታቸው እንደ አንበሳ ፊት ነበር፤ በተራሮችም ላይ እንደ ሜዳ ፍየል ፈጣኖች ነበሩ። 9 ኤጼር መሪ ነበር፤ ሁለተኛው አብድዩ፣ ሦስተኛው ኤልያብ፣ 10 አራተኛው ሚሽማና፣ አምስተኛው ኤርምያስ፣ 11 ስድስተኛው አታይ፣ ሰባተኛው ኤሊዔል፣ 12 ስምንተኛው ዮሃናን፣ ዘጠነኛው ኤልዛባድ፣ 13 አሥረኛው ኤርምያስ፣ አሥራ አንደኛው ማክባናይ ነበሩ። 14 እነዚህ የሠራዊቱ መሪዎች የሆኑ ጋዳውያን+ ነበሩ። ታናሽ የሆነው 100 ወታደሮችን፣ ታላቅ የሆነውም 1,000 ወታደሮችን ይቋቋም ነበር።+ 15 በመጀመሪያው ወር ዮርዳኖስ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ እየፈሰሰ ሳለ፣ ወንዙን አቋርጠው በቆላው የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ያባረሩት እነዚህ ነበሩ።
16 በተጨማሪም ከቢንያምና ከይሁዳ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ዳዊት ወደሚኖርበት ወደ ምሽጉ መጡ።+ 17 ዳዊትም ወደ እነሱ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “የመጣችሁት በሰላም ከሆነና እኔን ለመርዳት ከሆነ ልቤ ከእናንተ ጋር አንድ ይሆናል። ሆኖም እጄ ከበደል ንጹሕ ሆኖ ሳለ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ የአባቶቻችን አምላክ ጉዳዩን አይቶ ይፍረድ።”+ 18 ከዚያም የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በአማሳይ ላይ መንፈስ ወረደበት፤*+ እሱም እንዲህ አለ፦
“ዳዊት ሆይ፣ እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፣ እኛ ከአንተ ጋር ነን።+
ሰላም፣ አዎ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አንተን ለሚረዳም ሰላም ይሁን፤
አምላክህ እየረዳህ ነውና።”+
ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤ በሠራዊቱም መሪዎች መካከል ሾማቸው።
19 ከምናሴ ነገድ የሆኑ አንዳንድ ሰዎችም ከድተው ወደ እሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት ከፍልስጤማውያን ጋር ሆኖ ሳኦልን ለመውጋት ወጥቶ ነበር፤ ሆኖም ፍልስጤማውያንን አልረዳቸውም፤ ምክንያቱም የፍልስጤም ገዢዎች+ ከተመካከሩ በኋላ “ከድቶ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል በመሄድ እኛን ያስጨርሰናል”+ ሲሉ መልሰውት ነበር። 20 ዳዊት ወደ ጺቅላግ+ በሄደ ጊዜ ከምናሴ ነገድ ከድተው ወደ እሱ የመጡት አድናህ፣ ዮዛባድ፣ የዲአዔል፣ ሚካኤል፣ ዮዛባድ፣ ኤሊሁ እና ጺለታይ ሲሆኑ እነሱም ከምናሴ ነገድ የሆኑ የሺህ አለቆች ነበሩ።+ 21 ሁሉም ኃያልና ደፋር+ ስለነበሩ ዳዊት ከወራሪ ኃይሎች ጋር በሚያደርገው ውጊያ ረዱት። ከዚያም በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች ሆኑ። 22 ሠራዊቱም እንደ አምላክ ሠራዊት ታላቅ እስኪሆን ድረስ፣ ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጎርፉ ነበር።+
23 በይሖዋ ትእዛዝ መሠረት የሳኦልን ንግሥና ወደ ዳዊት ለማስተላለፍ በኬብሮን+ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት የመጡት ለውጊያ የታጠቁ መሪዎች ቁጥር ይህ ነው።+ 24 ትልቅ ጋሻና ረጅም ጦር የያዙ ለውጊያ የታጠቁ የይሁዳ ሰዎች 6,800 ነበሩ። 25 ከስምዖናውያን መካከል ከሠራዊቱ ጋር የተቀላቀሉ 7,100 ኃያልና ደፋር ሰዎች ነበሩ።
26 ከሌዋውያን 4,600 ነበሩ። 27 ዮዳሄ+ የአሮን ልጆች+ መሪ የነበረ ሲሆን ከእሱም ጋር 3,700 ሰዎች ነበሩ፤ 28 በተጨማሪም ሳዶቅ+ የተባለው ኃያልና ደፋር ወጣት ከአባቶቹ ቤት ከተውጣጡ 22 አለቆች ጋር መጣ።
29 የሳኦል ወንድሞች ከሆኑት ቢንያማውያን+ መካከል 3,000 ነበሩ፤ ቀደም ሲል ብዙዎቹ የሳኦልን ቤት በታማኝነት ይደግፉ ነበር። 30 ከኤፍሬማውያን መካከል ከአባቶቻቸው ቤት የተውጣጡ 20,800 ኃያል፣ ደፋርና ስመ ጥር ሰዎች ነበሩ።
31 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዳዊትን ለማንገሥ የመጡ በስም የተጠቀሱ 18,000 ሰዎች ነበሩ። 32 ከይሳኮር ነገድ መካከል ዘመኑን ያስተዋሉና እስራኤል ምን ማድረግ እንዳለበት የተገነዘቡ 200 መሪዎች ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ እነሱን ይታዘዙ ነበር። 33 ከዛብሎን ነገድ በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የሚችሉ፣ ለውጊያ ዝግጁ የሆኑና ልዩ ልዩ ዓይነት መሣሪያዎች የታጠቁ 50,000 ሰዎች ነበሩ፤ ሁሉም ወደ ዳዊት የመጡት በፍጹም ታማኝነት ነበር።* 34 ከንፍታሌም ነገድ 1,000 አለቆች ነበሩ፤ ከእነሱም ጋር ትልቅ ጋሻና ጦር የያዙ 37,000 ሰዎች ነበሩ። 35 ከዳናውያን ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ 28,600 ሰዎች ነበሩ። 36 ከአሴር ነገድ ደግሞ ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የሚችሉ 40,000 ሰዎች ነበሩ።
37 ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ+ ካሉት ከሮቤላውያን፣ ከጋዳውያንና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለጦርነት የሚያስፈልጉ የተለያዩ መሣሪያዎችን የታጠቁ 120,000 ወታደሮች ነበሩ። 38 እነዚህ ሁሉ በአንድነት ለውጊያ የተሰለፉና ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ወታደሮች ነበሩ፤ ዳዊትን በመላው እስራኤል ላይ ለማንገሥ በአንድ ልብ ሆነው ወደ ኬብሮን መጡ፤ በተጨማሪም የቀረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በአንድ ልብ ሆኖ ዳዊትን ለማንገሥ ተነሳ።+ 39 ወንድሞቻቸው አዘጋጅተውላቸው ስለነበር በዚያ እየበሉና እየጠጡ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ቆዩ። 40 በተጨማሪም በአቅራቢያቸው ያሉትም ሆኑ እስከ ይሳኮር፣ ዛብሎንና ንፍታሌም ድረስ ርቀው የሚገኙት ሰዎች በአህያ፣ በግመል፣ በበቅሎና በከብት ምግብ ጭነው መጡ፤ ይኸውም ከፍተኛ መጠን ያለው ዱቄት፣ የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣ የወይን ጠጅ፣ ዘይት፣ ከብትና በግ ነበር፤ በእስራኤል ታላቅ ደስታ ሰፍኖ ነበርና።
13 ዳዊት ከሺህ አለቆቹና ከመቶ አለቆቹ እንዲሁም ከመሪዎቹ ሁሉ ጋር ተማከረ።+ 2 ከዚያም ዳዊት ለመላው የእስራኤል ጉባኤ እንዲህ አለ፦ “ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁና በአምላካችን በይሖዋ ፊት ተቀባይነት ያለው ከሆነ፣ በእስራኤል ምድር ሁሉ ያሉት የቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም የግጦሽ መሬቶች ባሏቸው ከተሞቻቸው የሚኖሩት ካህናትና ሌዋውያን+ ወደ እኛ እንዲሰበሰቡ መልእክት እንላክባቸው። 3 የአምላካችንንም ታቦት መልሰን እናምጣ።”+ በሳኦል ዘመን ታቦቱን ችላ ብለውት ነበርና።+ 4 ነገሩ በሕዝቡ ሁሉ ፊት መልካም ሆኖ ስለተገኘ መላው ጉባኤ ይህን ለማድረግ ተስማማ። 5 በመሆኑም ዳዊት የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ከቂርያትየአሪም ለማምጣት ከግብፅ ወንዝ* አንስቶ እስከ ሌቦሃማት*+ ድረስ ያለውን የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰበሰበ።+
6 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የሚቀመጠውን+ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት ይኸውም ሰዎች የይሖዋን ስም የሚጠሩበትን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ምድር ወደምትገኘው ቂርያትየአሪም ወደምትባለው ወደ ባዓላ+ ወጡ። 7 ይሁን እንጂ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጭነው+ ከአቢናዳብ ቤት አመጡት፤ ደግሞም ዖዛና አሂዮ ሠረገላውን እየነዱ ነበር።+ 8 ዳዊትና መላው የእስራኤል ሕዝብ በመዝሙር፣ በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በአታሞ፣+ በሲምባልና*+ በመለከት+ ታጅበው በሙሉ ኃይላቸው በእውነተኛው አምላክ ፊት በደስታ ይጨፍሩ ነበር። 9 ወደ ኪዶን አውድማ ሲደርሱ ግን ከብቶቹ ታቦቱን ሊጥሉት ተቃርበው ስለነበር ዖዛ እጁን ዘርግቶ ታቦቱን ያዘ። 10 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ ታቦቱን ለመያዝ እጁን በመዘርጋቱም ቀሰፈው፤+ እሱም በአምላክ ፊት እዚያው ሞተ።+ 11 ሆኖም የይሖዋ ቁጣ በዖዛ ላይ ስለነደደ ዳዊት ተበሳጨ፤* ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ጴሬዝዖዛ* ተብሎ ይጠራል።
12 ዳዊትም በዚያን ዕለት እውነተኛውን አምላክ ፈርቶ “ታዲያ የእውነተኛውን አምላክ ታቦት እንዴት ወደ እኔ ማምጣት እችላለሁ?” አለ።+ 13 ዳዊት ታቦቱን እሱ ወዳለበት ወደ ዳዊት ከተማ አላመጣውም፤ ይልቁንም የጌት ሰው ወደሆነው ወደ ኦቤድዔዶም ቤት እንዲወሰድ አደረገ። 14 የእውነተኛው አምላክ ታቦት ከኦቤድዔዶም ቤተሰብ ጋር በቤቱ ለሦስት ወራት ያህል ተቀመጠ፤ ይሖዋም የኦቤድዔዶምን ቤተሰብና ያለውን ሁሉ ባረከ።+
14 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም+ ለዳዊት ቤት* እንዲሠሩለት መልእክተኞችን እንዲሁም የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና* አናጺዎችን ላከ።+ 2 ዳዊትም ይሖዋ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናው አወቀ፤+ ምክንያቱም አምላክ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤል ሲል ንግሥናውን ከፍ ከፍ አድርጎለት ነበር።+
3 ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤+ ደግሞም ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።+ 4 በኢየሩሳሌም ሳለ የተወለዱለት ልጆች ስም ይህ ነው፦+ ሻሙአ፣ ሾባብ፣ ናታን፣+ ሰለሞን፣+ 5 ይብሃር፣ ኤሊሹዓ፣ ኤልፔሌት፣ 6 ኖጋ፣ ኔፌግ፣ ያፊአ፣ 7 ኤሊሻማ፣ ቤኤልያዳ እና ኤሊፌሌት።
8 ፍልስጤማውያንም በሙሉ ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን+ ሲሰሙ እሱን ፍለጋ ወጡ።+ ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ሊገጥማቸው ወጣ። 9 ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው በረፋይም ሸለቆ* ወረራ አካሄዱ።+ 10 ዳዊትም “ወጥቼ ፍልስጤማውያንን ልግጠም? በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ?” ሲል አምላክን ጠየቀ። ይሖዋም “አዎ ውጣ፤ እኔም በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” አለው።+ 11 በመሆኑም ዳዊት ወደ በዓልጰራጺም+ ወጥቶ በዚያ መታቸው። ከዚያም ዳዊት “እውነተኛው አምላክ፣ ውኃ እንደጣሰው ግድብ ጠላቶቼን በእጄ ደረማመሳቸው” አለ። ከዚህም የተነሳ ያን ቦታ በዓልጰራጺም* ብለው ጠሩት። 12 ፍልስጤማውያንም አማልክታቸውን በዚያ ጥለው ሸሹ፤ ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረትም በእሳት አቃጠሏቸው።+
13 ከጊዜ በኋላ ፍልስጤማውያን ሸለቆውን* እንደገና ወረሩ።+ 14 ዳዊት ዳግመኛ አምላክን ጠየቀ፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ እንዲህ አለው፦ “እነሱን ለመግጠም በቀጥታ አትውጣ። ይልቁንም ከኋላቸው ዙርና በባካ* ቁጥቋጦዎቹ ፊት መጥተህ ግጠማቸው።+ 15 ደግሞም በባካ ቁጥቋጦዎቹ አናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ጥቃት ሰንዝር፤ ምክንያቱም ይህ በሚሆንበት ጊዜ እውነተኛው አምላክ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመምታት በፊትህ ወጥቷል ማለት ነው።”+ 16 ስለዚህ ዳዊት ልክ እውነተኛው አምላክ እንዳዘዘው አደረገ፤+ የፍልስጤማውያንንም ሠራዊት ከገባኦን አንስቶ እስከ ጌዜር+ ድረስ መቷቸው። 17 የዳዊትም ዝና በአገሩ ሁሉ ተሰማ፤ ይሖዋም ብሔራት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።+
15 ዳዊትም፣ በገዛ ከተማው ለራሱ ቤቶችን መገንባት ቀጠለ፤ ደግሞም የእውነተኛው አምላክ ታቦት የሚቀመጥበትን ስፍራ አዘጋጀ፤ ድንኳንም ተከለ።+ 2 በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “ከሌዋውያን በስተቀር ማንም ሰው የእውነተኛውን አምላክ ታቦት መሸከም የለበትም፤ የይሖዋን ታቦት እንዲሸከሙና ምንጊዜም እንዲያገለግሉት ይሖዋ የመረጠው እነሱን ነውና።”+ 3 ከዚያም ዳዊት የይሖዋን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ መላውን የእስራኤል ሕዝብ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።+
4 ዳዊት የአሮንን ዘሮችና+ ሌዋውያኑን+ ሰበሰበ፦ 5 ከቀአታውያን መካከል አለቃውን ዑሪኤልንና 120 ወንድሞቹን፣ 6 ከሜራራውያን መካከል አለቃውን አሳያህንና+ 220 ወንድሞቹን፣ 7 ከጌርሳማውያን መካከል አለቃውን ኢዩኤልንና+ 130 ወንድሞቹን፣ 8 ከኤሊጻፋን+ ዘሮች መካከል አለቃውን ሸማያህንና 200 ወንድሞቹን፣ 9 ከኬብሮን ዘሮች መካከል አለቃውን ኤሊዔልንና 80 ወንድሞቹን፣ 10 ከዑዚኤል+ ዘሮች መካከል አለቃውን አሚናዳብንና 112 ወንድሞቹን ሰበሰበ። 11 በተጨማሪም ዳዊት ካህናቱን ሳዶቅንና+ አብያታርን+ እንዲሁም ሌዋውያኑን ዑሪኤልን፣ አሳያህን፣ ኢዩኤልን፣ ሸማያህን፣ ኤሊዔልን እና አሚናዳብን ጠራ፤ 12 እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤት መሪዎች ናችሁ። እናንተና ወንድሞቻችሁ ራሳችሁን ቀድሱ፤ የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ታቦትም ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ አምጡ። 13 በመጀመሪያው ጊዜ ታቦቱን ሳትሸከሙ በመቅረታችሁ+ የአምላካችን የይሖዋ ቁጣ በእኛ ላይ ነድዶ ነበር፤+ ይህ የሆነው ትክክለኛውን መመሪያ ባለመከተላችን ነው።”+ 14 ስለዚህ ካህናቱና ሌዋውያኑ የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ታቦት ለማምጣት ራሳቸውን ቀደሱ።
15 ከዚያም ሌዋውያኑ ሙሴ በይሖዋ ቃል መሠረት እንዳዘዘው የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በመሎጊያዎቹ አድርገው በትከሻቸው ላይ ተሸከሙ።+ 16 ከዚያም ዳዊት በሙዚቃ መሣሪያዎች ይኸውም በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በበገና+ እና በሲምባል+ ታጅበው በደስታ ይዘምሩ ዘንድ ዘማሪ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን እንዲሾሙ ለሌዋውያኑ አለቆች ነገራቸው።
17 በመሆኑም ሌዋውያኑ የኢዩኤልን ልጅ ሄማንን፣+ ከወንድሞቹም መካከል የቤራክያህን ልጅ አሳፍን፣+ እንዲሁም ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከሜራራውያን መካከል የቁሻያህን ልጅ ኤታንን+ ሾሙ። 18 ከእነሱ ጋር በሁለተኛው ምድብ ያሉት ወንድሞቻቸው ይገኙ ነበር፤+ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦ ዘካርያስ፣ ቤን፣ ያአዚዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ዑኒ፣ ኤልያብ፣ በናያህ፣ ማአሴያህ፣ ማቲትያህ፣ ኤሊፌሌሁ፣ ሚቅኔያህ፣ በር ጠባቂዎቹ ኦቤድዔዶም እና የኢዔል። 19 ዘማሪዎቹ ሄማን፣+ አሳፍ+ እና ኤታን ከመዳብ በተሠራ ሲምባል+ እንዲጫወቱ ተመደቡ፤ 20 ዘካርያስ፣ አዚዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ዑኒ፣ ኤልያብ፣ ማአሴያህ እና በናያህ ደግሞ በአላሞት* ቅኝት+ በባለ አውታር መሣሪያዎች ይጫወቱ ነበር፤ 21 ማቲትያህ፣+ ኤሊፌሌሁ፣ ሚቅኔያህ፣ ኦቤድዔዶም፣ የኢዔል እና አዛዝያ ደግሞ በሸሚኒት* ቅኝት+ በገና ይጫወቱና የሙዚቀኞች ቡድን መሪ ሆነው ያገለግሉ ነበር። 22 የሌዋውያን አለቃ የሆነው ኬናንያ+ ሥራውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ታቦቱን የማጓጓዙን ሥራ በበላይነት ይከታተል ነበር፤ 23 ቤራክያህ እና ሕልቃና ታቦቱ የተቀመጠበትን ቦታ በር ይጠብቁ ነበር። 24 ካህናቱ ሸባንያህ፣ ዮሳፍጥ፣ ናትናኤል፣ አማሳይ፣ ዘካርያስ፣ በናያህ እና ኤሊዔዘር በእውነተኛው አምላክ ታቦት ፊት ከፍ ባለ ድምፅ መለከት ይነፉ ነበር፤+ ኦቤድዔዶም እና የሂያህ ታቦቱ የተቀመጠበትን ቦታ በር በመጠበቅም ያገለግሉ ነበር።
25 ከዚያም ዳዊትና የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲሁም የሺህ አለቆቹ የይሖዋን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከኦቤድዔዶም+ ቤት በታላቅ ደስታ ለማምጣት ሄዱ።+ 26 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን፣ እውነተኛው አምላክ ስለረዳቸው ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ሠዉ።+ 27 ዳዊት፣ ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣ ዘማሪዎቹ እንዲሁም ታቦቱን የማጓጓዙ ሥራ ኃላፊና የዘማሪዎቹ አለቃ የሆነው ኬናንያ እጅጌ የሌለው ምርጥ ልብስ ለብሰው ነበር፤ በተጨማሪም ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ ነበር።+ 28 መላው የእስራኤል ሕዝብ በቀንደ መለከት፣ በመለከትና+ በሲምባል ድምፅ ታጅቦ ባለ አውታር መሣሪያዎችንና በገናን+ ከፍ ባለ ድምፅ እየተጫወተ በእልልታ+ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት አመጣ።
29 ይሁንና የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በመጣ ጊዜ+ የሳኦል ልጅ ሜልኮል+ በመስኮት ሆና ወደ ታች ተመለከተች፤ ንጉሥ ዳዊት ሲዘልና በደስታ ሲጨፍር አይታ በልቧ ናቀችው።+
16 የእውነተኛውን አምላክ ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አስቀመጡት፤+ ከዚያም የሚቃጠሉ መባዎችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን በእውነተኛው አምላክ ፊት አቀረቡ።+ 2 ዳዊት የሚቃጠሉትን መባዎችና+ የኅብረት መሥዋዕቶቹን+ አቅርቦ ሲጨርስ ሕዝቡን በይሖዋ ስም ባረከ። 3 በተጨማሪም ለእስራኤላውያን ሁሉ፣ ለእያንዳንዱ ወንድና ሴት አንድ ዳቦ፣ አንድ የቴምር ጥፍጥፍና አንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ። 4 ከዚያም የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ያከብሩ፣* ያመሰግኑና ያወድሱ ዘንድ የተወሰኑ ሌዋውያንን በይሖዋ ታቦት ፊት እንዲያገለግሉ ሾመ።+ 5 መሪው አሳፍ+ ነበር፤ ከእሱ ቀጥሎ ዘካርያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ የኢዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ማቲትያህ፣ ኤልያብ፣ በናያህ፣ ኦቤድዔዶም እና የኢዔል+ ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና ይጫወቱ ነበር፤+ አሳፍ ደግሞ ሲምባል ይጫወት ነበር፤+ 6 ካህናቱ በናያህ እና ያሃዚኤል በእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ዘወትር መለከት ይነፉ ነበር።
7 በዚያ ቀን ዳዊት ለመጀመሪያ ጊዜ ለይሖዋ የምስጋና መዝሙር በማቀናበር አሳፍና+ ወንድሞቹ እንዲዘምሩት ሰጣቸው፦
10 በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+
ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+
11 ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ።+
ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።+
12 ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣
ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+
13 እናንተ የአገልጋዩ የእስራኤል ዘሮች፣+
እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ።
14 እሱ ይሖዋ አምላካችን ነው።+
ፍርዱ በመላው ምድር ላይ ነው።+
15 ቃል ኪዳኑን ለዘላለም አስቡ፤
16 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+
ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አስቡ።+
17 ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣
ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤+
18 ‘የከነአንን ምድር
ርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ’ አለ።+
19 ይህን የተናገረው በቁጥር ጥቂት፣
አዎ፣ በጣም ጥቂት በነበራችሁ ጊዜ ነው፤ በምድሪቱም ላይ የባዕድ አገር ሰዎች ነበራችሁ።+
20 እነሱም ከአንዱ ብሔር ወደ ሌላው ብሔር፣
ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ሕዝብ ተንከራተቱ።+
21 ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም፤+
ይልቁንም ለእነሱ ሲል ነገሥታትን ገሠጸ፤+
22 ‘የቀባኋቸውን አገልጋዮቼን አትንኩ፤
በነቢያቴም ላይ አንዳች ክፉ ነገር አታድርጉ’ አላቸው።+
23 መላዋ ምድር ለይሖዋ ትዘምር!
ማዳኑን በየቀኑ አሳውቁ!+
24 ክብሩን በብሔራት፣
አስደናቂ ሥራዎቹንም በሕዝቦች ሁሉ መካከል አስታውቁ።
25 ይሖዋ ታላቅ ነውና፤ ደግሞም እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።
ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ የሚፈራ ነው።+
28 እናንተ የሕዝብ ነገዶች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤
ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+
ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ።*+
30 ምድር ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጪ!
ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤ ከቦታዋ ልትንቀሳቀስ* አትችልም።+
32 ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማ፤
መስኩና በላዩ ላይ ያለው ሁሉ ሐሴት ያድርግ።
33 የዱር ዛፎችም በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ፤
እሱ በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነውና።*
36 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ
ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ።’”
ሕዝቡም ሁሉ “አሜን!”* አሉ፤ ይሖዋንም አወደሱ።
37 ከዚያም ዳዊት በዕለታዊው ልማድ መሠረት+ በታቦቱ ፊት ዘወትር እንዲያገለግሉ+ አሳፍንና+ ወንድሞቹን በዚያ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው። 38 ኦቤድዔዶምና 68 ወንድሞቹ እንዲሁም የየዱቱን ልጅ ኦቤድዔዶምና ሆሳ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤ 39 ካህኑ ሳዶቅና+ አብረውት የሚያገለግሉት ካህናት ደግሞ በገባኦን በሚገኘው ከፍ ያለ ቦታ፣+ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ነበሩ፤ 40 ይህም የሆነው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ዘወትር ጠዋትና ማታ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲያቀርቡና ይሖዋ ለእስራኤል በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በሕጉ ላይ የሰፈረውን ሁሉ እንዲፈጽሙ ነው።+ 41 ይሖዋን ያመሰግኑ ዘንድ ሄማን እና የዱቱን+ እንዲሁም በስም ተጠቅሰው የተመረጡት የቀሩት ሰዎች ከእነሱ ጋር ነበሩ፤+ ምክንያቱም “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል”፤+ 42 ደግሞም መለከት፣ ሲምባልና እውነተኛውን አምላክ ለማወደስ የሚያገለግሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን* ይጫወቱ ዘንድ ሄማን+ እና የዱቱን ከእነሱ ጋር ነበሩ፤ የየዱቱን+ ወንዶች ልጆች ደግሞ በር ላይ ተመድበው ነበር። 43 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ዳዊትም ቤተሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ሄደ።
17 ዳዊት በራሱ ቤት* መኖር እንደጀመረ ነቢዩ ናታንን+ “የይሖዋ የቃል ኪዳኑ ታቦት በድንኳን ውስጥ ተቀምጦ+ ሳለ ይኸው እኔ ከአርዘ ሊባኖስ+ በተሠራ ቤት ውስጥ እየኖርኩ ነው” አለው። 2 ናታንም ዳዊትን “እውነተኛው አምላክ ከአንተ ጋር ስለሆነ በልብህ ያለውን ነገር ሁሉ አድርግ” አለው።
3 በዚያው ሌሊት የአምላክ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ናታን መጣ፦ 4 “ሂድና አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም።+ 5 እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ድንኳን፣ ከአንዱም የማደሪያ ድንኳን ወደ ሌላው የማደሪያ ድንኳን* እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርኩም።+ 6 ከመላው እስራኤል ጋር በተጓዝኩበት ጊዜ ሁሉ ሕዝቤን እረኛ ሆነው እንዲጠብቁ ከሾምኳቸው የእስራኤል ፈራጆች መካከል ‘በአርዘ ሊባኖስ፣ ቤት ያልሠራህልኝ ለምንድን ነው?’ ያልኩት ማን አለ?” ’
7 “አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ ወሰድኩህ።+ 8 እኔም በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤+ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋለሁ፤+ ስምህንም በምድር ላይ እንዳሉ ታላላቅ ሰዎች ስም አደርገዋለሁ።+ 9 ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ተረጋግተው እንዲቀመጡም አደርጋለሁ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም የሚረብሻቸው አይኖርም፤ ክፉዎችም እንደቀድሞው ዳግመኛ አይጨቁኗቸውም፤*+ 10 በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን ከሾምኩበት+ ጊዜ አንስቶ ሲያደርጉ እንደነበሩት አያደርጉባቸውም። ጠላቶቻችሁም ሁሉ እንዲገዙላችሁ አደርጋለሁ።+ በተጨማሪም ‘ይሖዋ ቤት እንደሚሠራልህ’* እነግርሃለሁ።
11 “ ‘ “የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ ከአባቶችህ ጋር ለመሆን በምትሄድበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ዘርህን ይኸውም ከወንዶች ልጆችህ መካከል አንዱን አስነሳለሁ፤+ ንግሥናውንም አጸናለሁ።+ 12 ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 13 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ታማኝ ፍቅሬንም ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድኩ+ ከእሱ ላይ አልወስድም።+ 14 በቤቴና በንጉሣዊ ግዛቴ ላይ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርገዋለሁ፤+ ዙፋኑም ለዘላለም ይዘልቃል።” ’ ”+
15 ናታንም ይህን ቃል ሁሉና ይህን ራእይ በሙሉ ለዳዊት ነገረው።
16 በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ገብቶ በይሖዋ ፊት ተቀመጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ኧረ ለመሆኑ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ድረስ ያደረስከኝስ ቤቴ ምን ስለሆነ ነው?+ 17 አምላክ ሆይ፣ ይህ ሳያንስ ስለ አገልጋይህ ቤት ገና ወደፊት የሚሆነውንም ነገር ተናገርክ፤+ ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ከዚህ በላይ ከፍ ከፍ ሊደረግ እንደሚገባ ሰው* አድርገህ ተመልክተኸኛል። 18 ስለሰጠኸኝ ክብር አገልጋይህ ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? አንተ አገልጋይህን በሚገባ ታውቀው የለ?+ 19 ይሖዋ ሆይ፣ ለአገልጋይህ ስትል፣ ከልብህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ* ታላቅነትህን በመግለጥ እነዚህን ሁሉ ታላላቅ ነገሮች ፈጽመሃል።+ 20 ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤+ ከአንተ በቀር አምላክ የለም፤+ በጆሯችን የሰማነው ነገር ሁሉ ይህን ያረጋግጣል። 21 በምድር ላይ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ብሔር ማን አለ?+ እውነተኛው አምላክ ሄዶ ሕዝቡ አድርጎ ዋጀው።+ ብሔራትን ከግብፅ ከዋጀኸው ሕዝብህ ፊት አባረህ+ ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን በመፈጸም ስምህን አስጠራህ።+ 22 ሕዝብህን እስራኤልን እስከ ወዲያኛው የራስህ ሕዝብ አደረግከው፤+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተም አምላኩ ሆንክ።+ 23 አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህንና ቤቱን በተመለከተ የገባኸው ቃል እስከ ወዲያኛው የጸና ይሁን፤ ቃል እንደገባኸውም አድርግ።+ 24 ሰዎች ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ለእስራኤል አምላክ ነው’ እንዲሉ ስምህ የጸና* ይሁን፤ ደግሞም ለዘላለም ከፍ ከፍ ይበል፤+ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን።+ 25 አምላኬ ሆይ፣ አንተ ለአገልጋይህ ቤት የመሥራት* ዓላማ እንዳለህ አሳውቀኸዋልና። አገልጋይህ ይህን ጸሎት በልበ ሙሉነት ወደ አንተ የሚያቀርበው በዚህ ምክንያት ነው። 26 አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ እውነተኛው አምላክ አንተ ነህ፤ ለአገልጋይህም እነዚህን መልካም ነገሮች ለማድረግ ቃል ገብተህለታል። 27 በመሆኑም የአገልጋይህን ቤት እባክህ ባርክ፤ በፊትህም ለዘላለም የጸና ይሁን፤ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ቀድሞውንም ባርከኸዋልና፤ ለዘላለምም የተባረከ ይሆናል።”
18 ከጊዜ በኋላም ዳዊት ፍልስጤማውያንን ድል በማድረግ በቁጥጥር ሥር አዋላቸው፤ ጌትንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞችም ከፍልስጤማውያን እጅ ወሰደ።+ 2 ከዚያም ሞዓብን ድል አደረገ፤+ ሞዓባውያንም የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ ግብርም ገበሩለት።+
3 የጾባህ+ ንጉሥ ሃዳድኤዜር+ በኤፍራጥስ ወንዝ+ ላይ ያለውን የበላይነት ለማጠናከር በሄደ ጊዜ ዳዊት በሃማት+ አቅራቢያ ድል አደረገው። 4 ዳዊት ከእሱ ላይ 1,000 ሠረገሎች፣ 7,000 ፈረሰኞችና 20,000 እግረኛ ወታደሮች ማረከ።+ ከዚያም ዳዊት 100 የሠረገላ ፈረሶችን ብቻ አስቀርቶ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ።+ 5 የደማስቆዎቹ ሶርያውያን፣ የጾባህን ንጉሥ ሃዳድኤዜርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን መካከል 22,000 ሰዎችን ገደለ።+ 6 ከዚያም ዳዊት በደማስቆ ሶርያ የጦር ሰፈሮች አቋቋመ፤ ሶርያውያንም የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ ግብርም ገበሩለት። ይሖዋ ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።*+ 7 በተጨማሪም ዳዊት ከሃዳድኤዜር አገልጋዮች ላይ ከወርቅ የተሠሩ ክብ ጋሻዎችን ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። 8 ዳዊት የሃዳድኤዜር ከተሞች ከሆኑት ከጢብሃትና ከኩን እጅግ ብዙ መዳብ ወሰደ። ሰለሞን የመዳቡን ባሕር፣+ ዓምዶቹንና የመዳብ ዕቃዎቹን የሠራው በዚህ ነበር።+
9 የሃማት ንጉሥ ቶዑ፣* ዳዊት የጾባህን ንጉሥ የሃዳድኤዜርን ሠራዊት በሙሉ ድል እንዳደረገ በሰማ ጊዜ+ 10 ደህንነቱን እንዲጠይቅና ከሃዳድኤዜር ጋር ተዋግቶ ድል በማድረጉ የተሰማውን ደስታ እንዲገልጽለት ልጁን ሃዶራምን ወዲያውኑ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው (ሃዳድኤዜር ከቶዑ ጋር ብዙ ጊዜ ይዋጋ ነበርና)፤ እሱም ከወርቅ፣ ከብርና ከመዳብ የተሠሩ ብዙ ዓይነት ዕቃዎችን ይዞ መጣ። 11 ንጉሥ ዳዊት እነዚህን ዕቃዎች ከሁሉም ብሔራት ይኸውም ከኤዶም፣ ከሞዓብ፣ ከአሞናውያን፣+ ከፍልስጤማውያንና+ ከአማሌቃውያን+ ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር ለይሖዋ ቀደሰ።+
12 የጽሩያ ልጅ+ አቢሳ+ በጨው ሸለቆ 18,000 ኤዶማውያንን ገደለ።+ 13 እሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮች አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ።+ ይሖዋ ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አቀዳጀው።*+ 14 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ መግዛቱን ቀጠለ፤+ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕንና ጽድቅን አሰፈነላቸው።+ 15 የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ የሠራዊቱ አዛዥ ነበር፤+ የአሂሉድ ልጅ ኢዮሳፍጥ+ ታሪክ ጸሐፊ ነበር፤ 16 የአኪጡብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አሂሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሻውሻ ደግሞ ጸሐፊ ነበር። 17 የዮዳሄ ልጅ በናያህ የከሪታውያንና+ የጴሌታውያን+ አዛዥ ነበር። የዳዊት ወንዶች ልጆችም ከንጉሡ ቀጥሎ ዋና ባለሥልጣናት ነበሩ።
19 ከጊዜ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናሃሽ ሞተ፤ በእሱም ፋንታ ልጁ ነገሠ።+ 2 በዚህ ጊዜ ዳዊት “አባቱ ታማኝ ፍቅር+ ስላሳየኝ እኔም ለናሃሽ ልጅ ለሃኑን ታማኝ ፍቅር አሳየዋለሁ” አለ። በመሆኑም ዳዊት በአባቱ ሞት ከደረሰበት ሐዘን እንዲያጽናኑት መልእክተኞችን ላከ። ሆኖም የዳዊት አገልጋዮች ሃኑንን ለማጽናናት ወደ አሞናውያን+ ምድር ሲደርሱ 3 የአሞናውያን መኳንንት ሃኑንን እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት አጽናኞችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃል? አገልጋዮቹ ወደ አንተ የመጡት ምድሪቱን በሚገባ ለማጥናትና በውስጧ ያለውን ነገር ለመሰለል እንዲሁም አንተን ለመገልበጥ አይደለም?” 4 በመሆኑም ሃኑን የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ ላጫቸው፤+ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ላካቸው። 5 በአገልጋዮቹ ላይ የደረሰውን ነገር ለዳዊት በነገሩት ጊዜ ሰዎቹ በኀፍረት ተውጠው ስለነበር ዳዊት ወዲያውኑ መልእክተኞችን ወደ እነሱ ላከ፤ ንጉሡም “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ+ ቆዩ፤ ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።
6 ውሎ አድሮ አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ጥንብ እንደተቆጠሩ ተገነዘቡ፤ በመሆኑም ሃኑን እና አሞናውያን ከሜሶጶጣሚያ፣* ከአራምመዓካና ከጾባህ+ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ለመቅጠር 1,000 የብር ታላንት* ላኩ። 7 በዚህ መንገድ 32,000 ሠረገሎችን፣ የማአካን ንጉሥና ሕዝቡን ለራሳቸው ቀጠሩ። እነሱም መጥተው በመደባ+ ፊት ለፊት ሰፈሩ። አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት መጡ።
8 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን+ እንዲሁም እጅግ ኃያላን የሆኑትን ተዋጊዎቹን ጨምሮ መላውን ሠራዊት ላከ።+ 9 አሞናውያንም ወጥተው በከተማዋ መግቢያ ላይ ለውጊያ ተሰለፉ፤ የመጡት ነገሥታት ደግሞ ለብቻቸው ሜዳ ላይ ተሰለፉ።
10 ኢዮዓብ ወታደሮቹ ከፊትና ከኋላ ጥቃት ለመሰንዘር ወደ እሱ እየገሰገሱ መምጣታቸውን ሲያይ በእስራኤል ካሉት ምርጥ የሆኑ ተዋጊዎች መካከል የተወሰኑትን መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።+ 11 የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ+ አመራር ሥር* ሆነው አሞናውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው። 12 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ሶርያውያን+ ከበረቱብኝ አንተ ትደርስልኛለህ፤ አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እደርስልሃለሁ። 13 ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል ብርቱና ደፋር መሆን አለብን፤+ ይሖዋም በፊቱ መልካም የሆነውን ነገር ያደርጋል።”
14 ከዚያም ኢዮዓብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሶርያውያንን ለመግጠም ወደ እነሱ ሲገሰግሱ ሶርያውያኑ ከፊቱ ሸሹ።+ 15 አሞናውያንም ሶርያውያን እንደ ሸሹ ሲያዩ እነሱም ከወንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማዋ ገቡ። ከዚያም ኢዮዓብ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
16 ሶርያውያን በእስራኤላውያን ድል እንደተመቱ ሲያዩ መልእክተኞች ልከው በወንዙ*+ አካባቢ የነበሩትን ሶርያውያን አስጠሩ፤ የሃዳድኤዜር ሠራዊት አለቃ የሆነውም ሾፋክ* ይመራቸው ነበር።+
17 ዳዊት ወሬው በተነገረው ጊዜ ወዲያውኑ እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን በመሻገር ወደ እነሱ መጣ፤ ተዋጊዎቹንም በእነሱ ላይ አሰለፈ። ዳዊት ሶርያውያንን ለመግጠም ተዋጊዎቹን ባሰለፈ ጊዜ ከእሱ ጋር ተዋጉ።+ 18 ይሁንና ሶርያውያን ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን መካከል 7,000 ሠረገለኞችንና 40,000 እግረኛ ወታደሮችን ገደለ፤ የሠራዊቱ አዛዥ የሆነውን ሾፋክንም ገደለው። 19 የሃዳድኤዜር አገልጋዮች በእስራኤል እንደተሸነፉ+ ባዩ ጊዜ ወዲያውኑ ከዳዊት ጋር እርቅ በመፍጠር ለእሱ ተገዙ፤+ ሶርያም ከዚህ በኋላ አሞናውያንን ለመርዳት ፈቃደኛ አልሆነችም።
20 በዓመቱ መባቻ፣* ነገሥታት ለውጊያ በሚዘምቱበት ወቅት ኢዮዓብ+ የጦር ሠራዊቱን በመምራት የአሞናውያንን ምድር አወደመ፤ ወደ ራባ+ ሄዶም ከበባት፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።+ ኢዮዓብም በራባ ላይ ጥቃት ሰንዝሮ አፈራረሳት።+ 2 ከዚያም ዳዊት የማልካምን* ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱም ክብደት አንድ ታላንት* ወርቅ ነበር፤ በላዩም ላይ የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ፤ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተደረገ። በተጨማሪም ከከተማዋ በጣም ብዙ ምርኮ ወሰደ።+ 3 ነዋሪዎቿንም አውጥቶ ድንጋይ እንዲቆርጡ፣ ስለት ባላቸው የብረት መሣሪያዎችና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው።+ ዳዊት በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። በመጨረሻም ዳዊትና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
4 ከዚህ በኋላ ከፍልስጤማውያን ጋር በጌዜር ጦርነት ተከፈተ። በዚህ ጊዜ ሁሻዊው ሲበካይ+ የረፋይም+ ዘር የሆነውን ሲፓይን* ገደለው፤ ፍልስጤማውያንም ድል ተመቱ።
5 ዳግመኛም ከፍልስጤማውያን ጋር ጦርነት ተካሄደ፤ የያኢር ልጅ ኤልሃናን የሸማኔ መጠቅለያ+ የሚመስል ዘንግ ያለው ጦር ይዞ የነበረውን የጎልያድን+ ወንድም ጌታዊውን ላህሚን ገደለው።
6 እንደገናም በጌት+ ጦርነት ተቀሰቀሰ፤ በዚያም በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች፣ በድምሩ 24 ጣቶች ያሉት በጣም ግዙፍ የሆነ ሰው ነበር፤+ እሱም የረፋይም ዘር+ ነበር። 7 ይህ ሰው እስራኤልን ይገዳደር+ ስለነበር የዳዊት ወንድም የሺምአ+ ልጅ ዮናታን ገደለው።
8 እነዚህ በጌት+ የሚኖሩ የረፋይም+ ዘሮች ነበሩ፤ እነሱም በዳዊት እጅና በአገልጋዮቹ እጅ ወደቁ።
21 ከዚያም ሰይጣን* እስራኤልን ለማጥቃት ቆርጦ ተነሳ፤ ደግሞም እስራኤልን እንዲቆጥር ዳዊትን አነሳሳው።+ 2 በመሆኑም ዳዊት ኢዮዓብንና+ የሕዝቡን አለቆች “ሂዱና ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ዳን+ ድረስ ያሉትን እስራኤላውያን ቁጠሩ፤ ከዚያም ቁጥራቸውን አውቅ ዘንድ ንገሩኝ” አላቸው። 3 ኢዮዓብ ግን እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ሕዝቡን 100 እጥፍ ያብዛው! ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ሁሉም የጌታዬ አገልጋዮች አይደሉም? ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን ፈለገ? በእስራኤልስ ላይ ለምን በደል ያመጣል?”
4 ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል በኢዮዓብ ላይ አየለ። በመሆኑም ኢዮዓብ ወጥቶ በመላው እስራኤል ተጓዘ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።+ 5 ኢዮዓብም የተመዘገበውን የሕዝቡን ቁጥር ለዳዊት ሰጠው። በመላው እስራኤል ሰይፍ የታጠቁ 1,100,000 ወንዶች ነበሩ፤ በይሁዳ ደግሞ ሰይፍ የታጠቁ 470,000 ወንዶች ነበሩ።+ 6 ይሁንና ኢዮዓብ የንጉሡን ቃል ተጸይፎ ስለነበር ሌዊንና ቢንያምን በቆጠራው ውስጥ አላካተተም።+
7 ይህ ነገር እውነተኛውን አምላክ በጣም አስቆጣው፤ በመሆኑም እስራኤልን መታ። 8 በዚህ ጊዜ ዳዊት እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለ፦ “ይህን በማድረጌ ከባድ ኃጢአት ፈጽሜአለሁ።+ አሁንም እባክህ የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤+ ታላቅ የሞኝነት ድርጊት ፈጽሜአለሁና።”+ 9 ይሖዋም የዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን+ እንዲህ አለው፦ 10 “ሂድና ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሦስት ምርጫዎችን ሰጥቼሃለሁ። በአንተ ላይ አመጣብህ ዘንድ አንዱን ምረጥ።”’” 11 ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ገብቶ እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ምረጥ፤ 12 ለሦስት ዓመት ረሃብ+ ይሁን ወይስ የጠላቶችህ ሰይፍ አሸንፎህ ለሦስት ወራት ጠላቶችህ ጥፋት ያድርሱብህ+ ወይስ ለሦስት ቀናት የይሖዋ ሰይፍ ይኸውም ቸነፈር+ በምድሪቱ ላይ መጥቶ የይሖዋ መልአክ በመላው የእስራኤል ግዛት ጥፋት+ ያምጣ?’ እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስብበት።” 13 ስለዚህ ዳዊት ጋድን እንዲህ አለው፦ “ሁኔታው በጣም አስጨንቆኛል። ምሕረቱ እጅግ ታላቅ ስለሆነ+ እባክህ በይሖዋ እጅ ልውደቅ፤ ሰው እጅ ላይ ግን አትጣለኝ።”+
14 ከዚያም ይሖዋ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤+ በዚህም የተነሳ ከእስራኤል 70,000 ሰዎች ሞቱ።+ 15 በተጨማሪም እውነተኛው አምላክ ኢየሩሳሌምን እንዲያጠፋ መልአክ ላከ፤ ሆኖም መልአኩ ሊያጠፋት ሲል ይሖዋ ሁኔታውን አይቶ በደረሰው ጥፋት ተጸጸተ፤*+ ስለሆነም የሚያጠፋውን መልአክ “ይብቃ!+ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የይሖዋ መልአክ በኢያቡሳዊው+ በኦርናን*+ አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
16 ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት የይሖዋ መልአክ በምድርና በሰማያት መካከል ቆሞ አየ፤ እሱም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ነበር።+ ዳዊትና ሽማግሌዎቹ ማቅ+ እንደለበሱ ወዲያውኑ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።+ 17 ዳዊትም እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለ፦ “ሕዝቡ እንዲቆጠር ያዘዝኩት እኔ አይደለሁም? ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ፤ በደል የፈጸምኩትም እኔ ነኝ፤+ ታዲያ እነዚህ በጎች ምን አደረጉ? አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፤ በሕዝብህ ላይ ግን ይህን መቅሰፍት አታውርድ።”+
18 በዚህ ጊዜ የይሖዋ መልአክ፣ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርናን አውድማ ላይ ለይሖዋ መሠዊያ እንዲሠራ ለዳዊት እንዲነግረው ጋድን+ አዘዘው።+ 19 ዳዊትም ጋድ በይሖዋ ስም በነገረው ቃል መሠረት ወጣ። 20 ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦርናን ዞር ሲል መልአኩን አየው፤ ከእሱ ጋር የነበሩት አራት ወንዶች ልጆቹም ተሸሸጉ። በዚህ ጊዜ ኦርናን ስንዴ እየወቃ ነበር። 21 ኦርናን ቀና ብሎ ሲመለከት ዳዊት ወደ እሱ ሲመጣ አየ፤ ወዲያውኑም ከአውድማው ወጥቶ በግንባሩ መሬት ላይ በመደፋት ለዳዊት ሰገደ። 22 ዳዊትም ኦርናንን እንዲህ አለው፦ “ለይሖዋ መሠዊያ እንድሠራበት አውድማውን ሽጥልኝ።* በሕዝቡ ላይ የሚወርደው መቅሰፍት እንዲቆም+ ሙሉውን ዋጋ ከፍዬ ልግዛው።” 23 ኦርናን ግን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “በነፃ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሡ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ። እነሆ ከብቶቹን ለሚቃጠል መባ፣ ማሄጃውን*+ ለማገዶ፣ ስንዴውን ደግሞ ለእህል መባ አቀርባለሁ። ሁሉንም ነገር እኔ እሰጣለሁ።”
24 ይሁን እንጂ ንጉሥ ዳዊት ኦርናንን እንዲህ አለው፦ “በፍጹም አይሆንም! ሙሉውን ዋጋ ሰጥቼ እገዛዋለሁ፤ ምክንያቱም የአንተ የሆነውን ነገር ወስጄ ለይሖዋ አልሰጥም ወይም ምንም ያልከፈልኩበትን ነገር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም።”+ 25 በመሆኑም ዳዊት የቦታውን ዋጋ 600 የወርቅ ሰቅል* መዝኖ ለኦርናን ሰጠው። 26 ዳዊትም በዚያ ለይሖዋ መሠዊያ+ ሠርቶ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና የኅብረት መሥዋዕቶች አቀረበ፤ የይሖዋንም ስም ጠራ፤ እሱም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማያት በእሳት+ መለሰለት። 27 ከዚያም ይሖዋ መልአኩን+ ሰይፉን ወደ ሰገባው እንዲመልስ አዘዘው። 28 በዚህ ጊዜ ዳዊት፣ ይሖዋ በኢያቡሳዊው በኦርናን አውድማ መልስ እንደሰጠው ባየ ጊዜ በዚያ ቦታ ላይ መሥዋዕት ማቅረቡን ቀጠለ። 29 ሆኖም ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የይሖዋ የማደሪያ ድንኳንና የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያ በዚያን ጊዜ በገባኦን ባለው ከፍ ያለ ቦታ ላይ ይገኝ ነበር።+ 30 ይሁንና ዳዊት ከይሖዋ መልአክ ሰይፍ የተነሳ እጅግ ፈርቶ ስለነበር አምላክን ለመጠየቅ ወደዚያ መሄድ አልቻለም።
22 ከዚያም ዳዊት “የእውነተኛው አምላክ የይሖዋ ቤት በዚህ ይሆናል፤ ለእስራኤል የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያም በዚሁ ይቆማል” አለ።+
2 ዳዊት በእስራኤል ምድር የሚኖሩትን የባዕድ አገር ሰዎች+ እንዲሰበስቡ አዘዘ፤ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ለመገንባት የሚያስፈልጉትንም ድንጋዮች እንዲጠርቡ ድንጋይ ጠራቢዎች አድርጎ መደባቸው።+ 3 በተጨማሪም ዳዊት ለመግቢያዎቹ በሮች የሚያስፈልጉ ምስማሮችንና ማጠፊያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ከፍተኛ መጠን ያለው ብረት አዘጋጀ፤ ደግሞም ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የማይችል መዳብ አከማቸ፤+ 4 ከዚህም ሌላ ስፍር ቁጥር የሌለው ከአርዘ ሊባኖስ የተሠራ ሳንቃ+ አዘጋጀ፤ ሲዶናውያንና+ ጢሮሳውያን+ ከአርዘ ሊባኖስ የተዘጋጀ ብዛት ያለው ሳንቃ ለዳዊት አምጥተውለት ነበርና። 5 ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “ልጄ ሰለሞን ገና ወጣት ነው፤ ተሞክሮም የለውም፤*+ ለይሖዋ የሚሠራው ቤት ደግሞ እጅግ የሚያምር+ ከመሆኑ የተነሳ ዝናውም ሆነ ውበቱ+ በመላው ምድር የታወቀ ይሆናል።+ ስለዚህ የሚያስፈልገውን ነገር አዘጋጅለታለሁ።” በመሆኑም ዳዊት ከመሞቱ በፊት ለሥራው የሚያስፈልጉትን ነገሮች በብዛት አዘጋጀ።
6 በተጨማሪም ልጁን ሰለሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ፣ ቤት እንዲሠራ አዘዘው። 7 ዳዊት ልጁን ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “እኔ በበኩሌ ለአምላኬ ለይሖዋ ስም፣ ቤት ለመሥራት ከልብ ተመኝቼ ነበር።+ 8 ሆኖም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ ‘አንተ እጅግ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ታላላቅ ጦርነቶችንም አድርገሃል። በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ስላፈሰስክ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም።+ 9 እነሆ፣ የሰላም* ሰው የሚሆን ወንድ ልጅ ትወልዳለህ፤+ በዙሪያውም ካሉት ጠላቶቹ በሙሉ እረፍት እሰጠዋለሁ፤+ ስሙ ሰለሞን*+ ይባላልና፤ በእሱም ዘመን ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ እሰጣለሁ።+ 10 ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው።+ እሱ ልጄ ይሆናል፤ እኔም አባቱ እሆናለሁ።+ የንግሥናውን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’+
11 “አሁንም ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ ከአንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አንተም በተናገረው መሠረት ተሳክቶልህ የአምላክህን የይሖዋን ቤት ለመሥራት ያብቃህ።+ 12 ብቻ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ሲሾምህ የአምላክህን የይሖዋን ሕግ እንድትጠብቅ+ የማመዛዘንና የማስተዋል ችሎታ ይስጥህ።+ 13 ደግሞም ይሖዋ እስራኤልን በተመለከተ ሙሴን ያዘዘውን ሥርዓትና+ ድንጋጌ በጥንቃቄ ብትጠብቅ ይሳካልሃል።+ ደፋርና ብርቱ ሁን። አትፍራ ወይም አትሸበር።+ 14 እነሆ፣ እኔ ለይሖዋ ቤት 100,000 ታላንት* ወርቅና 1,000,000 ታላንት ብር እንዲሁም ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የማይችል መዳብና ብረት+ ለማዘጋጀት ብዙ ደክሜአለሁ፤ ደግሞም ሳንቃና ድንጋይ አዘጋጅቻለሁ፤+ አንተም በዚያ ላይ ትጨምርበታለህ። 15 ከአንተም ጋር ብዙ ሠራተኞች፣ ድንጋይ ጠራቢዎች፣ ግንበኞች፣+ አናጺዎችና በተለያዩ ሙያዎች የተካኑ ሠራተኞች አሉ።+ 16 ወርቁ፣ ብሩ፣ መዳቡና ብረቱ ስፍር ቁጥር የለውም።+ በል ሥራውን ጀምር፤ ይሖዋም ከአንተ ጋር ይሁን።”+
17 ከዚያም ዳዊት የእስራኤል መኳንንት ሁሉ ልጁን ሰለሞንን እንዲረዱት እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 18 “አምላካችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር አይደለም? በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉስ እረፍት አልሰጣችሁም? የምድሪቱን ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና፤ ምድሪቱም በይሖዋና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለች። 19 አሁንም በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ* አምላካችሁን ይሖዋን ጠይቁ፤+ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦትና የእውነተኛውን አምላክ የተቀደሱ ዕቃዎች+ ለይሖዋ ስም+ ወደሚሠራው ቤት እንድታመጡ የእውነተኛውን አምላክ የይሖዋን መቅደስ መሥራት ጀምሩ።”+
23 ዳዊት በሸመገለና የሕይወቱ ፍጻሜ በተቃረበ* ጊዜ ልጁን ሰለሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።+ 2 ከዚያም የእስራኤልን መኳንንት፣ ካህናቱንና+ ሌዋውያኑን+ ሁሉ ሰበሰበ። 3 ዕድሜያቸው 30 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሌዋውያን ተቆጠሩ፤+ እያንዳንዱ ወንድ በነፍስ ወከፍ ሲቆጠር 38,000 ነበር። 4 ከእነዚህም መካከል 24,000ዎቹ የይሖዋን ቤት ሥራ በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር፤ በተጨማሪም 6,000 አለቆችና ዳኞች ነበሩ፤+ 5 ደግሞም 4,000 በር ጠባቂዎች+ እንዲሁም ዳዊት “ውዳሴ ለማቅረብ የሠራኋቸው ናቸው” ባላቸው መሣሪያዎች ለይሖዋ ውዳሴ+ የሚያቀርቡ 4,000 ሰዎች ነበሩ።
6 ከዚያም ዳዊት በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀአት እና በሜራሪ+ ምድብ አደራጃቸው።*+ 7 ከጌድሶናውያን ወገን ላዳን እና ሺምአይ ነበሩ። 8 የላዳን ወንዶች ልጆች መሪው የሂኤል፣ ዜታም እና ኢዩኤል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። 9 የሺምአይ ወንዶች ልጆች ሸሎሞት፣ ሃዚኤል እና ካራን ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ። እነዚህ የላዳን ወገን የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ። 10 የሺምአይ ወንዶች ልጆች ያሃት፣ ዚና፣* የኡሽ እና በሪአ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሺምአይ ወንዶች ልጆች ነበሩ። 11 መሪው ያሃት ነበር፤ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛህ ነበር። የኡሽ እና በሪአ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች ስላልነበሯቸው በአንድ የሥራ መደብ እንደ አንድ የአባቶች ቤት ሆነው ተቆጠሩ።
12 የቀአት ወንዶች ልጆች አምራም፣ ይጽሃር፣+ ኬብሮን እና ዑዚኤል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ አራት ነበሩ። 13 የአምራም ወንዶች ልጆች አሮን+ እና ሙሴ+ ነበሩ። ሆኖም አሮንና ወንዶች ልጆቹ ቅድስተ ቅዱሳኑን እንዲቀድሱ፣ በይሖዋ ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ እሱን እንዲያገለግሉና ምንጊዜም በስሙ እንዲባርኩ+ በቋሚነት ተለይተው ነበር።+ 14 የእውነተኛው አምላክ ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆች የሌዋውያን ነገድ ክፍል ሆነው ተቆጠሩ። 15 የሙሴ ወንዶች ልጆች ጌርሳም+ እና ኤሊዔዘር+ ነበሩ። 16 ከጌርሳም ወንዶች ልጆች መካከል መሪው ሸቡኤል*+ ነበር። 17 ከኤሊዔዘር ዘሮች* መካከል መሪው ረሃቢያህ+ ነበር፤ ኤሊዔዘር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ይሁንና የረሃብያህ ወንዶች ልጆች እጅግ ብዙ ነበሩ። 18 ከይጽሃር+ ወንዶች ልጆች መካከል መሪው ሸሎሚት+ ነበር። 19 የኬብሮን ወንዶች ልጆች መሪ የሆነው የሪያ፣ ሁለተኛው አማርያህ፣ ሦስተኛው ያሃዚኤል እና አራተኛው የቃምአም+ ነበሩ። 20 የዑዚኤል ወንዶች ልጆች+ መሪ የሆነው ሚክያስ እና ሁለተኛው ይሽሺያህ ነበሩ።
21 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ።+ የማህሊ ወንዶች ልጆች አልዓዛር እና ቂስ ነበሩ። 22 ሆኖም አልዓዛር ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። በመሆኑም ዘመዶቻቸው* የቂስ ልጆች አገቧቸው። 23 የሙሺ ወንዶች ልጆች ማህሊ፣ ኤዴር እና የሬሞት ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ።
24 በአባቶቻቸው ቤት ይኸውም በአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ተቆጥረውና በስም ተዘርዝረው የተመዘገቡት በይሖዋ ቤት ያለውን አገልግሎት ያከናውኑ የነበሩ 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው የሌዊ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። 25 ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡ እረፍት ሰጥቷል፤+ እሱም በኢየሩሳሌም ለዘላለም ይኖራል።+ 26 ሌዋውያኑም የማደሪያ ድንኳኑን ወይም በውስጡ ያሉትን ለአምልኮ የሚያገለግሉ ዕቃዎች ሁሉ መሸከም አያስፈልጋቸውም።”+ 27 ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት ከሌዊ ልጆች መካከል የተቆጠሩት 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች እነዚህ ነበሩ። 28 የሌዋውያኑ ተግባር በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ይኸውም ቅጥር ግቢዎቹንና+ የመመገቢያ ክፍሎቹን፣ ቅዱስ የሆነውን ነገር ሁሉ የማንጻቱን ሥራና በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚከናወኑትን አስፈላጊ ሥራዎች ሁሉ ኃላፊነት ወስደው በመሥራት የአሮንን ልጆች+ መርዳት ነበር። 29 ደግሞም የሚነባበረውን ዳቦ፣*+ ለእህል መባ የሚያገለግለውን የላመ ዱቄት፣ እርሾ ያልገባበትን ስስ ቂጣ፣+ በምጣድ የሚጋገረውን ቂጣና በዘይት የሚለወሰውን ሊጥ+ በማዘጋጀት እንዲሁም ከሁሉም ዓይነት መለኪያዎችና መስፈሪያዎች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በማከናወን ያግዟቸው ነበር። 30 ለይሖዋ ምስጋናና ውዳሴ ለማቅረብ ጠዋት ጠዋትም+ ሆነ ማታ ማታ+ ይቆሙ ነበር። 31 ሕጉ በሚያዘው ቁጥር መሠረት ዘወትር በይሖዋ ፊት በየሰንበቱ፣+ በየወር መባቻውና+ በበዓላት ወቅት+ ለይሖዋ የሚቃጠል መሥዋዕት በቀረበ ጊዜ ሁሉ ያግዟቸው ነበር። 32 በተጨማሪም በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ከመገናኛ ድንኳኑ፣ ከቅዱሱ ስፍራና ወንድሞቻቸው ከሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ጋር በተያያዘ ያሉባቸውን ኃላፊነቶች ይወጡ ነበር።
24 የአሮን ዘሮች ምድብ ይህ ነበር፦ የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብ፣ አቢሁ፣+ አልዓዛር እና ኢታምር+ ነበሩ። 2 ይሁንና ናዳብ እና አቢሁ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤+ ወንዶች ልጆችም አልነበሯቸውም፤ አልዓዛር+ እና ኢታምር ግን ካህናት ሆነው ማገልገላቸውን ቀጠሉ። 3 ዳዊት፣ ከአልዓዛር ወንዶች ልጆች አንዱ ከሆነው ከሳዶቅ+ እንዲሁም ከኢታምር ወንዶች ልጆች አንዱ ከሆነው ከአሂሜሌክ ጋር ሆኖ የአሮንን ዘሮች በተሰጣቸው የአገልግሎት ኃላፊነት መሠረት መደባቸው። 4 የአልዓዛር ወንዶች ልጆች፣ ከኢታምር ወንዶች ልጆች ይልቅ ብዙ መሪዎች ስለነበሯቸው መሪዎቹን በዚሁ መሠረት መደቧቸው፦ የአልዓዛር ወንዶች ልጆች የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑ 16 መሪዎች፣ የኢታምር ወንዶች ልጆች ደግሞ የየአባቶቻቸው ቤት መሪዎች የሆኑ 8 መሪዎች ነበሯቸው።
5 በተጨማሪም ከአልዓዛር ወንዶች ልጆችም ሆነ ከኢታምር ወንዶች ልጆች መካከል በቅዱሱ ስፍራ የሚያገለግሉ አለቆችና እውነተኛውን አምላክ የሚያገለግሉ አለቆች ስለነበሩ አንደኛውን ቡድን ከሌላው ቡድን ጋር በዕጣ+ መደቧቸው። 6 ከዚያም የሌዋውያን ጸሐፊ የሆነው የናትናኤል ልጅ ሸማያህ በንጉሡ፣ በመኳንንቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣+ በአብያታር+ ልጅ በአሂሜሌክ+ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤት መሪዎች ፊት ስማቸውን መዘገበ፤ አንድ የአባቶች ቤት ከአልዓዛር ወገን ሲመረጥ፣ አንድ የአባቶች ቤት ደግሞ ከኢታምር ወገን ተመረጠ።
7 የመጀመሪያው ዕጣ ለየሆያሪብ ወጣ፤ ሁለተኛው ለየዳያህ፣ 8 ሦስተኛው ለሃሪም፣ አራተኛው ለሰኦሪም፣ 9 አምስተኛው ለማልኪያህ፣ ስድስተኛው ለሚያሚን፣ 10 ሰባተኛው ለሃቆጽ፣ ስምንተኛው ለአቢያህ፣+ 11 ዘጠነኛው ለየሹዋ፣ አሥረኛው ለሸካንያህ፣ 12 አሥራ አንደኛው ለኤልያሺብ፣ አሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣ 13 አሥራ ሦስተኛው ለሁፓ፣ አሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፣ 14 አሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፣ አሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፣ 15 አሥራ ሰባተኛው ለሄዚር፣ አሥራ ስምንተኛው ለሃፒጼጽ፣ 16 አሥራ ዘጠነኛው ለፐታያህ፣ ሃያኛው ለየሄዝቄል፣ 17 ሃያ አንደኛው ለያኪን፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣ 18 ሃያ ሦስተኛው ለደላያህ እና ሃያ አራተኛው ለማአዝያህ ወጣ።
19 የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት አባታቸው አሮን ወደ ይሖዋ ቤት ሲገቡ የአገልግሎት ኃላፊነታቸውን+ የሚያከናውኑበትን ሥርዓት በተመለከተ ያወጣው ደንብ ይህ ነበር።
20 ከቀሩት ሌዋውያን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ ከአምራም+ ወንዶች ልጆች መካከል ሹባኤል፤+ ከሹባኤል ወንዶች ልጆች መካከል የህድያ፤ 21 ከረሃቢያህ፦+ ከረሃቢያህ ወንዶች ልጆች መካከል፣ መሪ የሆነው ይሽሺያህ፤ 22 ከይጽሃራውያን መካከል ሸሎሞት፤+ ከሸሎሞት ወንዶች ልጆች መካከል ያሃት፤ 23 ከኬብሮን ወንዶች ልጆች መካከል፣ መሪ የሆነው የሪያ፣+ ሁለተኛው አማርያህ፣ ሦስተኛው ያሃዚኤል እና አራተኛው የቃምአም፤ 24 ከዑዚኤል ወንዶች ልጆች መካከል ሚክያስ፤ ከሚክያስ ወንዶች ልጆች መካከል ሻሚር። 25 ይሽሺያህ የሚክያስ ወንድም ነበር፤ ከይሽሺያህ ወንዶች ልጆች መካከል ዘካርያስ።
26 የሜራሪ+ ወንዶች ልጆች ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ፤ የያአዚያሁ ልጅ ቤኖ። 27 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፦ ከያአዚያሁ ልጆች መካከል ቤኖ፣ ሾሃም፣ ዛኩር እና ኢብሪ፤ 28 ከማህሊ ልጆች መካከል አልዓዛር፤ እሱ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤+ 29 ከቂስ፦ የቂስ ልጅ የራህምኤል፤ 30 የሙሺ ወንዶች ልጆች ማህሊ፣ ኤዴር እና የሪሞት ነበሩ።
በአባቶቻቸው ቤት መሠረት የተዘረዘሩት የሌዊ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ። 31 እነሱም ወንድሞቻቸው የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች እንዳደረጉት በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአሂሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤት መሪዎች ፊት ዕጣ+ ጣሉ። በዚህ ረገድ በመሪው አባት ቤት ወይም በትልቁ ቤተሰብ መሪና በታናሽ ወንድሙ አባት ቤት ወይም በአነስተኛው ቤተሰብ መሪ መካከል ምንም ልዩነት አልነበረም።
25 በተጨማሪም ዳዊትና የአገልግሎት ቡድኖቹ አለቆች በበገና፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና+ በሲምባል+ ትንቢት በመናገር እንዲያገለግሉ ከአሳፍ፣ ከሄማን እና ከየዱቱን+ ወንዶች ልጆች መካከል አንዳንዶቹን ለዩ። ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑት ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ 2 ከአሳፍ ወንዶች ልጆች መካከል ዛኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያህ እና አሼርዔላ፤ እነዚህ በአሳፍ አመራር ሥር ያሉ የአሳፍ ወንዶች ልጆች ሲሆኑ በንጉሡ አመራር ሥር ሆነው ትንቢት ይናገሩ ነበር። 3 ከየዱቱን፣+ የየዱቱን ወንዶች ልጆች፦ ጎዶልያስ፣ ጸሪ፣ የሻያህ፣ ሺምአይ፣ ሃሻብያህ እና ማቲትያህ፤+ እነዚህ ስድስቱ በአባታቸው በየዱቱን አመራር ሥር ሲሆኑ ይሖዋን እያመሰገኑና እያወደሱ+ በበገና ትንቢት ይናገሩ ነበር። 4 ከሄማን፣+ የሄማን ወንዶች ልጆች፦ ቡቂያ፣ ማታንያህ፣ ዑዚኤል፣ ሸቡኤል፣* የሪሞት፣ ሃናንያህ፣ ሃናኒ፣ ኤሊዓታህ፣ ጊዳልቲ፣ ሮማምቲኤዘር፣ ዮሽበቃሻ፣ ማሎቲ፣ ሆቲር እና ማሃዚዮት። 5 እነዚህ ሁሉ የሄማን ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ እሱም ለአምላክ ክብር ያመጣ ዘንድ* የእውነተኛውን አምላክ ቃል የሚገልጽ የንጉሡ ባለ ራእይ ነበር፤ እውነተኛውም አምላክ ለሄማን 14 ወንዶች ልጆችና 3 ሴቶች ልጆች ሰጠው። 6 እነዚህ ሁሉ በእውነተኛው አምላክ ቤት ለሚቀርበው አገልግሎት በአባታቸው አመራር ሥር ሆነው በሲምባል፣ በባለ አውታር መሣሪያዎችና በበገና+ በይሖዋ ቤት ይዘምሩ ነበር።
አሳፍ፣ የዱቱን እና ሄማን በንጉሡ አመራር ሥር ነበሩ።
7 የእነሱና ለይሖዋ በሚቀርበው መዝሙር የሠለጠኑት ወንድሞቻቸው ይኸውም በዚህ የተካኑት ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 288 ነበር። 8 በመሆኑም ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ታናሽም ሆነ ታላቅ፣ በሙያው የተካነም ሆነ ተማሪ ሳይባል ሁሉም ዕጣ+ ተጣጣሉ።
9 የመጀመሪያው ዕጣ ለአሳፍ ልጅ ለዮሴፍ+ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎዶልያስ+ ወጣ (እሱና ወንድሞቹ እንዲሁም ወንዶች ልጆቹ 12 ነበሩ)፤ 10 ሦስተኛው ለዛኩር፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 11 አራተኛው ለይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 12 አምስተኛው ለነታንያህ፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 13 ስድስተኛው ለቡቂያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 14 ሰባተኛው ለየሳርኤላ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 15 ስምንተኛው ለየሻያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 16 ዘጠነኛው ለማታንያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 17 አሥረኛው ለሺምአይ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 18 አሥራ አንደኛው ለአዛርዔል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 19 አሥራ ሁለተኛው ለሃሻብያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 20 አሥራ ሦስተኛው ለሹባኤል፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 21 አሥራ አራተኛው ለማቲትያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 22 አሥራ አምስተኛው ለየሬሞት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 23 አሥራ ስድስተኛው ለሃናንያህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 24 አሥራ ሰባተኛው ለዮሽበቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 25 አሥራ ስምንተኛው ለሃናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 26 አሥራ ዘጠነኛው ለማሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 27 ሃያኛው ለኤሊዓታህ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 28 ሃያ አንደኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 29 ሃያ ሁለተኛው ለጊዳልቲ፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 30 ሃያ ሦስተኛው ለማሃዚዮት፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር፤ 31 ሃያ አራተኛው ለሮማምቲኤዘር፣+ ለወንዶች ልጆቹና ለወንድሞቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 ነበር።
26 የበር ጠባቂዎቹ+ ምድብ እንደሚከተለው ነው፦ ከቆሬያውያን መካከል ከአሳፍ ልጆች አንዱ የሆነው የቆረ ልጅ መሺሌሚያህ።+ 2 መሺሌሚያህም ወንዶች ልጆች ነበሩት፦ የበኩር ልጁ ዘካርያስ፣ ሁለተኛው የዲአዔል፣ ሦስተኛው ዘባድያህ፣ አራተኛው ያትንኤል፣ 3 አምስተኛው ኤላም፣ ስድስተኛው የሆሃናን እና ሰባተኛው ኤሊየሆዔናይ። 4 ኦቤድዔዶምም ወንዶች ልጆች ነበሩት፦ የበኩር ልጁ ሸማያህ፣ ሁለተኛው የሆዛባድ፣ ሦስተኛው ዮአስ፣ አራተኛው ሳካር፣ አምስተኛው ናትናኤል፣ 5 ስድስተኛው አሚዔል፣ ሰባተኛው ይሳኮር እና ስምንተኛው ፐኡልታይ፤ አምላክ እነዚህን ልጆች በመስጠት ኦቤድዔዶምን ባረከው።
6 ልጁም ሸማያህ ልጆች ወለደ፤ እነሱም ብቃት ያላቸውና ኃያላን ነበሩ፤ የየቤተሰባቸውም መሪ ሆኑ። 7 የሸማያህ ወንዶች ልጆች ኦትኒ፣ ረፋኤል፣ ኢዮቤድ እና ኤልዛባድ ነበሩ፤ የኤልዛባድ ወንድሞች የሆኑት ኤሊሁ እና ሰማክያህም ብቃት ያላቸው ሰዎች ነበሩ። 8 እነዚህ ሁሉ የኦቤድዔዶም ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ እነሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው አገልግሎቱን ለማከናወን ችሎታና ብቃት ያላቸው ሰዎች ነበሩ፤ ከኦቤድዔዶም ወገን 62 ነበሩ። 9 መሺሌሚያህም+ ብቃት ያላቸው ወንዶች ልጆችና ወንድሞች ነበሩት፤ እነሱም 18 ነበሩ። 10 የሜራሪ ልጅ የሆነው ሆሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት። ሺምሪ የበኩር ልጅ ባይሆንም እንኳ አባቱ የቤተሰቡ መሪ አድርጎ ሾመው፤ 11 ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ተባልያህ እና አራተኛው ዘካርያስ ነበሩ። የሆሳ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች በአጠቃላይ 13 ነበሩ።
12 የበር ጠባቂዎቹ ምድብ መሪዎች ልክ እንደ ወንድሞቻቸው በይሖዋ ቤት በሚቀርበው አገልግሎት የሚያከናውኑት ሥራ ነበራቸው። 13 በመሆኑም ለእያንዳንዱ በር፣ ትንሽ ትልቅ ሳይባል ለሁሉም በየአባቶቻቸው ቤት ዕጣ+ ተጣለ። 14 ከዚያም የምሥራቁ በር ዕጣ ለሸሌምያህ ወጣ። አስተዋይ መካሪ ለሆነው ለልጁ ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ በዕጣውም መሠረት የሰሜን በር ደረሰው። 15 ኦቤድዔዶም በደቡብ በኩል ያለው በር ደረሰው፤ ወንዶች ልጆቹ+ ደግሞ ግምጃ ቤቶቹ ደረሷቸው። 16 ሹፒም እና ሆሳ+ በአቀበቱ መንገድ ባለው በሻለከት በር አቅራቢያ የሚገኘው የምዕራብ በር ደረሳቸው፤ የዘብ ጠባቂ ቡድኖቹ ጎን ለጎን ቆመው ይጠብቁ ነበር፤ 17 በምሥራቅ በኩል ስድስት ሌዋውያን ነበሩ፤ በሰሜን በኩል በየቀኑ አራት፣ በደቡብ በኩል በየቀኑ አራት እንዲሁም ግምጃ ቤቶቹን+ ሁለት ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር፤ 18 በምዕራብ በኩል ባለው መተላለፊያ በጎዳናው+ ላይ አራት፣ በመተላለፊያው ላይ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር። 19 የቆሬያውያንና የሜራራውያን ወንዶች ልጆች የበር ጥበቃ ምድብ ይህ ነበር።
20 ከሌዋውያን መካከል አኪያህ በእውነተኛው አምላክ ቤት የሚገኙት ግምጃ ቤቶችና ቅዱስ የሆኑ ነገሮች* ያሉባቸው ግምጃ ቤቶች ኃላፊ ነበር።+ 21 የላዳን ወንዶች ልጆች፦ የላዳን ወገን ከሆኑት ከጌድሶናውያን ወንዶች ልጆች ማለትም የጌድሶናዊው የላዳን ወገን ከሆኑት የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች መካከል የሂኤሊ+ 22 እንዲሁም የየሂኤሊ ወንዶች ልጆች ዜታምና ወንድሙ ኢዩኤል ነበሩ። እነሱም በይሖዋ ቤት የሚገኙት ግምጃ ቤቶች+ ኃላፊዎች ነበሩ። 23 ከአምራማውያን፣ ከይጽሃራውያን፣ ከኬብሮናውያን እና ከዑዚኤላውያን+ መካከል፣ 24 የሙሴ ልጅ፣ የጌርሳም ልጅ ሸቡኤል የግምጃ ቤቶቹ ኃላፊ ነበር። 25 የኤሊዔዘር+ ዘሮች የሆኑት ወንድሞቹ ረሃቢያህ፣+ የሻያህ፣ ዮራም፣ ዚክሪ እና ሸሎሞት ነበሩ። 26 ሸሎሞትና ወንድሞቹ ንጉሥ ዳዊት፣+ የአባቶች ቤት መሪዎች፣+ የሺህ አለቆቹ፣ የመቶ አለቆቹና የሠራዊቱ አለቆች የቀደሷቸው ቅዱስ ነገሮች+ የሚገኙባቸው ግምጃ ቤቶች ሁሉ ኃላፊዎች ነበሩ። 27 የይሖዋን ቤት ለማደስ በጦርነት+ ከተገኘው ምርኮ+ ውስጥ የተወሰነውን ቀደሱ፤ 28 በተጨማሪም ባለ ራእዩ+ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አበኔር+ እና የጽሩያ+ ልጅ ኢዮዓብ+ የቀደሷቸውን ነገሮች ሁሉ በኃላፊነት ይይዙ ነበር። ማንኛውም ሰው የቀደሰው ነገር በሸሎሚት* እና በወንድሞቹ እጅ ይሆን ነበር።
29 ከይጽሃራውያን+ መካከል ኬናንያ እና ወንዶች ልጆቹ ከአምላክ ቤት ውጭ ባለው የአስተዳደር ሥራ ላይ በእስራኤል አለቆችና ዳኞች+ ሆነው ተመደቡ።
30 ከኬብሮናውያን+ መካከል ብቁ የሆኑት ሃሻብያህ እና ወንድሞቹ 1,700 ነበሩ፤ እነሱም ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ባለው የእስራኤል ምድር ከይሖዋ ሥራ ሁሉና ከንጉሡ አገልግሎት ጋር በተያያዘ የማስተዳደር ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር። 31 የሪያህ+ የኬብሮናውያን አባቶች ቤቶችና ቤተሰቦች መሪ ነበር። በዳዊት ዘመነ መንግሥት 40ኛ ዓመት+ ምርመራ ተካሄደ፤ በእነሱም መካከል በጊልያድ፣ ያዜር+ በተባለ ቦታ ኃያላን የሆኑና ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ። 32 የአባቶች ቤቶች መሪዎች የሆኑ ብቃት ያላቸው ወንድሞቹ 2,700 ነበሩ። በመሆኑም ንጉሥ ዳዊት ከእውነተኛው አምላክና ከንጉሡ ጉዳዮች ሁሉ ጋር በተያያዘ በሮቤላውያን፣ በጋዳውያንና በምናሴያውያን ነገድ እኩሌታ ላይ ሾማቸው።
27 የእስራኤላውያን ቁጥር ይኸውም የአባቶች ቤቶች መሪዎች፣ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆችና+ ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚገቡትንም ሆነ የሚወጡትን ምድቦች በመምራት ንጉሡን የሚያገለግሉት+ አለቆቻቸው ቁጥር ይህ ነው፤ በእያንዳንዱ ምድብ 24,000 ነበሩ።
2 በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ምድብ አዛዥ የዛብድኤል ልጅ ያሾብአም+ ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 3 እሱ ከፋሬስ+ ወንዶች ልጆች መካከል በመጀመሪያው ወር እንዲያገለግሉ የተመደቡት የቡድኖቹ አለቆች ሁሉ መሪ ነበር። 4 አሆሐያዊው+ ዶዳይ+ የሁለተኛው ወር ምድብ አዛዥ ነበር። መሪው ሚቅሎት ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 5 በሦስተኛው ወር እንዲያገለግል የተመደበው የሦስተኛው ቡድን አዛዥ የካህናት አለቃው የዮዳሄ+ ልጅ በናያህ+ ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 6 በናያህ ከሠላሳዎቹ ኃያላን ተዋጊዎች አንዱ የነበረ ሲሆን የሠላሳዎቹ አለቃ ነበር፤ ልጁ አሚዛባድም በእሱ ምድብ ውስጥ የበላይ ነበር። 7 በአራተኛው ወር፣ አራተኛው አዛዥ የኢዮዓብ ወንድም+ አሳሄል+ ሲሆን ልጁ ዘባድያህ የእሱ ተተኪ ነበር፤ በምድቡም ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 8 በአምስተኛው ወር፣ አምስተኛው አዛዥ ይዝራሃዊው ሻምሁት ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 9 በስድስተኛው ወር፣ ስድስተኛው አዛዥ የተቆአዊው+ የኢቄሽ ልጅ ኢራ+ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 10 በሰባተኛው ወር፣ ሰባተኛው አዛዥ ከኤፍሬማውያን ወገን የሆነው ጴሎናዊው ሄሌጽ+ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 11 በስምንተኛው ወር፣ ስምንተኛው አዛዥ ከዛራውያን+ ወገን የሆነው ሁሻዊው ሲበካይ+ ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 12 በዘጠነኛው ወር፣ ዘጠነኛው አዛዥ ከቢንያማውያን ወገን የሆነው አናቶታዊው+ አቢዔዜር+ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 13 በአሥረኛው ወር፣ አሥረኛው አዛዥ ከዛራውያን+ ወገን የሆነው ነጦፋዊው ማህራይ+ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 14 በ11ኛው ወር፣ 11ኛው አዛዥ ከኤፍሬም ልጆች ወገን የሆነው ጲራቶናዊው በናያህ+ ነበር፤ በእሱም ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ። 15 በ12ኛው ወር፣ 12ኛው አዛዥ ከኦትኒኤል ቤተሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሄልዳይ ሲሆን በእሱ ምድብ ውስጥ 24,000 ሰዎች ነበሩ።
16 የእስራኤል ነገዶች መሪዎች እነዚህ ናቸው፦ ከሮቤላውያን የዚክሪ ልጅ ኤሊዔዘር መሪ ነበር፤ ከስምዖናውያን የማአካ ልጅ ሰፋጥያህ፤ 17 ከሌዊ የቀሙኤል ልጅ ሃሻብያህ፤ ከአሮን ቤተሰብ ሳዶቅ፤ 18 ከይሁዳ ከዳዊት ወንድሞች አንዱ የሆነው ኤሊሁ፤+ ከይሳኮር የሚካኤል ልጅ ኦምሪ፤ 19 ከዛብሎን የአብድዩ ልጅ ይሽማያህ፤ ከንፍታሌም የአዝርዔል ልጅ የሪሞት፤ 20 ከኤፍሬማውያን መካከል የአዛዝያ ልጅ ሆሺአ፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ የፐዳያህ ልጅ ኢዩኤል፤ 21 በጊልያድ ካለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ የዘካርያስ ልጅ ኢዶ፤ ከቢንያም የአበኔር+ ልጅ ያአሲዔል፤ 22 ከዳን የየሮሃም ልጅ አዛርዔል። እነዚህ የእስራኤል ነገዶች አለቆች ነበሩ።
23 ይሖዋ እስራኤልን በሰማያት እንዳሉ ከዋክብት እንደሚያበዛ ቃል ገብቶ ስለነበር ዳዊት 20 ዓመትና ከዚያ በታች የሆናቸውን አልቆጠረም።+ 24 የጽሩያ ልጅ ኢዮዓብ ቆጠራውን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም አልፈጸመውም። የአምላክ ቁጣ በእስራኤል ላይ ስለነደደ*+ በንጉሥ ዳዊት ዘመን ስለተከናወኑት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ ዘገባ ላይ ቁጥሩ አልሰፈረም።
25 የአዲዔል ልጅ አዝማዌት በንጉሡ ግምጃ ቤቶች+ ላይ ተሹሞ ነበር። የዖዝያ ልጅ ዮናታን ደግሞ በገጠሩ፣ በከተሞቹ፣ በመንደሮቹና በማማዎቹ ውስጥ በሚገኙት ግምጃ ቤቶች ላይ ተሹሞ ነበር። 26 የከሉብ ልጅ ኤዝሪ መሬቱን ለማልማት በመስክ በሚሠሩት ሠራተኞች ላይ ተሹሞ ነበር። 27 ራማዊው ሺምአይ በወይን እርሻዎቹ ላይ ተሹሞ ነበር፤ ሲፍሞታዊው ዛብዲ ለወይን ጠጅ አቅርቦት በሚውለው የወይን እርሻዎቹ ምርት ላይ ተሹሞ ነበር። 28 ጌዴራዊው ባአልሀናን በሸፌላ+ በነበሩት የወይራ ዛፎችና የሾላ ዛፎች+ ላይ ተሹሞ ነበር፤ ዮአስ ደግሞ በዘይት ማከማቻዎቹ ላይ ተሹሞ ነበር። 29 ሳሮናዊው ሺጥራይ በሳሮን+ የግጦሽ መሬት በሚሰማሩት ከብቶች ላይ ተሹሞ ነበር፤ የአድላይ ልጅ ሻፋጥ ደግሞ በሸለቋማ ሜዳዎቹ* ላይ በሚሰማሩት ከብቶች ላይ ተሹሞ ነበር። 30 እስማኤላዊው ኦቢል በግመሎቹ ላይ ተሹሞ ነበር፤ መሮኖታዊው የህድያ በአህዮቹ* ላይ ተሹሞ ነበር። 31 አጋራዊው ያዚዝ በመንጎቹ ላይ ተሹሞ ነበር። እነዚህ ሁሉ በንጉሥ ዳዊት ንብረት ላይ የተሾሙ አለቆች ነበሩ።
32 የዳዊት የወንድሙ ልጅ ዮናታን+ አስተዋይ የሆነ አማካሪና ጸሐፊ ነበር፤ የሃክሞኒ ልጅ የሂኤል የንጉሡ ልጆች ተንከባካቢ ነበር።+ 33 አኪጦፌል+ የንጉሡ አማካሪ ነበር፤ አርካዊው ኩሲ+ ደግሞ የንጉሡ ወዳጅ* ነበር። 34 ከአኪጦፌል በኋላ አማካሪ ሆነው የተሾሙት የበናያህ+ ልጅ ዮዳሄ እና አብያታር+ ነበሩ፤ ኢዮዓብ+ ደግሞ የንጉሡ ሠራዊት ዋና አዛዥ ነበር።
28 ዳዊት የእስራኤልን መኳንንት ሁሉ ይኸውም የነገዶቹን አለቆች፣ ንጉሡን በሚያገለግሉት ምድቦች ላይ የተሾሙትን አለቆች፣+ የሺህ አለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን+ እንዲሁም በንጉሡና በልጆቹ ንብረትም ሆነ መንጋ ሁሉ ላይ የተሾሙትን አለቆች+ ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ፣ ከኃያላኑና ብቃት ካላቸው ሰዎች+ ሁሉ ጋር በኢየሩሳሌም ሰበሰባቸው። 2 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ተነስቶ እንዲህ አለ፦
“ወንድሞቼና ወገኖቼ ሆይ፣ ስሙኝ። እኔ ለይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ማረፊያና ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ የሚሆን ቤት ለመሥራት ከልቤ ተመኝቼ ነበር፤+ ደግሞም ይህን ቤት ለመሥራት ዝግጅት አድርጌ ነበር።+ 3 እውነተኛው አምላክ ግን ‘ብዙ ጦርነት ስላካሄድክና ደም ስላፈሰስክ ለስሜ የሚሆን ቤት አትሠራም’ አለኝ።+ 4 ይሁንና የእስራኤል አምላክ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ለዘላለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መረጠኝ፤+ መሪ እንዲሆን የመረጠው ይሁዳን ነውና፤+ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት፣+ ከአባቴም ወንዶች ልጆች መካከል በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ እኔን መረጠ።+ 5 ይሖዋ ከሰጠኝ ብዙ ወንዶች ልጆች+ መካከል ደግሞ በይሖዋ የንግሥና ዙፋን ላይ ተቀምጦ እስራኤልን እንዲገዛ ልጄን ሰለሞንን+ መርጦታል።+
6 “እንዲህም አለኝ፦ ‘ቤቴንና ቅጥር ግቢዎቼን የሚሠራው ልጅህ ሰለሞን ነው፤ እሱን እንደ ልጄ አድርጌ መርጬዋለሁና፤ እኔም አባቱ እሆናለሁ።+ 7 አሁን እያደረገ እንዳለው ትእዛዛቴንና ድንጋጌዎቼን+ ሳያወላውል የሚፈጽም ከሆነ ንግሥናውን ለዘላለም አጸናለሁ።’+ 8 በመሆኑም የይሖዋ ጉባኤ በሆነው በእስራኤል ሁሉ ፊት፣ አምላካችን እየሰማ ይህን እነግራችኋለሁ፦ መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱና+ ከእናንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻችሁ ቋሚ ርስት አድርጋችሁ እንድታወርሱ የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት በሙሉ በጥብቅ ተከተሉ፤ ደግሞም ፈልጉ።
9 “አንተም ልጄ ሰለሞን ሆይ፣ የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በሙሉ ልብና*+ በደስተኛ* ነፍስ* አገልግለው፤ ይሖዋ ልብን ሁሉ ይመረምራልና፤+ ሐሳብንና ውስጣዊ ዝንባሌን ሁሉ ይረዳል።+ ብትፈልገው ይገኝልሃል፤+ ከተውከው ግን ለዘላለም ይተውሃል።+ 10 አሁንም ለመቅደስ የሚሆን ቤት እንድትሠራ ይሖዋ እንደመረጠህ ልብ በል። እንግዲህ ደፋር ሁን፤ ሥራህንም ጀምር።”
11 ከዚያም ዳዊት የበረንዳውን፣+ የመቅደሱን ክፍሎች፣ የግምጃ ቤቶቹን፣ ሰገነት ላይ ያሉትን ክፍሎች፣ የውስጠኛዎቹን ክፍሎችና የስርየት መክደኛው+ የሚቀመጥበትን ክፍል* ንድፍ+ ለልጁ ለሰለሞን ሰጠው። 12 ዳዊት በመንፈስ የተገለጠለትን የይሖዋን ቤት ቅጥር ግቢዎች፣+ በዙሪያው ያሉትን የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉ፣ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ግምጃ ቤቶችና የተቀደሱት ነገሮች*+ የሚቀመጡባቸውን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ለሰለሞን ሰጠው፤ 13 እንዲሁም የካህናቱንና+ የሌዋውያኑን ምድብ፣ በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ሁሉና በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ በተመለከተ መመሪያ ሰጠው፤ 14 በተጨማሪም የወርቁን ይኸውም ለተለያዩ አገልግሎቶች ለሚውሉት ዕቃዎች ሁሉ የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠን፣ የብር ዕቃዎቹን ሁሉ መጠንና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ መጠን አሳወቀው፤ 15 ደግሞም እንደየመቅረዙ አገልግሎት ዓይነት፣ ለወርቅ መቅረዞቹና+ ለወርቅ መብራቶቻቸው ይኸውም ለተለያዩ ዓይነት መቅረዞችና መብራቶቻቸው የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠን እንዲሁም ለብር መቅረዞቹ ማለትም ለእያንዳንዱ መቅረዝና ለመብራቶቹ የሚያስፈልገውን ብር መጠን ገለጸለት፤ 16 በተጨማሪም የሚነባበረው ዳቦ*+ ለሚቀመጥበት ለእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠንና ለብር ጠረጴዛዎቹ የሚያስፈልገውን ብር መጠን አሳወቀው፤ 17 ከንጹሕ ወርቅ ለሚሠሩት ሹካዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖችና ማንቆርቆሪያዎች እንዲሁም ለእያንዳንዱ ትንሽ የወርቅ ጎድጓዳ ሳህን+ የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠንና ለእያንዳንዱ ትንሽ የብር ጎድጓዳ ሳህን የሚያስፈልገውን ብር መጠን ገለጸለት። 18 ደግሞም ለዕጣኑ መሠዊያ+ የሚያስፈልገውን እንዲሁም ለሠረገላው ምስል+ ይኸውም ክንፋቸውን ለሚዘረጉትና የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ለሚሸፍኑት የወርቅ ኪሩቦች+ የሚያስፈልገውን የጠራ ወርቅ መጠን አሳወቀው። 19 ዳዊትም “የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ የግንባታ ንድፉንም+ ዝርዝር በሙሉ በጽሑፍ እንዳሰፍር ማስተዋል ሰጠኝ” አለ።+
20 ከዚያም ዳዊት ልጁን ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤ ሥራህንም ጀምር። አትፍራ ወይም አትሸበር፤ አምላኬ፣ ይሖዋ አምላክ ከአንተ ጋር ነውና።+ በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት አስፈላጊ የሆነው ሥራ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአንተ ጋር ይሆናል እንጂ አይጥልህም ወይም አይተውህም።+ 21 እነሆ፣ በእውነተኛው አምላክ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ሁሉ የሚያስፈልጉት የካህናትና+ የሌዋውያን+ ምድቦች ተዘጋጅተዋል። ማንኛውንም ዓይነት አገልግሎት ለማከናወን ፈቃደኛ የሆኑና የተካኑ ሠራተኞች አሉልህ፤+ መኳንንቱና+ ሕዝቡም ሁሉ መመሪያህን በሙሉ ይፈጽማሉ።”
29 ንጉሥ ዳዊትም ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፦ “አምላክ የመረጠው+ ልጄ ሰለሞን ገና ወጣት ነው፤ ተሞክሮም የለውም፤*+ ሥራው ደግሞ ታላቅ ነው፤ ቤተ መቅደሱ* የሚሠራው ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ አምላክ ነውና።+ 2 እኔም አቅሜ በፈቀደው መጠን ለአምላኬ ቤት በወርቅ ለሚሠራው ወርቅ፣ በብር ለሚሠራው ብር፣ በመዳብ ለሚሠራው መዳብ፣ በብረት ለሚሠራው ብረትና+ በሳንቃ ለሚሠራው ሳንቃ+ እንዲሁም ኦኒክስ ድንጋዮች፣ በማያያዣ የሚጣበቁ ድንጋዮች፣ እንደ ጌጥ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ሕብር ያላቸው ድንጋዮች፣ ማንኛውንም ዓይነት የከበረ ድንጋይና የአልባስጥሮስ ድንጋይ በብዛት አዘጋጅቻለሁ። 3 ከዚህም በላይ ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር+ የተነሳ ለቅዱሱ ቤት አስቀድሞ ካዘጋጀሁት በተጨማሪ የግል ሀብቴ+ የሆነውን ወርቅና ብርም ለአምላኬ ቤት እሰጣለሁ፤ 4 ከዚህም ሌላ የቤቶቹን ግድግዳ ለመለበጥ 3,000 ታላንት* የኦፊር ወርቅና+ 7,000 ታላንት የተጣራ ብር፣ 5 በወርቅ ለሚሠራው ወርቅ፣ በብር ለሚሠራው ብር፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ለሚሠሩትም ሥራ ሁሉ የሚያስፈልገውን እሰጣለሁ። ታዲያ ዛሬ ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ በእጁ ይዞ ለመቅረብ ፈቃደኛ የሆነ ማን ነው?”+
6 በመሆኑም የአባቶች ቤቶች አለቆች፣ የእስራኤል ነገዶች አለቆች፣ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆችና+ የንጉሡን ጉዳይ የሚያስፈጽሙት አለቆች+ በፈቃደኝነት ቀረቡ። 7 ደግሞም ለእውነተኛው አምላክ ቤት አገልግሎት የሚውል 5,000 ታላንት ወርቅ፣ 10,000 ዳሪክ፣* 10,000 ታላንት ብር፣ 18,000 ታላንት መዳብና 100,000 ታላንት ብረት ሰጡ። 8 የከበሩ ድንጋዮች ያለው ሰው ሁሉ ጌድሶናዊው+ የሂኤል+ በኃላፊነት ለሚያስተዳድረው በይሖዋ ቤት ላለው ግምጃ ቤት ሰጠ። 9 ሕዝቡ በፈቃደኝነት መባ በመስጠታቸው እጅግ ተደሰቱ፤ በፈቃደኝነት ተነሳስተው ለይሖዋ መባ የሰጡት በሙሉ ልባቸው ነበርና፤+ ንጉሥ ዳዊትም እጅግ ደስ አለው።
10 ከዚያም ዳዊት በጉባኤው ሁሉ ፊት ይሖዋን አወደሰ። እንዲህም አለ፦ “የአባታችን የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ውዳሴ ይድረስህ። 11 ይሖዋ ሆይ፣ ታላቅነት፣+ ኃያልነት፣+ ውበት፣ ግርማና ሞገስ*+ የአንተ ነው፤ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነው።+ ይሖዋ ሆይ፣ መንግሥት የአንተ ነው።+ ከሁሉም በላይ ከፍ ከፍ ያልክ ራስ ነህ። 12 ሀብትና ክብር ከአንተ ነው፤+ አንተም ሁሉንም ነገር ትገዛለህ፤+ ኃይልና+ ብርታት+ በእጅህ ነው፤ እጅህ ሁሉንም ታላቅ ማድረግና+ ለሁሉም ብርታት መስጠት ይችላል።+ 13 አሁንም አምላካችን ሆይ፣ እናመሰግንሃለን፤ ውብ የሆነውን ስምህንም እናወድሳለን።
14 “ይሁንና በፈቃደኝነት ተነሳስተን እንዲህ ያለ መባ ማቅረብ እንችል ዘንድ እኔም ሆንኩ ሕዝቤ ማን ነን? ሁሉም ነገር የተገኘው ከአንተ ነውና፤ የሰጠንህም ከገዛ እጅህ የተቀበልነውን ነው። 15 እንደ አባቶቻችን ሁሉ እኛም በፊትህ የባዕድ አገር ሰዎችና ሰፋሪዎች ነንና።+ የሕይወት ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤+ ተስፋም የለውም። 16 አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ ለቅዱስ ስምህ ቤት ለመሥራት ያዘጋጀነው ይህ ሁሉ ሀብት የተገኘው ከገዛ እጅህ ነው፤ ሁሉም የአንተ ነው። 17 አምላኬ ሆይ፣ አንተ ልብን እንደምትመረምርና+ በንጹሕ አቋም * ደስ እንደምትሰኝ+ በሚገባ አውቃለሁ። እኔ በልቤ ቅንነት፣ በፈቃደኝነት ተነሳስቼ ይህን ሁሉ ነገር ሰጥቻለሁ፤ ደግሞም እዚህ የተገኘው ሕዝብህ በፈቃደኝነት ተነሳስቶ ለአንተ መባ ሲያቀርብ በማየቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። 18 የአባቶቻችን የአብርሃም፣ የይስሐቅና የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሕዝብ እንዲህ ያለ የፈቃደኝነት መንፈስና ዝንባሌ ይዞ ለዘላለም እንዲኖርና በሙሉ ልቡ እንዲያገለግልህ እርዳው።+ 19 ልጄ ሰለሞንም ትእዛዛትህን፣ ማሳሰቢያዎችህንና ሥርዓቶችህን እንዲጠብቅ+ ሙሉ* ልብ ስጠው፤+ እነዚህን ሁሉ ነገሮች እንዲያደርግና እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ቤተ መቅደስ* እንዲገነባ እርዳው።”+
20 ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ “አሁን፣ አምላካችሁን ይሖዋን አወድሱ” አለ። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን አወደሱ፤ ለይሖዋና ለንጉሡም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ። 21 በማግስቱም ለይሖዋ መሥዋዕት መሠዋታቸውንና ለይሖዋ የሚቃጠል መባ+ ማቅረባቸውን ቀጠሉ፤ 1,000 ወይፈኖች፣ 1,000 አውራ በጎች፣ 1,000 ተባዕት የበግ ጠቦቶችና የመጠጥ መባዎች+ አቀረቡ፤ ስለ እስራኤል ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።+ 22 በዚያ ዕለት በይሖዋ ፊት በታላቅ ደስታ ይበሉና ይጠጡ ነበር፤+ ደግሞም የዳዊትን ልጅ ሰለሞንን ለሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ በይሖዋም ፊት መሪ አድርገው ቀቡት፤+ ሳዶቅንም ካህን አድርገው ቀቡት።+ 23 ሰለሞንም በአባቱ በዳዊት ፋንታ በይሖዋ ዙፋን+ ላይ ንጉሥ ሆኖ ተቀመጠ፤ እሱም ተሳካለት፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ታዘዙለት። 24 መኳንንቱና+ ኃያላን ተዋጊዎቹ+ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ ዳዊት ወንዶች ልጆች+ ሁሉ ለንጉሥ ሰለሞን ተገዙለት። 25 ይሖዋም በእስራኤል ሁሉ ፊት ሰለሞንን እጅግ ታላቅ አደረገው፤ ደግሞም በእስራኤል ከእሱ በፊት የነበሩት ነገሥታት ያላገኙትን ንጉሣዊ ግርማ አጎናጸፈው።+
26 በዚህ መንገድ የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ገዛ፤ 27 በእስራኤልም ላይ ንጉሥ ሆኖ የገዛበት ጊዜ ርዝመት* 40 ዓመት ነበር። በኬብሮን ለ7 ዓመት፣+ በኢየሩሳሌም ደግሞ ለ33 ዓመት ነገሠ።+ 28 እሱም አስደሳች የሆነ ብዙ ዘመን ኖሮ፣+ ዕድሜ* ጠግቦ እንዲሁም ብዙ ሀብትና ክብር አግኝቶ ሞተ፤ ልጁ ሰለሞንም በእሱ ፋንታ ነገሠ።+ 29 የንጉሥ ዳዊት ታሪክ ከመጀመሪያ አንስቶ እስከ መጨረሻ ድረስ፣ ባለ ራእዩ* ሳሙኤል፣ ነቢዩ ናታንና+ ባለ ራእዩ ጋድ+ ባዘጋጇቸው ጽሑፎች ውስጥ ሰፍሯል፤ 30 በተጨማሪም ስለ ንግሥናውና ስለ ኃያልነቱ ሁሉ እንዲሁም ከእሱ፣ ከእስራኤልና በዙሪያው ካሉ መንግሥታት ሁሉ ጋር በተያያዘ ስለተከናወኑት ነገሮች ተጽፏል።
ቀጥሎ የተዘረዘሩት የአራም ወንዶች ልጆች ናቸው። ዘፍ 10:23ን ተመልከት።
“ክፍፍል” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “የምድር ሕዝብ ተከፋፍሎ።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “በእስራኤል ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ሜዳ።”
ቃል በቃል “ሺኮች።” የነገድ አለቃ የሆነ ሰው “ሺክ” ተብሎ ይጠራ ነበር።
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
“መዓት አምጪ፤ ሞገስ የሚያሳጣ” የሚል ትርጉም አለው። ኢያሱ 7:1 ላይ አካን ተብሎም ተጠርቷል።
ወይም “ችግር፤ መጠላት።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
በ1ዜና 2:18, 19, 42 ላይ ካሌብ ተብሎም ተጠርቷል።
በ1ዜና 2:9 ላይ ከሉባይ ተብሎም ተጠርቷል።
ወይም “በዙሪያዋ።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
በ1ዜና 2:9 ላይ ከሉባይ ተብሎም ተጠርቷል።
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ያቤጽ የሚለው ስም “ሥቃይ” የሚል ትርጉም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተዛማጅነት ሳይኖረው አይቀርም።
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
“የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሸለቆ” የሚል ትርጉም አለው።
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
በ1ዜና 4:18 ላይ የተጠቀሰችውን ቢትያን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ወይም “ይህ ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ መረጃ ነው።”
ወይም “ዙሪያ።”
ዳግማዊ ኢዮርብዓምን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ደጋን የሚረግጡና።”
ወይም “የሰው ነፍሳት።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
በ1ዜና 6:1 ላይ ጌድሶን ተብሎም ተጠርቷል።
ወይም “ዘሮች።”
ወይም “ዘሮች።”
ቃል በቃል “የተሰጡ ነበሩ።”
ወይም “በግንብ በታጠሩት ሰፈሮቻቸው።”
ኢያሱ 21:13 ላይ በተጠቀሰው መሠረት “ከተማን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ኢያሱ 21:21 ላይ በተጠቀሰው መሠረት “ከተማን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ራሶች።”
ወይም “ሹፒምና ሁፒም።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
“ከመከራ ጋር” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “የሆሹዋን።” “ይሖዋ አዳኝ ነው” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “በዙሪያዋ።”
“ጋዛ” ማለትም ሊሆን ይችላል። ይሁንና በፍልስጤም የምትገኘውን ጋዛን አያመለክትም።
በ1ዜና 7:32 ላይ ሾሜር ተብሎም ተጠርቷል።
በ1ዜና 7:32 ላይ ከተጠቀሰው “ሆታም” ጋር አንድ ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ሜዳ።”
“ሚስቶቹን ይኸውም ሁሺምን እና ባዓራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ምድር ልጆች ወለደ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በዙሪያዋ።”
ኢሽቦሼት ተብሎም ተጠርቷል።
ሜፊቦስቴ ተብሎም ተጠርቷል።
ቃል በቃል “ደጋን የሚረግጡና።”
ወይም “ናታኒም።” ቃል በቃል “የተሰጡ ሰዎች።”
ቃል በቃል “ለአባቶቻቸው ቤት የአባቶች ራሶች ነበሩ።”
ወይም “ቤተ መቅደስ።”
ቃል በቃል “የድንኳኑን ቤት።”
ቃል በቃል “ኃያላን።”
ወይም “መመገቢያ ክፍሎችና።”
ገጸ ኅብስቱን ያመለክታል።
ወይም “በመመገቢያ ክፍሎቹ።”
ወይም “እንዳያንገላቱኝ።”
ወይም “በረባዳማው ሜዳ የነበሩት።”
ወይም “ቤተ መቅደስ።”
ወይም “የሥጋ ዘመዶችህ ነን።”
ቃል በቃል “እስራኤልን የምታስወጣውና የምታስገባው።”
ቃል በቃል “ራስና።”
ወይም “ከሚሎ።” “መሙላት” የሚል ትርጉም ያለው የዕብራይስጥ ቃል ነው።
ወይም “ይሖዋ መዳን አስገኘ።”
ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
ወይም “ነፍሳቸውን።”
ወይም “በነፍሳቸው።”
ቃል በቃል “የጀግና ልጅ።”
ቁመቱ 2.23 ሜትር ገደማ ነበር። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ለበሰ።”
ወይም “ከዳዊት ጋር ያበሩት ሰዎች ሁሉ መንታ ልብ አልነበራቸውም።”
ወይም “ከሺሆር።”
ወይም “እስከ ሃማት መግቢያ።”
“በኪሩቤል መካከል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
እዚህ ላይ የገባው የዕብራይስጥ ቃል፣ እርስ በርሱ ሲጋጭ ኃይለኛ ድምፅ የሚያወጣን ክብ ቅርጽ ያለው ከብረት የተሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ያመለክታል።
ወይም “አዘነ።”
“በዖዛ ላይ መገንፈል” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “ቤተ መንግሥት።”
ወይም “ቅጥር የሚሠሩ ግንበኞችንና።”
ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
“በመደረማመስ የተዋጣለት” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “ረባዳማውን ሜዳ።”
“ባካ” የሚለው ስም የዕብራይስጥ ቃል ነው። የተክሉ ዓይነት በትክክል አይታወቅም።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ያስታውሱ።”
“አስደናቂ ስለሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ተናገሩ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ያዘዘውን ቃል።”
ወይም “ክብርና።”
“ከቅድስናው ግርማ የተነሳ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ይሖዋን አምልኩ።”
ወይም “ፍሬያማ የሆነችው ምድር።”
ወይም “ልትናወጥ፤ ልትነቃነቅ።”
ወይም “መጥቷልና።”
ወይም “በውዳሴህ ሐሴት እንድናደርግ።”
ወይም “ይሁን!”
ወይም “የእውነተኛውን አምላክ መዝሙር መሣሪያዎች።”
ወይም “ቤተ መንግሥት።”
“ከአንዱ የድንኳን ስፍራ ወደ ሌላው፣ ከአንዱም የመኖርያ ቦታ ወደ ሌላው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “አያደክሟቸውም።”
ወይም “ሥርወ መንግሥት እንደሚያቋቁምልህ።”
ወይም “ትልቅ ቦታ እንዳለው ሰው።”
ወይም “ከፈቃድህ ጋር በሚስማማ ሁኔታ።”
ወይም “የታመነ።”
ወይም “ሥርወ መንግሥት የማቋቋም።”
ወይም “በዙሪያዋ።”
ወይም “አዳነው።”
በ2ሳሙ 8:9, 10 ላይ ቶአይ ተብሎም ተጠርቷል።
ወይም “አዳነው።”
ቃል በቃል “ከአራምናሃራይም።”
አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ቃል በቃል “እጅ።”
ኤፍራጥስን ያመለክታል።
በ2ሳሙ 10:16 ላይ ሾባክ ተብሎም ተጠርቷል።
የበልግን ወቅት ያመለክታል።
ይህ የአሞናውያን ጣዖት ሳይሆን አይቀርም፤ በሌላ ቦታ ላይ ሞሎክ ወይም ሚልኮም ተብሎም ተጠርቷል።
አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
በ2ሳሙ 21:18 ላይ ሳፍ ተብሎም ተጠርቷል።
“ተቃዋሚ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “አዘነ።”
በ2ሳሙ 24:16 ላይ አረውና ተብሎም ተጠርቷል።
ቃል በቃል “ስጠኝ።”
ጥርስ መሳይ ጉጦች ያሉት የእህል መውቂያ።
አንድ ሰቅል 11.4 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “አልበሰለም።”
ቃል በቃል “የእረፍት።”
“ሰላም” የሚል ትርጉም ካለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ነው።
አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ባረጀና ዕድሜ በጠገበ።”
ወይም “ደለደላቸው።”
በ1ዜና 23:11 ላይ ዚዛህ ተብሎም ተጠርቷል።
በ1ዜና 24:20 ላይ ሹባኤል ተብሎም ተጠርቷል።
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንድሞቻቸው።”
ገጸ ኅብስቱን ያመለክታል።
በ1ዜና 24:20 እና 25:20 ላይ ሹባኤል ተብሎም ተጠርቷል።
ቃል በቃል “ቀንዱን ከፍ ያደርግ ዘንድ።”
ወይም “ለአምላክ የተሰጡ ነገሮች።”
በ1ዜና 26:25, 26 ላይ ሸሎሞት ተብሎም ተጠርቷል።
ቃል በቃል “በእስራኤልም ላይ ቁጣ ስለሆነ።”
ወይም “በረባዳማ ሜዳዎቹ።”
ቃል በቃል “በእንስት አህዮቹ።”
ወይም “ሚስጥረኛ።”
ወይም “ሙሉ በሙሉ ለእሱ በማደር።”
ወይም “በፈቃደኛ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “የማስተሰረያውን ቤት።”
ወይም “ለአምላክ የተሰጡት ነገሮች።”
ገጸ ኅብስቱን ያመለክታል።
ወይም “አልበሰለም።”
ወይም “ግንቡ፤ ቤተ መንግሥቱ።”
አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ዳሪክ የፋርስ የወርቅ ሳንቲም ነበር። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ክብር።”
ወይም “በታማኝነት፤ በቅንነት።”
ወይም “ሙሉ በሙሉ ለአንተ ያደረ።”
ወይም “ግንብ፤ ቤተ መንግሥት።”
ቃል በቃል “ቀናት።”
ቃል በቃል “ቀናት።”
የዕብራይስጡ ቃል በአምላክ እርዳታ መለኮታዊውን ፈቃድ ማስተዋል የቻለን ሰው ያመለክታል።